ይሄ በማህደራችን የተመዘገበ የግላዊነት ፖሊሲያችን ስሪት ነው። ያሁኑን ስሪት ወይም ሁሉንም ያለፉት ስሪቶች እይ።

የግላዊነት መምሪያ

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፦ 27 ጁላይ 2012 (የተመዘገቡ ስሪቶችን አሳይ)

መረጃን ለመፈለግ እና ለማጋራት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘት ወይም አዲስ ይዘት ለመፍጠር – አገልግሎቶቻችንን መጠቀም የምትችልበት የተለያዩ በርካታ መንገዶች አሉ። ከኛ ጋር መረጃ ስታጋራ፣ ለምሳሌ የGoogle መለያ በመፍጠር፣ የበለጠ ተዛማጅነት ያላቸውን የፍለጋ ውጤቶች እና ማስታወቂያዎች ለማሳየት፣ ከሰዎች ጋር እንድትገናኝ ለማገዝ፣ ወይም ከሌሎች ጋር መጋራትን የበለጠ ፈጣን እና ቀላል ለማድረግ – እነዚያን አገልግሎቶች የበለጠ የተሻሉ እንዲሆኑ እናደርጋለን። የኛን አገልግሎቶች እንደመጠቀምህ፣ እንዴት መረጃን እንደምንጠቀም እና ግላዊነትህን መጠበቅ የምትችልባቸው መንገዶችን በተመለከተ ግልጽ እንዲሆንልህ እንፈልጋለን።

የኛ የግላዊነት ፖሊሲ የሚከተለውን ያስረዳል፦

  • ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ እና ለምን እንደምንሰበስብ።
  • መረጃውን እንዴት እንደምንጠቀምበት።
  • እንዴት መረጃን መዳረስ እና ማዘመን እንሚቻል ጨምሮ የምናቀርባቸው አማራጮች።

ፖሊሲውን በተቻለ መጠን ቀላል እንዲሆን ለማድረግ ሞክረናል፣ ሆኖም ግን እንደ ኩኪስ /Cookies/፣ አይፒ አድራሻ /IP Address/፣ ፒክሴል መለያ /pixel tags/ እና አሳሾች0020/Browsers/ ለመሳሰሉት ቃላት አዲስ ከሆንክ፣ በመጀመሪያ ስለነዚህ ቁልፍ ቃላት ትርጉም አንብብ። አዲስ የጉግል ተጠቃሚም ሆንክ የጉግል የረዥም ጊዜ ደንበኛ፣ ያንተን የግላዊነት መብት ማስጠበቅ ለGoogle የሚያሳስበው ጉዳይ ነው፣ ስለሆነም እባክህ ጊዜ ወስደህ ስለኛ አሰራር ለማወቅ ሞክር – ጥያቄ ካለህም አግኘን።

የምንሰበስበው መረጃ

መረጃ የምንሰበስበው ለተጠቃሚዎቻችን የተሽለ ይአገልግሎት ለመስጠት አንድንችል ነው ይህም ምን አይነት ÌንÌ አንደምትናገር ከማወቅ አንስቶ የትኞቹን ማስኝታወቂንያዎች በጣም ጠቃሚ ሆነው አንዳገኘሃቸው ወይም በድረገጽ ከምታገኛቸው ሰዎች መካከል ላንተ አስፈላጊ የሆኑት የትኞቹ አንደሆኑ ማወቅን የመሳሰለውን ከበድ ያለ መረጃ መሰብሰብን ይጨምራል።

በሁለት መንገድ መረጃ እንሰበስባለን፦

  • በምትሰጠን መረጃ። ለምሳሌ፣ አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን የGoogle አድራሻ አንዲኖርህ የሚጠይቁ ናቸው። የGoogle አድራሻ ስትከፍት ስምህን፣ የኢሜይል አድራሻህን፣ የስልክ ቁጥርህን ወይም የክሬዲት ካርድህን የመሳስሉ የግል መረጃ እንጠይቅሃለን። በምንሰጣቸው የመረጃ ማጋራት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለግህ ምናልባት ስምህን እና ፎቶህን ያካተተ በይፋ የሚታይ Google መገለጫ እንድትፈጥር ልንጠይቅህ እንችላለን።

