ይሄ በማህደራችን የተመዘገበ የግላዊነት ፖሊሲያችን ስሪት ነው። ያሁኑን ስሪት ወይም ሁሉንም ያለፉት ስሪቶች እይ።

የግላዊነት መምሪያ

የምንሰበስበው መረጃ

የምንሰበስበውን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም

የአሰራር ግልጽነት እና ምርጫዎች

የሚያጋሩት መረጃ

የግል መረጃዎን መድረስ እና ማዘመን

የምናጋራው መረጃ

የመረጃ ደህንነት ጥበቃ

ይህ የግላዊነት መመሪያ ሲተገበር

ከአስተዳዳሪ ባለስልጣናት ጋር ማክበር እና መተባበር

ለውጦች

የተወሰኑ ምርት ልማዶች

ሌሎች ጠቃሚ ከግላዊነት እና ከደህንነት ጋር የሚዛመዱ መሣሪያዎች

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፦ 31 ማርች 2014 (የተመዘገቡ ስሪቶችን አሳይ)

መረጃን ለመፈለግ እና ለማጋራት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘት ወይም አዲስ ይዘት ለመፍጠር – አገልግሎቶቻችንን መጠቀም የምትችልበት የተለያዩ በርካታ መንገዶች አሉ። ከኛ ጋር መረጃ ስታጋራ፣ ለምሳሌ የGoogle መለያ በመፍጠር፣ የበለጠ ተዛማጅነት ያላቸውን የፍለጋ ውጤቶችን እና ማስታወቂያዎች ለማሳየት፣ ከሰዎች ጋር እንድትገናኝ ለማገዝ ወይም ለሌሎች ጋር ማጋራትን ይበልጥ ፈጣን እና ቀላል ለማድረግ– እነዚያን አገልግሎቶች የበለጠ የተሻሉ እንዲሆኑ እናደርጋለን። የኛን አገልግሎቶች እንደመጠቀምህ፣ እንዴት መረጃን እንደምንጠቀም እና ግላዊነትህን መጠበቅ የምትችልባቸው መንገዶችን በተመለከተ ግልጽ እንዲሆንልህ እንፈልጋለን።

የእኛ የግላዊነት መምሪያ የሚከተለውን ያስረዳል፦

  • ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ እና ለምን እንደምንሰበስብ።
  • መረጃውን እንዴት እንደምንጠቀምበት።
  • መረጃን መድረስ እና ማዘመን የሚቻልበትን መንገድ ጨምሮ የምናቀርባቸው አማራጮች።

መምሪያውን በተቻለ መጠን ቀላል እንዲሆን ለማድረግ ሞክረናል፣ ሆኖም ግን እንደ ኩኪስ፣ የአይፒ አድራሻ፣ ፒክስል መለያዎች እና አሳሾች ለመሳሰሉት ቃላት አዲስ ከሆኑ በመጀመሪያ ስለነዚህ ቁልፍ ቃላት ትርጉም ያንብቡ። አዲስ የGoogle ተጠቃሚም ሆኑ የGoogle የረጅም ጊዜ ደንበኛ የእርስዎን የግላዊነት መብት ማስጠበቅ ለGoogle የሚያሳስበው ጉዳይ ነው፣ ስለሆነም እባክዎ ጊዜ ወስደው ስለእኛ አሰራር ለማወቅ ይሞክሩ - ጥያቄ ካለዎትም ይህንን ገጽ ያማክሩ

የምንሰበስበው መረጃ

መረጃ የምንሰበስበው ለተጠቃሚዎቻችን የተሻለ አገልግሎት መስጠት አንድንችል ነው – ይህም ምን አይነት ÌንÌ አንደምትናገር ከማወቅ አንስቶ የትኞቹን ማስታወቂያዎች በጣም ጠቃሚ ሆነው አንዳገኘሃቸው ወይም በድረገጽ ከምታገኛቸው ሰዎች መካከል ላንተ አስፈላጊ የሆኑት የትኞቹ አንደሆኑ ማወቅን የመሳሰለውን ከበድ ያለ መረጃ መሰብሰብን ይጨምራል።

