ይሄ በማህደራችን የተመዘገበ የግላዊነት ፖሊሲያችን ስሪት ነው። ያሁኑን ስሪት ወይም ሁሉንም ያለፉት ስሪቶች እይ።

የግላዊ ሁኔታ መመሪያ

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፦ 20 ዲሴምበር 2013 (የተመዘገቡ ስሪቶችን አሳይ)

አገልግሎቶቻችንን መጠቀም የሚችሉበት የተለያዩ በርካታ መንገዶች አሉ – መረጃን ለመፈለግ እና ለማጋራት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘት ወይም አዲስ ይዘት ለመፍጠር። ከእኛ ጋር መረጃ ሲያጋሩ፣ ለምሳሌ የGoogle መለያ በመፍጠር እነዚያን አገልግሎቶች የበለጠ የተሻሉ እንዲሆኑ እናደርጋለን – የበለጠ ተዛማጅነት ያላቸውን የፍለጋ ውጤቶች እና ማስታወቂያዎች ለእርስዎ ለማሳየት፣ እርስዎ ከሰዎች ጋር እንዲገናኙ ለማገዝ ወይም ከሌሎች ጋር መጋራትን የበለጠ ፈጣን እና ቀላል ለማድረግ። የእኛን አገልግሎቶች እንደሚጠቀሙ፣ እንዴት መረጃን እንደምንጠቀም እና ግላዊነትዎን መጠበቅ የሚችሉባቸውን መንገዶች በተመለከተ በግልጽ እንዲያውቁ እንፈልጋለን።

የእኛ የግላዊነት መምሪያ የሚከተለውን ያስረዳል፦

  • ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ እና ለምን እንደምንሰበስብ።
  • መረጃውን እንዴት እንደምንጠቀምበት።
  • መረጃን መድረስ እና ማዘመን የሚቻልበትን መንገድ ጨምሮ የምናቀርባቸው አማራጮች።

መምሪያውን በተቻለ መጠን ቀላል እንዲሆን ለማድረግ ሞክረናል፣ ሆኖም ግን እንደ ኩኪስ፣ የአይፒ አድራሻ፣ ፒክስል መለያዎች እና አሳሾች ለመሳሰሉት ቃላት አዲስ ከሆኑ በመጀመሪያ ስለነዚህ ቁልፍ ቃላት ትርጉም ያንብቡ። አዲስ የGoogle ተጠቃሚም ሆኑ የGoogle የረጅም ጊዜ ደንበኛ የእርስዎን የግላዊነት መብት ማስጠበቅ ለGoogle የሚያሳስበው ጉዳይ ነው፣ ስለሆነም እባክዎ ጊዜ ወስደው ስለእኛ አሰራር ለማወቅ ይሞክሩ - ጥያቄ ካለዎትም ይህንን ገጽ ያማክሩ

የምንሰበስበው መረጃ

መረጃ የምንሰበስበው ለተጠቃሚዎቻችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት አንድንችል ነው ይህም ምን አንደሚናገሩ ከማወቅ አንስቶ የትኞቹን ማስታወቂያዎች በጣም ጠቃሚ ሆነው አንዳገኟቸው ወይም በድረገጽ ከሚያገኟቸው ሰዎች መካከል ለእርስዎ አስፈላጊ የሆኑት የትኞቹ አንደሆኑ ማወቅን የመሳሰለውን ከበድ ያለ መረጃ መሰብሰብን ይጨምራል።

በሁለት መንገድ መረጃ እንሰበስባለን፦

  • እርስዎ የሚሰጡን መረጃ። ለምሳሌ አብዛኛዎቹ የእኛ አገልግሎቶች እርስዎ ለGoogle መለያ እንዲመዘገቡ ይጠይቅዎታል። ሲመዘገቡ እንደ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር ወይም ክሬዲት ካርድ የመሳሰሉትን የግል መረጃ እንጠይቅዎታለን። በምንሰጣቸው የማጋራት ባህሪያት በሙሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለጉ፣ በይፋ የሚታይ ስምዎን እና ፎቶዎን ያካተተ የGoogle መገለጫ እንዲፈጥሩ ልንጠይቅዎ እንችላለን።

