ጉግል እንዴት ነው የእኔን ግላዊ ሁኔታ እና መረጃዎቼን ሊጠብቅልኝ የሚችለው

የግል ሁኔታዎንና ደህንነትዎን እንደዋና ነገር አድርገው እንደሚያዩት እናውቃለን፡፡ እናም ይህን እንደዋና ነገር አድርገን እናየዋለን፡፡ ለእርሶ መረጃዎች ጠንካራ ጥበቃ መስጠት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ሲሆን በዚህም መተማመን እንዲያድርቦት እና ባስፈለገዎት ጊዜ መረጃዎን እንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡

ጠንካራ ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ ግላዊነትዎን ለመጠበቅ እና Googleን ለእርስዎ ይበልጥ ውጤታማ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ለማድረግ ያለማቋረጥ እየሰራን ነው። የመረጃዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለደህንነት ወጪ እናደርጋለን እና በውሂብ ደህንነት በዓለም የታወቁ ባለሙያዎችን እንቀጥራለን። እንዲሁም እንደ Google ዳሽቦርድ፣ ባለ-2-ደረጃ ማረጋገጫ እና በየእኔ የማስታወቂያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙትን ግላዊነትን የተላበሱ የማስታወቂያ ቅንብሮች ጨምሮ ለአጠቃቀም ቀላል የሆኑ የግላዊነት እና የደህንነት መሣሪያዎችን ገንብተናል። ስለዚህ በGoogle የሚያጋሩት መረጃን በተመለከተ የሚቆጣጠሩት እርስዎ ነዎት።

የGoogle ደህንነት ማዕከል ላይ ራስዎን እና ቤተሰብዎን በመስመር ላይ እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ጨምሮ በመስመር ላይ ስላለ ጥንቃቄ እና ደህንነት ተጨማሪ ማወቅ ይችላሉ።

እንዴት የግል መረጃዎን የግል እና የተጠበቀ እንደሆነ እንደምናቆይ — እና እርስዎን ተቆጣጣሪ እንደምናደርግ — ተጨማሪ ይወቁ

የእኔ መለያ ከአገር ጋር የተጎዳኘው ለምንድን ነው?

የሚከተሉትን ሁለት ነገሮችን ለመወሰን እንድንችል የእርስዎ መለያ በአገልግሎት ውሉ ውስጥ ካለው አገር (ወይም ግዛት) ጋር ተጎዳኝቷል።

  1. አገልግሎቶቹን የሚያቀርበው፣ የእርስዎን መረጃ የሚያሰናዳው እና የሚመለከታቸው በግላዊነት ሕጎቹ የመገዛት ኃላፊነቱን የሚወስደው የGoogle አጋር። በአጠቃላይ፣ Google ከሁለቱ ኩባንያዎች ውስጥ በአንዱ በኩል የደንበኛ አገልግሎቶቹን ያቀርባል፦
    1. Google Ireland Limited፣ በአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ ቀጠና (አኅ አገሮች እንዲሁም አይስላንድን፣ ሊቸተንስቴንን እና ኖርዌይን ጨምሮ) ወይም ስዊዘርላንድ ውስጥ እርስዎ የሚገኙ ከሆነ
    2. Google LLC፣ በአሜሪካ ውስጥ፣ በተቀረው ዓለም ውስጥ ለሚገኙ
  2. ግንኙነታችንን የሚገዙት የደንቦች ስሪት እንደ የአካባቢው ሕጎች ሊለያዩ ይችላሉ

የGoogle አገልግሎቶች በመሠረቱ አገልግሎቶቹን የሚያቀርበው አጋር ወይም የአገርዎን ጉድኝት ምንም ይሁኑ አንድ ዓይነት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ ያስገቡ።