በሁለት መንገድ መረጃ እንሰበስባለን፦

  • በምትሰጠን መረጃ። ለምሳሌ፣ አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን የGoogle አድራሻ አንዲኖርህ የሚጠይቁ ናቸው። የGoogle አድራሻ ስትከፍት ስምህን፣ የኢሜይል አድራሻህን፣ የስልክ ቁጥርህን ወይም የክሬዲት ካርድህን የመሳስሉ የግል መረጃ እንጠይቅሃለን። በምንሰጣቸው የመረጃ ማጋራት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለግህ ምናልባት ስምህን እና ፎቶህን ያካተተ በይፋ የሚታይ Google መገለጫ እንድትፈጥር ልንጠይቅህ እንችላለን።

  • አገልግሎታችንን ስትጠቀም የምናገኘው መረጃ። ስለምትጠቀማቸው አገልግሎቶች እና እንዴት እንደምትጠቀምባቸው፣ ለምሳሌ አንድ የኛን ማስታወቂያ አገልግሎቶች የሚጠቀም ድረ ገጽ ስትጎበኝ ወይም የኛን ማስታወቂያዎች እና አይተህ ምላሽ በምት ሰጥበት ወቅት መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን። ይህ መረጃው የሚከተለውን ያካትታል፦

    • የምትጠቀምበትን ኮምፒዩተር ወይም ፕሮግራም የሚመለከት መረጃ መገልገያ-ተኮር መረጃ (ያንተ ሃርድዌር ሞዴል፣ ኮምፒዩተርህ የሚሰራበትን ስርዓት አይነት (operating system version)፣ መሳሪያ ለይቶ አዋቂዎች፣ እና የስልክ ቁጥርን ጨምሮ የሞባይል ኔትወርክ መረጃዎችን የመሳሰሉ) እንሰበስባለን። Google የኮምፒዩተር መሳሪያ መለያዎችህን ወይም ስልክ ቁጥርህን ከGoogle መለያህ ጋር ሊያዛምድ ይችላል።
    • ምዝግብ ማስታወሻ

      አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ ወይም በGoogle የቀረበ ይዘትን ሲመለከቱ፣በአገልጋይ ምዝግቦች ላይ የተወሰነ መረጃ በራስሰር ልንሰበስብ እና ልናከማች እንችላለን። ይህ የሚከተለውን ሊያካትት ይችላል፦

      • አገልግሎታችንን እንዴት እንደተጠቀሙ ለምሳሌ የፍለጋ ጥያቄዎችዎን ዝርዝሮች።
      • እንደ የስልክ ቁጥርዎ፣ የደወለልዎ አካል ስልክ ቁጥር፣ የማስተላለፊያ ቁጥሮች፣ የጥሪዎች ጊዜ እና ቀን፣ የጥሪው ቆይታ ጊዜ፣ ኤስኤምኤስ ማስተላለፊያ መረጃ እና የጥሪዎች አይነቶች ያሉ የስልክ ምዝግብ መረጃዎች።
      • የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አማራጮች
      • እንደ ብልሽቶች፣ የስርዓት እንቅስቃሴ፣ የሃርድዌር ቅንጅቶች፣ የአሳሽ ዓይነት፣ አሳሽ ቋንቋ፣ የጥያቄዎ ቀን እና ጊዜ እና ማጣቀሻ ዩአርኤል ያለ የመሳሪያ ሁኔታ መረጃ።
      • አሳሽዎን ወይም የGoogle መለያዎን በልዩ ሁኔታ ለይተው ሊያውቁ የሚችሉ ኩኪዎች።
    • የስፍራ መረጃ

      በአካባቢ-የነቃ የGoogle አገልግሎት የሚጠቀሙ ከሆነ እንደ ከሞባይል መሳሪያ የተላኩ እንደ ጂፒኤስ ምልክት ያሉመረጃዎችን ልንሰበስብ እና ወደ መረጃ ስርዓታችን ልናስገባቸው እንችላለን። አካባቢን ለይቶ ለመወሰን ከመሳሪያህ ላይ ለምሳሌ በቅርብ ካለ Wi-Fi መዳረሸ ነጥቦች እና ሕዋስ ማማዎች መረጃ ሊሰጥ የሚችል ውሂብ አነፍናፊ ያሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ልንጠቀም እንችላለን።

    • ልዩ መተግበሪያ ቁጥሮች

      የተወሰኑ አገልግሎቶች ልዩ መተግበሪያ ቁጥር ያካትታሉ። ስለ አጫጫንዎ (ለምሳሌ፣ የክወና ስርዓት ዓይነት እና የመተግበሪያ ስሪት ቁጥር) ያንን አገልግሎትን ሲጭኑ ወይም ሲያራግፉ ወይም አገልግሎት ለምሳሌ ለራስ ሰር ዝማኔዎች በተወሰነ ጊዜ ወቅት ጠብቆ የእኛን አገልጋዮች ሲገናኝ ይህ ቁጥር እና መረጃ ወደ Google ሊላክ ይችላል።