  • አገልግሎታችንን ስትጠቀም የምናገኘው መረጃ። ስለምትጠቀማቸው አገልግሎቶች እና እንዴት እንደምትጠቀምባቸው፣ ለምሳሌ አንድ የኛን ማስታወቂያ አገልግሎቶች የሚጠቀም ድረ ገጽ ስትጎበኝ ወይም የኛን ማስታወቂያዎች እና አይተህ ምላሽ በምት ሰጥበት ወቅት መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን። መረጃው የሚከተለውን ያካትታል። መረጃው የሚከተለውን ያካትታል፦

    • የምትጠቀምበትን ኮምፒዩተር ወይም ፕሮግራም የሚመለከት መረጃ

      መገልገያ-ተኮር መረጃ (ያንተ ሃርድዌር ሞዴል፣ ኮምፒዩተርህ የሚሰራበትን ስርዓት አይነት (operating system version)፣ መሳሪያ ለይቶ አዋቂዎች፣ እና የስልክ ቁጥርን ጨምሮ የሞባይል ኔትወርክ መረጃዎችን የመሳሰሉ) እንሰበስባለን። Google የኮምፒዩተር መሳሪያ መለያዎችህን ወይም ስልክ ቁጥርህን ከGoogle መለያህ ጋር ሊያዛምድ ይችላል።

    • ምዝግብ ማስታወሻ መረጃ

      አገልግሎቶቻችንን ስትጠቀም ወይም በGoogle የቀረበ ይዘትን ስታይ በአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች ላይ የተወሰነ መረጃ በራስሰር ልንሰበስብ እና ልናከማች እንችላለን። ይህ የሚከተለውን ሊያካትት ይችላል፦

      • አገልግሎታችንን እንዴት እንደተጠቀምክ ለምሳሌ የፍለጋ ጥያቄዎችህን ዝርዝሮች።
      • የስልክ ቁጥርህን፣ የደወለልህን ወገን ስልክ ቁጥር፣ የተላለፉ ቁጥሮች፣ የጥሪ ጊዜ እና ቀን፣ የጥሪው ቆይታ ጊዜ፣ ኤስኤምኤስ የተላለፈበት መሾመር መረጃ እና የጥሪ ዓይነቶችን የመሳሰሉ በስልክ አጠቃቀም ወቅት የሚመዘገቡ መረጃዎች
      • የበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ።
      • እንደ ብልሽቶች፣ የስርዓት እንቅስቃሴ፣ የሃርድዌር ቅንጅቶች፣ የአሳሽ ዓይነት፣ አሳሽ ቋንቋ፣ የጥያቄህ ቀን እና ጊዜ እና ማጣቀሻ ዩአርኤል ያለ የመሳሪያ ሁኔታ መረጃ
      • አሳሽህን ወይም የGoogle መለያህን በልዩ ሁኔታ ለይተው ሊያውቁ የሚችሉ ኩኪዎች።
    • የአካባቢ መረጃ

      አድራሻን ለይቶ የሚጠቁም የGoogle አገልግሎት የምትጠቀም ከሆነ ስላለህበት ስፍራ፣ ከሞባይል መሳሪያ የተላኩ እንደ ጂፒኤስ ሲጊናሎች ያሉ መረጃዎችን ልንሰበስብ እና ወደ መረጃ ስርዓታችን ልናስገባቸው እንችላለን። አካባቢን ለይቶ ለመወሰን ከመሳሪያህ ላይ ለምሳሌ በቅርብ ካለ Wi-Fi መዳረሸ ነጥቦች እና ሕዋስ ማማዎች መረጃ ሊሰጥ የሚችል ውሂብ አነፍናፊ ያሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ልንጠቀም እንችላለን።

    • ልዩ መተግበሪያ ቁጥሮች

      የተወሰኑ አገልግሎቶች ልዩ መተግበሪያ ቁጥር ያካትታሉ። ስለ አጫጫንህ (ለምሳሌ፣ የክወና ስርዓት ዓይነት እና የመተግበሪያ ስሪት ቁጥር) ያንን አገልግሎትን ስትጭን ወይም ስታራግፍ ወይም ያ አገልግሎት ለምሳሌ ለራስ ሰር ዝማኔዎች በተወሰነ ጊዜ ወቅት ጠብቆ የኛን አገልጋዮች ሲገናኝ ይህ ቁጥር እና መረጃ ወደ Google ሊላክ ይችላል።