  • የእኛን አገልግሎቶች በሚጠቀሙበት ወቅት የምናገኘው መረጃ። እርስዎ ስለሚጠቀሟቸው አገልግሎቶች እና እንዴት እንደሚጠቀሟቸው መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን፣ ለምሳሌ የእኛን የማስታወቂያ አገልግሎት የሚጠቀም አንድ ድር ጣቢያ ሲጎበኙ ወይም የእኛን ማስታወቂያዎች ወይም ይዘት ሲመለከቱ ወይም ከእነሱ ጋር ሲገናኙ። ይህ መረጃ የሚከተለውን ያካትታል፦

    • የመሳሪያ መረጃ

      መሳሪያ-ተኮር መረጃ (እንደ የእርስዎ ሃርድዌር ሞዴል፣ የክወና ስርዓት ስሪት፣ ልዩ መሳሪያ ለይቶ አዋቂዎች፣ እና የስልክ ቁጥርን ጨምሮ ተንቀሳቃሽ አውታረመረብ መረጃ ያሉ) እንሰበስባለን። Google የመሳሪያ ለይቶ ማወቂያዎችዎን ወይም ስልክ ቁጥርዎን ከGoogle መለያዎ ጋር ሊያዛምድ ይችላል።

    • ምዝግብ ማስታወሻ

      አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ ወይም በGoogle የቀረበ ይዘትን ሲመለከቱ፣ በአገልጋይ ምዝግቦች ላይ የተወሰነ መረጃ በራስሰር ልንሰበስብ እና ልናከማች እንችላለን። ይህ የሚከተለውን ሊያካትት ይችላል፦

      • አገልግሎታችንን እንዴት እንደተጠቀሙ ለምሳሌ የፍለጋ ጥያቄዎችዎን ዝርዝሮች።
      • እንደ የስልክ ቁጥርዎ፣ የደወለልዎ አካል ስልክ ቁጥር፣ የማስተላለፊያ ቁጥሮች፣ የጥሪዎች ጊዜ እና ቀን፣ የጥሪው ቆይታ ጊዜ፣ ኤስኤምኤስ ማስተላለፊያ መረጃ እና የጥሪዎች አይነቶች ያሉ የስልክ ምዝግብ መረጃዎች።
      • የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አማራጮች
      • እንደ ብልሽቶች፣ የስርዓት እንቅስቃሴ፣ የሃርድዌር ቅንጅቶች፣ የአሳሽ ዓይነት፣ አሳሽ ቋንቋ፣ የጥያቄዎ ቀን እና ጊዜ እና ማጣቀሻ ዩአርኤል ያለ የመሳሪያ ሁኔታ መረጃ።
      • አሳሽዎን ወይም የGoogle መለያዎን በልዩ ሁኔታ ለይተው ሊያውቁ የሚችሉ ኩኪዎች።
    • የስፍራ መረጃ

      በስፍራ-የነቃ የGoogle አገልግሎት የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ስለተጨባጩ ያሉበት ስፍራ፣ ከሞባይል መሳሪያ የተላኩ እንደ ጂፒኤስ ሲግናሎች ያሉ መረጃዎችን ልንሰበስብ እና ልናስኬዳቸው እንችላለን። አካባቢን ለይቶ ለመወሰን እንደ ከመሳሪያዎ ላይ ለምሳሌ በቅርብ ካለ Wi-Fi መዳረሻ ነጥቦች እና ሕዋስ ማማዎች መረጃ ሊሰጥ የሚችል ውሂብ አነፍናፊ ያሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ልንጠቀም እንችላለን።

    • ልዩ መተግበሪያ ቁጥሮች

      የተወሰኑ አገልግሎቶች ልዩ መተግበሪያ ቁጥር ያካትታሉ። ስለ አጫጫንዎ (ለምሳሌ፣ የክወና ስርዓት ዓይነት እና የመተግበሪያ ስሪት ቁጥር) ያንን አገልግሎትን ሲጭኑ ወይም ሲያራግፉ ወይም አገልግሎት ለምሳሌ ለራስ ሰር ዝማኔዎች በተወሰነ ጊዜ ወቅት ጠብቆ የእኛን አገልጋዮች ሲገናኝ ይህ ቁጥር እና መረጃ ወደ Google ሊላክ ይችላል።