    • አካባቢያዊ ማከማቻ

      መረጃ (የግል መረጃን ጨምሮ) ልንሰበስብ እና እንደየአሳሽ ድር ክምችት (ኤችቲኤምኤል 5ን ጨምሮ) እና የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫዎች ያሉ ስልቶችን በመጠቀም በመሣሪያዎ ላይ ልናከማች እንችላለን።

    • ኩኪዎች እና ማንነታቸው ያልተወቀ ለይቶ አዋቂዎች

      የGoogle አገልግሎት ስትጎበኝ መረጃ ለመሰብሰብ እና ለማከማቸት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን አና ይህ አንድ ወይም ከዛ በላይኩኪዎች ወይም ማንነታቸው ያልታወቁ ለይቶ አዋቂዎች ወደ መሳሪያህ መላክን ሊያካትት ይችላል። በተጨማሪ ለአጋሮቻችን በምናቀርባቸው አገልግሎቶች ጋር ማለትም እንደ ማስታወቂያ ማስነገር አገልግሎቶች ወይም በሌሎች ጣቢያዎች ላይ ብቅ የሚሉ የGoogle ባህሪያት ጋር መልዕክት ስትለዋወጥ ኩኪዎች እና ማንነታቸው ያልታወቁ ለይቶ አዋቂዎችን እንጠቀማለን።

የምንሰበስበውን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም

ከሁሉም አገልግሎቶቻችን የምንሰበስበውን መረጃ ለሌሎች ለማቅረብ፣ ለመጠገን፣ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ እና ለማሻሻል እንዲሁም አዳዲሶችን ለመገንባት፣ እና የGoogle እና የኛን ተጠቃሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ እንጠቀምበታለን። ይህን መረጃ ለአንተ በልክ የተዘጋጀ ይዘት ለማቅረብ – ማለትም እንደ ለፍለጋ ውጤቶች እና ማስታወቂያዎች የበለጠ ተዛማጅነት ያላቸው መረጃዎችን ለመስጠት እንጠቀምበታለን።

ለሁሉም የGoogle መለያ የሚጠይቁ አገልግሎቶች በሙሉ ለGoogle መገለጫ የሰጡትን ስም ልንጠቀምበት እንችላለን። በተጨማሪ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻችን ዙሪያ በወጥነት እንዲወከሉ ከGoogle መለያዎ ጋር የተቆራኙ ሌሎች የዱሮ ስሞችዎን ልንተካቸው እንችል ይሆናል። ሌሎች ተጠቃሚዎች አስቀድመው የእርስዎ ኢሜይል ወይም እርስዎን ለይቶ የሚያሳውቅ ሌላ መረጃ ካላቸው በይፋ የሚታዩትን እንደ ስምዎ እና ፎቶዎ ያሉ የእርስዎን የGoogle መገለጫ መረጃዎች ልናሳያቸው እንችላለን።

ከGoogle አገልግሎት ሲገናኙ፣ እያጋጠዎ ያለውን ማናቸውም ችግር ለመፍታት እንዲረዳ ስላደረጉት ግንኙነት ሪኮርድ ልንይዝ እንችል ይሆናል። የኢሜይል አድራሻዎን ስለአገልግሎቶቻችን መረጃ ለመስጠት ማለትም በቅርቡ እንደሚደረጉ ለውጦች ወይም መሻሻሎች ያሉ መረጃዎችን ለእርስዎ ለመስጠት ልንጠቀምበት እንችላለን።

የተጠቃሚ ተሞክሮህን እና የአገልግሎቶቻችንን አጠቃላይ ጥራት ደረጃ ለማሻሻል እንደ ፒክስል ስያሜዎች ካሉ ኩኪዎችእና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ የቋንቋ ምርጫችህን በማስቀመጥ፣ በምትመረጠው ቋንቋ አገልግሎቶቻችን እንዲታዩህ ለማድረግ እንችላለን። በልክ የተዘጋጁ ማስታወቂያዎችን ስናሳይህ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በስነጾታ ተራክቦ ቅኝት ወይም ጤና በመሳሰሉ ስሜት ሊጎዱ በሚችሉ አደገኛ ምድቦች ጋር ኩኪ ወይም ማንነቱ ያልታወቀ ለይቶ አዋቂን አናቆራኝም።