    • አካባቢያዊ ማከማቻ

      እንደ አሳሽ ድር ማከማቻ (HTML 5 ያሉትን ጨምሮ) እና የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫዎች ያሉ ስልቶችን በመጠቀም በመሳሪያህ ላይ በአካባቢ ደረጃ መረጃን (የግል መረጃን ጨምሮ) ልንሰበስብ እና ልናከማች እንችላለን።

    • ኩኪዎች እና ማንነታቸው ያልተወቀ ለይቶ አዋቂዎች

      የGoogle አገልግሎት ስትጎበኝ መረጃ ለመሰብሰብ እና ለማከማቸት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን አና ይህ አንድ ወይም ከዛ በላይ ኩኪዎች ወይም ማንነታቸው ያልታወቁ ለይቶ አዋቂዎች ወደ መሳሪያህ መላክን ሊያካትት ይችላል። በተጨማሪ ለአጋሮቻችን በምናቀርባቸው አገልግሎቶች ጋር ማለትም እንደ ማስታወቂያ ማስነገር አገልግሎቶች ወይም በሌሎች ጣቢያዎች ላይ ብቅ የሚሉ የGoogle ባህሪያት ጋር መልዕክት ስትለዋወጥ ኩኪዎች እና ማንነታቸው ያልታወቁ ለይቶ አዋቂዎችን እንጠቀማለን።

የምንሰበስበውን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም

ከሁሉም አገልግሎቶቻችን የምንሰበስበውን መረጃ ለሌሎች ለማቅረብ፣ ለመጠገን፣ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ እና ለማሻሻል እንዲሁም አዳዲሶችን ለመገንባት እና የGoogle እና የኛን ተጠቃሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ እንጠቀምበታለን። ይህን መረጃ ለአንተ በልክ የተዘጋጀ ይዘት ለማቅረብ – ማለትም እንደ ለፍለጋ ውጤቶች እና ማስታወቂያዎች የበለጠ ተዛማጅነት ያላቸው መረጃዎችን ለመስጠት እንጠቀምበታለን።

ለሁሉም የGoogle መለያ የሚጠይቁ አገልግሎቶች በሙሉ ለGoogle መገለጫ የሰጠኸውን ስም ልንጠቀምበት እንችላለን። በተጨማሪ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻችን ዙሪያ በወጥነት እንድትወከል ከGoogle መለያህ ጋር የተቆራኙ ሌሎች የዱሮ ስሞችህን ልንተካቸው እንችል ይሆናል። ሌሎች ተጠቃሚዎች ቀደም ሲል ኢሜይልህ ወይም ሌላ ማንነትህን የሚገልጽ መረጃ ያላቸው ከሆነ፣ እንደ ስምህ እና ፎቶህ ያለ በይፋ የሚታይ የGoogle መገለጫ መረጃህን ልናሳያቸው እንችል ይሆናል።

Googleን ስትገናኝ፣ እያጋጠመህ ያለውን ማናቸውም ችግር ለመፍታት እንዲረዳ ስላደረግከው ግንኙነት ሪኮርድ ልንይዝ እንችል ይሆናል። የኢሜይል አድራሻህን ስለአገልግሎቶቻችን መረጃ ለመስጠት ማለትም እንደ በቅርቡ ስለሚደረጉ ለውጦች ወይም መሻሻሎች ያሉ መረጃዎችን ላንተ ለመስጠት ልንጠቀምበት እንችል ይሆናል።

የተጠቃሚ ተሞክሮህን እና የአገልግሎቶቻችንን አጠቃላይ ጥራት ደረጃ ለማሻሻል እንደ ፒክሴል ስያሜዎች ካሉ ኩኪዎች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን እንጠቀማለን። ለምሳሌ፣ የቋንቋ ምርጫችህን በማስቀመጥ፣ በምትመረጠው ቋንቋ አገልግሎቶቻችን እንዲታዩህ ለማድረግ እንችላለን። በልክ የተዘጋጁ ማስታወቂያዎችን ስናሳይህ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በስነጾታ ተራክቦ ቅኝት ወይም ጤና በመሳሰሉ ስሜት ሊጎዱ በሚችሉ አደገኛ ምድቦች ጋር ኩኪ ወይም ማንነቱ ያልታወቀ ለይቶ አዋቂን አናቆራኝም።