    • አካባቢያዊ ማከማቻ

      እንደ አሳሽ ድር ማከማቻ (HTML 5 ያሉትን ጨምሮ) እና የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫዎች ያሉ ስልቶችን በመጠቀም በመሳሪያዎ ላይ በአካባቢ ደረጃ መረጃን (የግል መረጃን ጨምሮ) ልንሰበስብ እና ልናከማች እንችላለን።

    • ኩኪዎች እና ማንነታቸው ያልተወቀ ለይቶ አዋቂዎች

      የGoogle አገልግሎት ሲጎበኙ መረጃ ለመሰብሰብ እና ለማከማቸት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን፣ ይህም አንድ ወይም ከዚያ በላይ ኩኪዎች ወይም ማንነታቸው ያልታወቁ ለይቶ አዋቂዎችን ወደ መሳሪያዎ መላክን ሊያካትት ይችላል። በተጨማሪ ለአጋሮቻችን በምናቀርባቸው አገልግሎቶች ጋር ማለትም እንደ ማስታወቂያ ማስነገር አገልግሎቶች ወይም በሌሎች ጣቢያዎች ላይ ብቅ የሚሉ የGoogle ባህሪያት ጋር መልዕክት ሲለዋወጡ ኩኪዎች እና ማንነታቸው ያልታወቁ ለይቶ አዋቂዎችን እንጠቀማለን።

የምንሰበስበውን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም

ከሁሉም አገልግሎቶቻችን የምንሰበስበውን መረጃ ለሌሎች ለማቅረብ፣ ለመጠገን፣ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ እና ለማሻሻል እንዲሁም አዳዲሶችን ለመገንባት እና የGoogle እና የእኛን ተጠቃሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ እንጠቀምበታለን። ይህን መረጃ ለእርስዎ በልክ የተዘጋጀ ይዘት ለማቅረብ - ማለትም እንደ ለፍለጋ ውጤቶች እና ማስታወቂያዎች የበለጠ ተዛማጅነት ያላቸው መረጃዎችን ለመስጠት እንጠቀምበታለን።

ለሁሉም የGoogle መለያ የሚጠይቁ አገልግሎቶች በሙሉ ለGoogle መገለጫ የሰጡትን ስም ልንጠቀምበት እንችላለን። በተጨማሪ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻችን ዙሪያ በወጥነት እንዲወከሉ ከGoogle መለያዎ ጋር የተቆራኙ ሌሎች የዱሮ ስሞችዎን ልንተካቸው እንችል ይሆናል። ሌሎች ተጠቃሚዎች አስቀድመው የእርስዎ ኢሜይል ወይም እርስዎን ለይቶ የሚያሳውቅ ሌላ መረጃ ካላቸው በይፋ የሚታዩትን እንደ ስምዎ እና ፎቶዎ ያሉ የእርስዎን የGoogle መገለጫ መረጃዎች ልናሳያቸው እንችላለን።

ከGoogle አገልግሎት ሲገናኙ፣ እያጋጠዎ ያለውን ማናቸውም ችግር ለመፍታት እንዲረዳ ስላደረጉት ግንኙነት ሪኮርድ ልንይዝ እንችል ይሆናል። የኢሜይል አድራሻዎን ስለአገልግሎቶቻችን መረጃ ለመስጠት ማለትም በቅርቡ እንደሚደረጉ ለውጦች ወይም መሻሻሎች ያሉ መረጃዎችን ለእርስዎ ለመስጠት ልንጠቀምበት እንችላለን።

ከኩኪዎች እና እንደ ፒክስል መለያዎች ከመሳሰሉ ሌሎች ቴክኖሎጂዎች የተሰበሰቡትን መረጃዎች የእርስዎን የተጠቃሚ ተሞክሮ እና የእኛን አገልግሎቶች አጠቃላይ ጥራት ለማሻሻል እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ የእርስዎን የቋንቋ ምርጫዎች በማስቀመጥ የእኛን አገልግሎቶች እርስዎ በመረጡት ቋንቋ እንዲኖረን ማድረግ እንችላለን። በልክ የተዘጋጁ ማስታወቂያዎችን ስናሳይዎ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በስነጾታ ተራክቦ ቅኝት ወይም ጤና በመሳሰሉ ስሜት ሊጎዱ በሚችሉ አደገኛ ምድቦች ጋር ኩኪ ወይም ማንነቱ ያልታወቀ ለይቶ አዋቂን አናቆራኝም።