ከእርስዎ መለያ ጋር የተጎዳኘውን አገር መወሰን

እርስዎ አዲስ መለያ ሲፈጥሩ መለያዎን እርስዎ የGoogle መለያዎን በፈጠሩበት አገር ላይ ተመስርተን ከአንድ አገር ጋር እናጎዳኘዋለን። ቢያንስ አንድ ዓመት ለሆናቸው መለያዎች እርስዎ አብዛኛውን ጊዜ የGoogle አገልግሎቶችን የሚደርሱበትን አገር — ባለፈው ዓመት አብዛኛውን ጊዜዎን ያሳለፉበትን አገር — እንጠቀማለን።

በተደጋጋሚ መጓዝ በአጠቃላይ ከመለያዎ ጋር በሚጎዳኘው አገር ላይ ተጽዕኖ አይፈጥርም። ወደ አዲስ አገር ለመኖር ከሄዱ የአገርዎ ጉድኝት ለመዘመን አንድ ዓመት ገደማ ሊወስድ ይችላል።

ከእርስዎ መለያ ጋር የተጎዳኘው አገር ከመኖሪያ አገርዎ ጋር የማይዛመድ ከሆነ ይህ እርስዎ በሚሠሩበት እና በሚኖሩበት አገር መካከል ባለ ልዩነት፣ እርስዎን አይፒ አድራሻ ለመሸፈን ምናባዊ የግል አውታረ መረብ (ቪፒኤን) ስለጫኑ ወይም ከድንበር ቦታ አቅራቢያ ስለሚኖሩ የተነሣ ሊሆን ይችላል። የእርስዎ አገር ጉድኝት የተሳሳተ ነው ብለው ካመኑ እኛን ያነጋግሩን

በምን አይነት ሁኔታ ነው በጉግል ላይ ያለውን የራሴን መረጃ ከሰርች ውጤቶች ማውጣት የምችለው?

የጉግል ፍለጋ ውጤቶች ለሁሉም የሚዳረሱት መረጃዎች አካሎች ናቸው፡፡ ሰርች ኤንጅኖች በቀላሉ መረጃዎችን ከድረ ገጽ ማስወገድ ከፈለጉ መረጃው የተቀመጠበትን በ ዌብ ማስተሩን ማነጋገር በመገናኘት የመረጃ ለውጥ እንዲደረግ ይጠይቃሉ፡፡እንዴ መረጃው ከተወገደ እና ጉግልም ይህን ከመዘገበ በኋላ ይህ መረጃ በጉግል ፍለጋ ውጤት ላይ አይታይም፡፡ የመረጃ ማስወገድ አስቸኳይ ከሆነ የእኛን ሄልፕ ፔጅ ለተጨማሪ መረጃ የእገዛ ገጾችን መጎብኘት ይችላሉ፡፡

የጉግል ፍለጋ ውጤትን በምንነካበት ጊዜ የፍለጋ ጥያቄዎቼ ወደ ድረ ገጽ ይላካሉን?

በተለምዶ፣ አይ። በGoogle ፍለጋ ውስጥ የፍለጋ ውጤት ላይ ጠቅ ሲያደርጉ፣ የድር አሳሽዎ የተወሰነ መረጃ ወደ መድረሻው ድረ-ገጽ ይልካል። የፍለጋ ቃላትዎ በፍለጋ ውጤቶች ገጽ በይነመረብ አድራሻ ወይም ዩአርኤል ላይ ሊታዩ ይችላሉ፣ ነገር ግን Google ፍለጋ አሳሾችን ያንን ዩአርኤል ወደ መድረሻ ገጹ እንደ ላኪ ዩአርኤል እንዳይልኩ እንዲከላከል የታሰበ ነው። የፍለጋ መጠይቆችን በGoogle በመታየት ላይ ያሉ እና Google ፍለጋ Console በኩል እናቀርባለን፣ ነገርግን ይህን ስናደርግ በብዙ ተጠቃሚዎች የተሰጡ መጠይቆችን ብቻ እንድናጋራ ጥያቄዎችን አንድ ላይ እንሰበስባለን።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