ከሌሎች Google አገልግሎቶች የሚገኝ መረጃን፣ የግል መረጃን ጨምሮ፣ – ለምሳሌ ልታውቃቸው ከምትችል ሰዎች ጋር ማጋራትን ቀለል ለማድረግ ሲባል ከአንዱ አገልግሎት የሚገኘውን የግል መረጃ ከሌሎቹ ጋር ልናጣምረው እንችል ይሆናል። በመርጠህ-ግባ ስምምነትህን ካልገለጽክልን በቀር የDoubleClick ኩኪ መረጃን በግል ተለይቶ ሊታወቅ ከሚችል መረጃ ጋር አናጣምርም።

በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ከተቀመጡት ምክንያቶች እና ሁኔታዎች ውጪ መረጃህን መጠቀም ቢያስፈልገን በቅድሚያ ፈቃደኛ መሆንህን እንጠይቅሃለን።

Google የግል መረጃዎችን በመላ ዓለም በሚገኙ በርካታ ሃገሮች በኛ አገልጋዮች አማካኝነት ያስኬዳል። የግል መረጃህን ከምትኖርበት ሃገር ውጪ ባለ አገልጋይ ላይ ልናስኬደው እንችል ይሆናል።

የአሰራር ግልጽነት እና ምርጫዎች

ሰዎች የተለያዩ ስለግላዊነት መብት የሚያሳስቡዋቸው ነገሮች አሉ። መረጃው እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል አውቀህ ትርጉም ያለው ምርጫ እንድታደርግ፣ ዓላማችን ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ ግልጽ ሆኖ መገኘት ነው። ለምሳሌ፣ የሚከተለውን ማድረግ ትችላለህ፦

  • ከGoogle መለያህ ጋር የተሳሰሩ የተወሰኑ መረጃዎችን Google Dashboard በመጠቀምመገምገም እና መቆጣጠር።
  • የማስታወቂያዎች ምርጫዎች አስተዳዳሪን በመጠቀም እንደ የትኞቹ ምድቦች እንደሚሻሉህ የማስታወቂያ ምርጫዎችህን ማየት እና አርትዕ ማድረግ። የተወሰኑ የGoogle ማስታወቂያ ማስነገር አገልግሎቶችን እዚህ ላይ መርጠህ አልፈልግም ብለህ መርጠህ መውጣት ትችላለህ።
  • የGoogle መገለጫህ ለተወሰኑ ግለሰቦች እንዴት እንደሚታያቸው ለማየት እና ለማስተካከል የኛን አርታኢ መጠቀም።
  • ከማን ጋር መረጃ እንደምትጋራ መቆጣጠር።
  • ከበርካታዎቹ የኛ አገልግቶች መረጃ መውሰድ።

ከኛ አገልግሎቶች ጋር የተጣመሩ ኩኪዎችን ጨምሮ፣ ሁሉንም ኩኪዎች ለማገድ ወይም ኩኪ በኛ ሲቀናበር እንዲጠቁምህ አሳሽህን ማቀናበር ጭምር ትችላለህ። ሆኖም ግን፣ ኩኪዎችህ እንዲቦዝኑ ከተደረጉ በርካታዎቹ የኛ አገልግሎቶች በሚገባ ሊሰሩ የማይችሉበት ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፣ የቋንቋ ምርጫህን ላናስታውስ እንችላለን።

የምታጋራው መረጃ

በርካታዎቹ የኛ አገልግሎቶች መረጃ ከሌሎች ጋር እንድትጋራ ያስችሉሃል። በይፋ መረጃ ስታጋራ፣ በፍለጋ ፕሮግራሞች፣ Googleን ጨምሮ ዋቢ ሊደረግ እንደሚችል አስታውስ። አገልግሎቶቻችን በማጋራት እና ይዘትህን በማስወገድ ረገድ በርካታ አማራጮችን ይሰጡሃል።