ከሌሎች Google አገልግሎቶች የሚገኝ መረጃን፣ የግል መረጃን ጨምሮ፣ - ለምሳሌ ሊያውቋቸው ከሚችሉ ሰዎች ጋር ማጋራትን ቀለል ለማድረግ ሲባል ከአንዱ አገልግሎት የሚገኘውን የግል መረጃ ከሌሎቹ ጋር ልናጣምረው እንችል ይሆናል። በመረጡት እንደገቡ ስምምነትዎን ካልገለጹልን በቀር የDoubleClick ኩኪ መረጃን በግል ተለይቶ ሊታወቅ ከሚችል መረጃ ጋር አናጣምርም።

በዚህ የግላዊነት መምሪያ ከተቀመጡት ምክንያቶች እና ሁኔታዎች ውጪ መረጃዎን መጠቀም ቢያስፈልገን በቅድሚያ ፈቃደኛ መሆንዎን እንጠይቅዎታለን።

Google የግል መረጃዎችን በመላ ዓለም በሚገኙ በርካታ ሃገሮች በእኛ አገልጋዮች አማካኝነት ያስኬዳል። የግል መረጃዎን ከሚኖሩበት ሃገር ውጪ ባለ አገልጋይ ላይ ልናስኬደው እንችል ይሆናል።

የአሰራር ግልጽነት እና ምርጫዎች

ሰዎች የተለያዩ ስለግላዊነት መብት የሚያሳስቡዋቸው ነገሮች አሉ። መረጃው እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል አውቀው ትርጉም ያለው ምርጫ እንዲያደርጉ፣ ዓላማችን ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ ግልጽ ሆኖ መገኘት ነው። ለምሳሌ፣ የሚከተለውን ማድረግ ይችላሉ፦

  • Google Dashboard በመጠቀም ከእርስዎ የGoogle መለያ ጋር የተሳሰሩ የተወሰኑ አይነት መረጃዎችን ይገምግሙ እና ይቆጣጠሩ።
  • የማስታወቂያ ቅንብሮችን በመጠቀም የትኛዎቹ ምድቦች የእርስዎ ፍላገት ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን የመሳሰሉ በGoogle እና በድር ውስጥ በሙሉ ለእርስዎ ስለሚታዩ ማስታወቂያዎች እርስዎ ምርጫዎችን ይመልከቱ እና ያርትዑ። በተጨማሪም እዚህ ከተወሰኑ የGoogle ማስታወቂያ ስራ አገልግሎቶች መርጠው መውጣት ይችላሉ።
  • የGoogle መገለጫዎ ለተወሰኑ ግለሰቦች እንዴት እንደሚታያቸው ለማየት እና ለማስተካከል የእኛን አርታዒ መጠቀም
  • መረጃን ከማን ጋር እንደሚጋሩ መቆጣጠር
  • ከአብዛኛዎቹ የእኛ አገልግሎቶች ውስጥ መረጃ ማውጣት

ከእኛ አገልግሎቶች ጋር የተጣመሩ ኩኪዎችን ጨምሮ፣ ሁሉንም ኩኪዎች ለማገድ ወይም ኩኪ በእኛ ሲቀናበር እንዲጠቁምዎ አሳሽዎን ማቀናበር ጭምር ይችላሉ። ሆኖም ግን፣ ኩኪዎችዎ እንዲቦዝኑ ከተደረጉ በርካታዎቹ የእኛ አገልግሎቶች በሚገባ ሊሰሩ የማይችሉበት ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፣ የቋንቋ ምርጫዎን ላናስታውስ እንችላለን።

የሚያጋሩት መረጃ

በርካታዎቹ የእኛ አገልግሎቶች መረጃ ከሌሎች ጋር እንዲጋሩ ያስችልዎታል። በይፋ መረጃ ሲያጋሩ፣ በፍለጋ ፕሮግራሞች፣ Googleን ጨምሮ ዋቢ ሊደረግ እንደሚችል ያስታውሱ። አገልግሎቶቻችን በማጋራት እና ይዘትዎን በማስወገድ ረገድ በርካታ አማራጮችን ይሰጥዎታል።