ከሌሎች Google አገልግሎቶች የሚገኝ መረጃን፣ የግል መረጃን ጨምሮ፣ ለምሳሌ ልታውቃቸው ከምትችል ሰዎች ጋር ማጋራትን ቀለል ለማድረግ ሲባል ከአንዱ አገልግሎት የሚገኘውን የግል መረጃ ከሌሎቹ ጋር ልናጣምረው እንችል ይሆናል። በመርጠህ-ግባ ስምምነትህን ካልገለጽክልን በቀር የDoubleClick ኩኪ መረጃን በግል ተለይቶ ሊታወቅ ከሚችል መረጃ ጋር አናጣምርም።

በዚህ የግላዊነት መምሪያ ከተቀመጡት ምክንያቶች እና ሁኔታዎች ውጪ መረጃዎን መጠቀም ቢያስፈልገን በቅድሚያ ፈቃደኛ መሆንዎን እንጠይቅዎታለን።

Google የግል መረጃዎችን በመላ ዓለም በሚገኙ በርካታ ሃገሮች በእኛ አገልጋዮች አማካኝነት ያስኬዳል። የግል መረጃዎን ከሚኖሩበት ሃገር ውጪ ባለ አገልጋይ ላይ ልናስኬደው እንችል ይሆናል።

የአሰራር ግልጽነት እና ምርጫዎች

ሰዎች የተለያዩ ስለግላዊነት መብት የሚያሳስቡዋቸው ነገሮች አሉ። መረጃው እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል አውቀው ትርጉም ያለው ምርጫ እንዲያደርጉ፣ ዓላማችን ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ ግልጽ ሆኖ መገኘት ነው። ለምሳሌ፣ የሚከተለውን ማድረግ ይችላሉ፦

  • Google Dashboard በመጠቀም ከእርስዎ የGoogle መለያ ጋር የተሳሰሩ የተወሰኑ አይነት መረጃዎችን ይገምግሙ እና ይቆጣጠሩ።
  • የማስታወቂያ ቅንብሮችን በመጠቀም የትኛዎቹ ምድቦች የእርስዎ ፍላገት ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን የመሳሰሉ በGoogle እና በድር ውስጥ በሙሉ ለእርስዎ ስለሚታዩ ማስታወቂያዎች እርስዎ ምርጫዎችን ይመልከቱ እና ያርትዑ። በተጨማሪም እዚህ ከተወሰኑ የGoogle ማስታወቂያ ስራ አገልግሎቶች መርጠው መውጣት ይችላሉ።
  • የGoogle መገለጫዎ ለተወሰኑ ግለሰቦች እንዴት እንደሚታያቸው ለማየት እና ለማስተካከል የእኛን አርታዒ መጠቀም
  • መረጃን ከማን ጋር እንደሚጋሩ መቆጣጠር
  • ከአብዛኛዎቹ የእኛ አገልግሎቶች ውስጥ መረጃ ማውጣት

ከኛ አገልግሎቶች ጋር የተጣመሩ ኩኪዎችን ጨምሮ፣ ሁሉንም ኩኪዎች ለማገድ ወይም ኩኪ በኛ ሲቀናበር እንዲጠቁምህ አሳሽህን ማቀናበር ጭምር ትችላለህ። ሆኖም ግን፣ ኩኪዎችህ እንዲቦዝኑ ከተደረጉ በርካታዎቹ የኛ አገልግሎቶች በሚገባ ሊሰሩ የማይችሉበት ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፣ የቋንቋ ምርጫህን ላናስታውስ እንችላለን።

የሚያጋሩት መረጃ

በርካታዎቹ የኛ አገልግሎቶች መረጃ ከሌሎች ጋር እንድትጋራ ያስችሉሃል። በይፋ መረጃ ስታጋራ፣ በፍለጋ ፕሮግራሞች፣ Googleን ጨምሮ ዋቢ ሊደረግ እንደሚችል አስታውስ። አገልግሎታችን በማጋራት እና በይዘትህን በማስወገድ ረገድ በርካታ አማራጮችን ይሰጡሃል።