የግል መረጃህን መድረስ እና ማዘመን

አገልግሎቶቻችን በማናቸውም ጊዜ ስትጠቀም፣ ወደ ግል መረጃ መዳረስ እንድትችል ማድረግ ዓላማችን ነው። መረጃው የተሳሳተ ከሆነ፣ መረጃውን ለህጋዊ የንግድ ስራ ምክንያት ወይም ለሕግ ጉዳይ ከኛ ጋር ማስቀረት ካልተገደድን በቀር – መረጃውን በፍጥነት ልታዘምን የምትችልበትን ወይም ልትሰርዝ የምትችልበትን አማራጭ መንገዶች ለማቅረብ ተግተን እንሰራለን። የግል መረጃህን ስታዘምን፣ ጥያቄህን ከማስተናገዳችን በፊት ማንነትህን እንድታረጋግጥልን ልንጠይቅህ እንችል ይሆናል።

ያለምንም ምክንያት ተደጋጋሚ የሆኑ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ የቴክኒክ ጥረት የሚጠይቁ (ለምሳሌ፣ አዲስ ስርዓት መገንባት ወይም ያለ አሰራርን ከስር መሰረቱ መቀየር)፣ የሌሎችን ግላዊነት መብት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ፣ ወይም ከልክ በላይ ሊፈጸም የማይችል (ለምሳሌ፣ በምትኬ ቴፖች ላይ የተቀመጠን መረጃ ለማግኘት የሚቀርቡ ጥያቄዎች) ወድቅ ልናደርገው እንችላለን።

ያልተመጣጠነ ጥረት የሚጠይቅ እስካልሆነ ድረስ መረጃ መዳረሻ እና ማስተካከያ መስጠት ችለን ስንሰጥ በነጻ ነው የምንሰጠው። አገልግሎቶቻችንን ከድንገተኛ እና ከጎጂ ጥፋቶች ለመጠበቅ ዓላማችን ነው። በዚህ ምክንያት፣ ከአገልግሎቶቻችን መረጃ ከሰረዝክ በኋላ፣ ትራፊ ቅጂዎችን ከንቁ አገልጋዮች ወዲያውኑ ላንሰርዝ እና ከምትኬ ስርዓቶቻችን ላናስወግድ እንችላለን።

የምናጋራው መረጃ

ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ካላስገደደ በቀር የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ከኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አንሰጥም።

  • በራስህ ፈቃድ

    የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ከኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር ፈቃድህን ስናገኝ የግል መረጃህን እንሰጣለን። ማናቸውንም ስሜት ሊጎዱ የሚችሉ የግል መረጃዎች ለማጋራት መርጠህ-ግባ ፈቃድ መስጫን እንጠይቃለን።

  • ከጎራ አስተዳዳሪዎች ጋር

    የGoogle መለያህ በጎራ አስተዳዳሪ የሚተዳደር ከሆነ (ለምሳሌ፣ ለGoogle መተግበሪያዎች ተጠቃሚዎች) ወደ Google መለያ መረጃህ (ኢሜይልህን እና ሌሎች ውሂቦችን ጨምሮ) ለድርጅትህ የተጠቃሚ ድጋፍ የሚሰጡ የጎራ አስተዳዳሪ እና አከፋፋይ ሻጮች ወደ መለያህ መረጃ መዳረሻ ይኖራቸዋል። የጎራ አስተዳዳሪህ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፦

    • የድረገጽ አድራሻህን አጠቃቀም የሚመለከት (ለምሳሌ አዳዲስ ፕሮግራሞች ጭነህ አንድሆነ) ስታስቲክስን ማየት።
    • የመለያህን የይለፍ ቃል መለወጥ።
    • የመለያህን መዳረሻ ለጊዜው ማገድ ወይም ከናካቴው ማቋረጥ።
    • በመለያህ እንደ አንድ አካል ሆኖ የተቀመጠን መረጃ መድረስ ወይም መያዝ።
    • ተገቢነት ያለውን ሕግ፣ ደንብ ለማስከበር፣ ሕጋዊ ሂደት ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የመለያህን መረጃ መቀበል።
    • መረጃ ወይም የግላዊነት ቅንብሮችህን የመሰረዝ ወይም አርትዖት የማድረግ ችሎታህን መገደብ።