የግል መረጃዎን መድረስ እና ማዘመን

የእኛን አገልግሎቶች በተጠቀሙ ቁጥር ወደ ግል መረጃዎ መዳረሻን ለእርስዎ ለመስጠት እንሞክራለን። መረጃው የተሳሳተ ከሆነ፣ መረጃውን ለህጋዊ የንግድ ስራ ምክንያት ወይም ለሕግ ጉዳይ ከእኛ ጋር ማስቀረት ካልተገደድን በቀር - መረጃውን በፍጥነት ሊያዘምኑ የሚችሉበትን ወይም ሊሰርዙ የሚችሉበትን አማራጭ መንገዶች ለማቅረብ ተግተን እንሰራለን። የግል መረጃዎን ሲያዘምኑ፣ ጥያቄዎን ከማስተናገዳችን በፊት ማንነትዎን እንዲያረጋግጡልን ልንጠይቅዎ እንችላለን።

ያለምንም ምክንያት ተደጋጋሚ የሆኑ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ የቴክኒክ ጥረት የሚጠይቁ (ለምሳሌ፣ አዲስ ስርዓት መገንባት ወይም ያለ አሰራርን ከስር መሰረቱ መቀየር)፣ የሌሎችን ግላዊነት መብት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ፣ ወይም ለፈጸም ከቃም በላይ የሆነ (ለምሳሌ፣ በምትኬ ስርዓቶች ላይ የተቀመጠን መረጃ ለማግኘት የሚቀርቡ ጥያቄዎች) ላንቀበላቸው እንችላለን።

ያልተመጣጠነ ጥረት የሚጠይቅ እስካልሆነ ድረስ፣ የመረጃ መዳረሻ እና ማስተካከያ ስንሰጥ በነጻ ነው የምንሰጠው። አገልግሎቶቻችንን ከድንገተኛ እና ከጎጂ ጥፋቶች ለመጠበቅ ዓላማችን ነው። በዚህ ምክንያት፣ ከአገልግሎቶቻችን መረጃ ከሰረዙ በኋላ፣ ትራፊ ቅጂዎችን ከንቁ አገልጋዮች ወዲያውኑ ላንሰርዝ እና ከምትኬ ስርዓቶቻችን ላናስወግድ እንችላለን።

የምናጋራው መረጃ

ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ካልተከሰተ በስተቀር የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ላሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አናጋራም፦

  • በራስዎ ፈቃድ

    የእርስዎን ፈቃድ ካገኘን የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ካሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር እናጋራለን። ማናቸውንም ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው የግል መረጃዎችን ለማጋራት ተመርጦ የሚገባበት ፈቃድ መስጫን እንጠይቃለን።

  • ከጎራ አስተዳዳሪዎች ጋር

    የእርስዎ የGoogle መለያ በጎራ አስተዳዳሪ የሚተዳደርልዎ ከሆነ (ለምሳሌ፣ ለGoogle መተግበሪያዎች ተጠቃሚዎች) የጎራ አስተዳዳሪዎ እና ለድርጅትዎ የተጠቃሚ ድጋፍ የሚሰጡት መልሶ ሻጮች ለGoogle መለያ መረጃዎ (ኢሜይልዎን እና ሌሎች ውሂቦችን ጨምሮ) መዳረሻ ይኖራቸዋል። የጎራ አስተዳዳሪዎ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፦

    • የድረገጽ አድራሻዎን አጠቃቀም የሚመለከት (ለምሳሌ አዳዲስ ፕሮግራሞች ጭነው አንደሆነ) ስታስቲክስን ማየት።
    • የመለያዎን የይለፍ ቃል መለወጥ።
    • የመለያዎን መዳረሻ ለጊዜው ማገድ ወይም ከናካቴው ማቋረጥ።
    • በመለያዎ እንደ አንድ አካል ሆኖ የተቀመጠን መረጃ መድረስ ወይም መያዝ።
    • ተገቢነት ያለውን ሕግ፣ ደንብ ለማስከበር፣ ሕጋዊ ሂደት ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የመለያዎን መረጃ መቀበል።
    • መረጃ ወይም የግላዊነት ቅንብሮችዎን የመሰረዝ ወይም አርትዖት የማድረግ ችሎታዎን መገደብ።