    ለበለጠ መረጃ የጎራህን አስተዳዳሪ የግላዊነት መረጃ እባክህ ተመልከት።

  • መረጃዎችን ከGoogle ውጭ ለሆኑ አካላት መስጠት

    በመመሪያዎቻችን መሰረት እና በግላዊነት ፖሊሲዎቻችን እና ሌሎች ተገቢነት ያላቸው የሚስጢራዊነት እና የደህንነት እርምጃዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ለተባባሪዎቻችን ወይም ሌሎች የታመኑ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን እኛ ለምንፈልገው ዓላማ እንዲያጠናክሩት እንሰጣለን።

  • ለህጋዊ ምክንያቶች

    ከGoogle ውጪ ላሉ ወደ ግል መረጃ በመድረስ፣ በመጠቀም፣ በማስቀመጥ ወይም ለሌሎች በመግለጽ ላይ ጥሩ እምነት ለምንጥልባቸው ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን በሚከተሉት ሁኔታዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እናጋራለን፦

    • ማናቸውንም ተገቢ ህግ፣ ደንብ፣ የህግ አካሄድ ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የሚያስፈልገውን መስፈርት አሟልተው ሲገኙ፤
    • ተገቢነት ያላቸውን የአገልግሎት ውሎች ሊፈጸም የሚችል የሕግ ጥሰትን ጨምሮ ለማስፈጸም፤
    • ለወንጀል ምርመራ፣ ለመከላከል ወይም በሌላ መልኩ የማጭበርበር ስራን ለማጋለጥ፣ ለደህንነት ወይም ቴክኒካዊ ጉዳዮች፤
    • ህግ በሚፈቀደውና በሚጠይቀው መልኩ በGoogle፣ የኛ ተጠቃሚዎች ወይም የሕዝቡን መብቶች፣ ንብረቶች ወይም ደህንነቶች ላይ ሊደረስ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል፤

እንደ አሳታሚዎች፣ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ወይም የተገናኙ ጣቢያዎች ካሉ አጋሮቻችን ጋር – በጣምራ በግል-ተለይቶ ሊታወቅ የማይችል መረጃ በይፋ ልንጋራ እንችላለን። ለምሳሌ፣ ስለአገልግሎቶቻችን አጠቃላይ አጠቃቀም በተመለከተ ያለውን አዝማሚያ ለማሳየት መረጃን በይፋ ልናጋራ እንችላለን።

Google ከሌላ ድርጅት ጋር ቢዋሃድ፣ ቢወረስ ወይም ንብረቱ ቢሸጥ፣ ማናቸውንም የግል መረጃ ምስጢራዊነት ጠብቀን እንቀጥላለን እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተጠቃሚዎችን የግል መረጃቸው ለሌላ ከመተላለፉ በፊት ወይም የሌላ የተለየ ግላዊነት ፖሊሲ ተገዢ ከመሆኑ በፊት ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው እናደርጋለን።

የመረጃ ደህንነት ጥበቃ

Google እና የኛን ተጠቃሚዎች ያልተፈቀደለት ሰው አንዳያገኘው ወይም አንዳይለውጠው ይፋ ማድረግ ወይም የያዝነው መረጃ ከመበላሸት ለመጠበቅ ጠንክረን እንሰራለን። በተለይ፦

  • አብዛኛዎቹን አገልግሎቶቻችንን SSL በመጠቀም እንመሰጥራለን።
  • የGoogle መለያህን ስትዳረስ ባለሁለት-ድርጃ ማረጋገጫ እና በGoogle Chrome ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የማሰስ ባህሪ እናቀርብልሃለን።
  • የኛን የመረጃ አሰባሰብ፣ አከመቻቸት እና ሂደት አካሄድ ልማዶች፣ አካላዊ የደህንነት እርምጃዎችን ጨምሮ ፈቃድ ካልተሰጠው ወደ ስርዓቶች መዳረስን ለመከላከል ስንል እንገመግማለን።
  • የግል መረጃን ለኛ ሂደት ለማስኬድ ሲሉ የግል መረጃን የሚፈልጉ የGoogle ሰራተኞች፣ ሾል ተቋራጮች እና ወኪሎች እንዲሁም በውል ሚስጢር እንዲጠብቁ ግዴታ ያለባቸውን ወደ ግል መረጃ መዳረሻ እንዳያገኙ እንገድባቸዋለን፣ እናም እነዚህን ግዴታዎችን ሳይወጡ ቢቀሩ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰደባቸው ወይም ስራቸው እንዲቋረጥ ሊደረግ ይችላል።