    ለበለጠ መረጃ የጎራዎን አስተዳዳሪ የግላዊነት መረጃ እባክዎ ይመልከቱ።

  • መረጃዎችን ከGoogle ውጭ ለሆኑ አካላት መስጠት

    በመመሪያዎቻችን መሰረት እና በግላዊነት መምሪያዎቻችን እና ሌሎች ተገቢነት ያላቸው የሚስጢራዊነት እና የደህንነት እርምጃዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ለተባባሪዎቻችን ወይም ሌሎች የታመኑ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን እኛ ለምንፈልገው ዓላማ እንዲያጠናክሩት እንሰጣለን።

  • ለህጋዊ ምክንያቶች

    ከGoogle ውጪ ላሉ ወደ ግል መረጃ በመድረስ፣ በመጠቀም፣ በማስቀመጥ ወይም ለሌሎች በመግለጽ ላይ ጥሩ እምነት ለምንጥልባቸው ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን በሚከተሉት ሁኔታዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እናጋራለን፦

    • ማናቸውንም ተገቢ ህግ፣ ደንብ፣ የህግ አካሄድ ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የሚያስፈልገውን መስፈርት አሟልተው ሲገኙ፤
    • ተገቢነት ያላቸውን የአገልግሎት ውሎች ሊፈጸም የሚችል የሕግ ጥሰትን ጨምሮ ለማስፈጸም፤
    • ለወንጀል ምርመራ፣ ለመከላከል ወይም በሌላ መልኩ የማጭበርበር ስራን ለማጋለጥ፣ ለደህንነት ወይም ቴክኒካዊ ጉዳዮች፤
    • ህግ በሚፈቅደውና በሚጠይቀው መልኩ በGoogle፣ የእኛ ተጠቃሚዎች ወይም የሕዝቡን መብቶች፣ ንብረቶች ወይም ደህንነቶች ላይ ሊደረስ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል።

የተቀላቀለ፣ በግል ተለይቶ ሊታወቅ የማይችል መረጃ በይፋ እና ከአጋሮቻችን ጋር ልንጋራ እንችላለን – እንደ አሳታሚዎች፣ አስተዋዋቂዎች ወይም የተገናኙ ጣቢያዎች የመሳሰሉ። ለምሳሌ፣ ስለአገልግሎቶቻችን አጠቃላይ አጠቃቀም በተመለከተ ያለውን አዝማሚያ ለማሳየት መረጃን በይፋ ልናጋራ እንችላለን።

Google ከሌላ ድርጅት ጋር ቢዋሃድ፣ ቢወረስ ወይም ንብረቱ ቢሸጥ፣ ማናቸውንም የግል መረጃ ምስጢራዊነት ጠብቀን እንቀጥላለን እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተጠቃሚዎችን የግል መረጃቸው ለሌላ ከመተላለፉ በፊት ወይም የሌላ የተለየ ግላዊነት መምሪያ ተገዢ ከመሆኑ በፊት ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው እናደርጋለን።

የመረጃ ደህንነት ጥበቃ

Google እና የእኛን ተጠቃሚዎች ያልተፈቀደለት ሰው አንዳያገኘው ወይም አንዳይለውጠው ይፋ ማድረግ ወይም የያዝነው መረጃ ከመበላሸት ለመጠበቅ ጠንክረን እንሰራለን። በተለይ፦