መተግበሪያ

የግላዊነት ፖሊሲያችን በሁሉም በGoogle Inc. እና ተባባሪዎቹ እንዲሁም በሌሎች ጣቢያዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች (እንደ ማስታወቂያ ማስነገር አገልግሎቶች ያሉ) ተፈጻሚ ሲሆን ይህን የግላዊነት ፖሊሲ የማያካትቱ የተለዩ የግላዊነት ፖሊሲዎችን የያዙ አገልግሎቶችን ግን አያካትትም።

የኛ የግላዊነት ፖሊሲ በሌሎች ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች እንዲሁም በፍለጋ ውጤቶችህ ላይ ሊታዩ የሚችሉ ምርቶችን ወይም ጣቢያዎችን፣ የGoogle አገልግሎቶችን የሚያካትቱ፣ ወይም ሌሎች ከኛ አገልግሎቶች ጋር የተገናኙ ጣቢያዎችን ጨምሮ ተፈጻሚ አይሆንም። የግላዊነት ፖሊሲያችን የኛን አገልግሎቶች የሚያስተዋውቁ እና ኩኪዎች፣ ፒክሴል ስያሜዎችን እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ተዛማጅነት ያላቸውን ለማስተናገድ እና ለማቅረብ የሚጠቀሙ ሌሎች ኩባንያዎች እና ድርጅቶች የመረጃ ልማዶችን አያካትትም።

አፈጻጸም

ከግላዊነት ፖሊሲያችን ጋር ምን ያክል እንደተጣጣምን በየጊዜው ግምገማ እናደርጋለን። በተጨማሪ በበርካታ የራስ መቆጣጠሪያ መሰረታዊ ስርዓተደንቦች እንገዛለን። መደበኛ የጽሑፍ ቅሬታዎች ስንቀበል፣ ክትትል እንዲያደርግ ቅሬታውን ያቀረበውን ሰው እናገኘዋለን። የግል ውሂብን ማስተላለፍ በተመለከተ የቀረበ ማናቸውንም ቅሬታዎች ከተጠቃሚዎቻችን ጋር በቀጥታ መፍታት ሳንችል ስንቀር ተገቢነት ካለቸው ቁጥጥር አድራጊ ባለስልጣኖች፣ የአካባቢ ውሂብ ደህንነት አስጠባቂ ባለስልጣኖች ጋር በጋራ እንሰራለን።

ለውጦች

የግላዊነት ፖሊሲያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለወጥ ይችላል። በግልጽ የተቀመጠ ፈቃድህን ሳናገኝ በዚህ ግላዊነት ፖሊሲ ላይ ያሉህን መብቶች አንቀንስም። ማናቸውንም የግላዊነት ፖሊሲ ለውጦች በዚህ ገጽ ላይ የምንለጥፍ ሲሆን የተደረጉት ለውጦች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ዓይነት ከሆኑ፣ የበለጠ ዋጋ የሚሰጠው ማሳወቂያ (ለተወሰኑ አገልግሎቶች፣ የግላዊነት ፖሊሲ ለውጦች ኢሜይል ማሳወቂያን ጨምሮ) እንልካለን። ለግምገማ እንዲረዳህ የዚህን የግላዊነት ፖሊሲ የቀድሞ እትሞች በቤተማህደር እናስቀምጣቸዋለን።

የተወሰኑ ምርት ልማዶች

የሚከተሉት ማሳወቂያዎች ልትጠቀምባቸው የምትችል ከተወሰኑ የGoogle ምርቶች እና አገልግሎቶች ጋር ያሉ ልዩ የተወሰኑ የግላዊነት ልማዶችን ያብራራሉ፦

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