  • አብዛኛዎቹን አገልግሎቶቻችንን SSL በመጠቀም እንመሰጥራለን።
  • የእርስዎን የGoogle መለያ ሲደርሱበት Google Chrome ውስጥ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ እና አስተማማኝ የአሰሳ ባህሪይ እናቀርብልዎታለን።
  • የእኛን የመረጃ አሰባሰብ፣ አከመቻቸት እና ሂደት አካሄድ ልማዶች፣ አካላዊ የደህንነት እርምጃዎችን ጨምሮ ፈቃድ ካልተሰጠው ወደ ስርዓቶች መድረስን ለመከላከል ስንል እንገመግማለን።
  • የግል መረጃን ለእኛ ሂደት ለማስኬድ ሲሉ የግል መረጃን የሚፈልጉ የGoogle ሰራተኞች፣ ስራ ተቋራጮች እና ወኪሎች እንዲሁም በውል ሚስጢር እንዲጠብቁ ግዴታ ያለባቸውን ወደ ግል መረጃ መዳረሻ እንዳያገኙ እንገድባቸዋለን፣ እናም እነዚህን ግዴታዎችን ሳይወጡ ቢቀሩ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰደባቸው ወይም ስራቸው እንዲቋረጥ ሊደረግ ይችላል።

መተግበሪያ

የግላዊነት መምሪያችን በሁሉም በGoogle Inc. እና ተባባሪዎቹ እንዲሁም በሌሎች ጣቢያዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች (እንደ ማስታወቂያ ማስነገር አገልግሎቶች ያሉ) ተፈጻሚ ሲሆን ይህን የግላዊነት መምሪያ የማያካትቱ የተለዩ የግላዊነት መምሪያዎችን የያዙ አገልግሎቶችን ግን አያካትትም።

የእኛ የግላዊነት መምሪያ በሌሎች ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች እንዲሁም በፍለጋ ውጤቶችዎ ላይ ሊታዩ የሚችሉ ምርቶችን ወይም ጣቢያዎችን፣ የGoogle አገልግሎቶችን የሚያካትቱ፣ ወይም ሌሎች ከእኛ አገልግሎቶች ጋር የተገናኙ ጣቢያዎችን ጨምሮ ተፈጻሚ አይሆንም። የግላዊነት መምሪያችን የእኛን አገልግሎቶች የሚያስተዋውቁ እና ኩኪዎች፣ ፒክስል ስያሜዎችን እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ተዛማጅነት ያላቸውን ለማስተናገድ እና ለማቅረብ የሚጠቀሙ ሌሎች ኩባንያዎች እና ድርጅቶች የመረጃ ልማዶችን አያካትትም።

አፈጻጸም

ከግላዊነት መመሪያችንን ጋር ምን ያክል እንዳከበርን በየጊዜው ግምገማ እናደርጋለን። በተጨማሪም ከበርካታ የራስ መቆጣጠሪያ ማዕቀፎችን እንከተላለን። መደበኛ የጽሑፍ ቅሬታዎች ስንቀበል፣ ክትትል እንዲያደርግ ቅሬታውን ያቀረበውን ሰው እናገኘዋለን። የግል ውሂብን ማስተላለፍ በተመለከተ የቀረበ ማናቸውንም ቅሬታዎች ከተጠቃሚዎቻችን ጋር በቀጥታ መፍታት ሳንችል ስንቀር ተገቢነት ካለቸው ቁጥጥር አድራጊ ባለስልጣኖች፣ የአካባቢ ውሂብ ደህንነት አስጠባቂ ባለስልጣኖች ጋር በጋራ እንሰራለን።

ለውጦች

የግላዊነት መምሪያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለወጥ ይችላል። በግልጽ የተቀመጠ ፈቃድዎን ሳናገኝ በዚህ ግላዊነት መምሪያ ላይ ያሉዎን መብቶች አንቀንስም። ማናቸውንም የግላዊነት መምሪያ ለውጦች በዚህ ገጽ ላይ የምንለጥፍ ሲሆን የተደረጉት ለውጦች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ዓይነት ከሆኑ፣ የበለጠ ዋጋ የሚሰጠው ማሳወቂያ (ለተወሰኑ አገልግሎቶች፣ የግላዊነት መምሪያ ለውጦች ኢሜይል ማሳወቂያን ጨምሮ) እንልካለን። ለግምገማ እንዲረዳዎ የዚህን የግላዊነት መምሪያ የቀድሞ እትሞች በቤተ-ማህደር እናስቀምጣቸዋለን።

የተወሰኑ ምርት ልማዶች

የሚከተሉት ማሳወቂያዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ከተወሰኑ የGoogle ምርቶች እና አገልግሎቶች ጋር ያሉ ልዩ የተወሰኑ የግላዊነት ልማዶችን ያብራራሉ፦

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