የግል መረጃዎን መድረስ እና ማዘመን

አገልግሎቶቻችን በማናቸውም ጊዜ ስትጠቀም፣ ወደ ግል መዳረሻ እንድትችል ማድረግ ዓላማችን ነው። መረጃው የተሳሳተ ከሆነ፣ መረጃውን ለህጋዊ የንግድ ስራ ምክንያት ወይም ለሕግ ጉዳይ ከኛ ጋር ማስቀረት ካልተገደድን በቀር – መረጃውን በፍጥነት ልታዘምን የምትችልበትን ወይም ልትሰርዝ የምትችልበትን አማራጭ መንገዶች ለማቅረብ ተግተን እንሰራለን። የግል መረጃህን ስታዘምን፣ ጥያቄህን ከማስተናገዳችን በፊት ማንነትህን እንድታረጋግጥልን ልንጠይቅህ እንችል ይሆናል።

ያለምንም ምክንያት ተደጋጋሚ የሆኑ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ የቴክኒክ ጥረት የሚጠይቁ (ለምሳሌ፣ አዲስ ስርዓት መገንባት ወይም ያለ አሰራርን ከስር መሰረቱ መቀየር)፣ የሌሎችን ግላዊነት መብት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ፣ ወይም ለፈጸም ከቃም በላይ የሆነ (ለምሳሌ፣ በምትኬ ስርዓቶች ላይ የተቀመጠን መረጃ ለማግኘት የሚቀርቡ ጥያቄዎች) ላንቀበላቸው እንችላለን።

ያልተመጣጠነ ጥረት የሚጠይቅ እስካልሆነ ድረስ፣ የመረጃ መዳረሻ እና ማስተካከያ ስንሰጥ በነጻ ነው የምንሰጠው። አገልግሎቶቻችንን ከድንገተኛ እና ከጎጂ ጥፋቶች ለመጠበቅ ዓላማችን ነው። በዚህ ምክንያት፣ ከአገልግሎቶቻችን መረጃ ከሰረዙ በኋላ፣ ትራፊ ቅጂዎችን ከንቁ አገልጋዮች ወዲያውኑ ላንሰርዝ እና ከምትኬ ስርዓቶቻችን ላናስወግድ እንችላለን።

የምናጋራው መረጃ

ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ካልተከሰተ በስተቀር የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ላሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አናጋራም፦

  • በራስዎ ፈቃድ

    የእርስዎን ፈቃድ ካገኘን የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ካሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር እናጋራለን። ማናቸውንም ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው የግል መረጃዎችን ለማጋራት ተመርጦ የሚገባበት ፈቃድ መስጫን እንጠይቃለን።

  • ከጎራ አስተዳዳሪዎች ጋር

    የእርስዎ የGoogle መለያ በጎራ አስተዳዳሪ የሚተዳደርልዎ ከሆነ (ለምሳሌ፣ ለGoogle መተግበሪያዎች ተጠቃሚዎች) የጎራ አስተዳዳሪዎ እና ለድርጅትዎ የተጠቃሚ ድጋፍ የሚሰጡት መልሶ ሻጮች ለGoogle መለያ መረጃዎ (ኢሜይልዎን እና ሌሎች ውሂቦችን ጨምሮ) መዳረሻ ይኖራቸዋል። የጎራ አስተዳዳሪዎ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፦

    • የድረገጽ አድራሻዎን አጠቃቀም የሚመለከት (ለምሳሌ አዳዲስ ፕሮግራሞች ጭነው አንደሆነ) ስታስቲክስን ማየት።
    • የመለያዎን የይለፍ ቃል መለወጥ።
    • የመለያዎን መዳረሻ ለጊዜው ማገድ ወይም ከናካቴው ማቋረጥ።
    • በመለያዎ እንደ አንድ አካል ሆኖ የተቀመጠን መረጃ መድረስ ወይም መያዝ።
    • ተገቢነት ያለውን ሕግ፣ ደንብ፣ ለማስከበር፣ ሕጋዊ ሂደት ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የመለያህን መረጃ መቀበል።
    • መረጃ ወይም የግላዊነት ቅንብሮችዎን የመሰረዝ ወይም አርትዖት የማድረግ ችሎታዎን መገደብ።

    ለበለጠ መረጃ የጎራዎን አስተዳዳሪ የግላዊነት መረጃ እባክዎ ይመልከቱ።

  • መረጃዎችን ከGoogle ውጭ ለሆኑ አካላት መስጠት

    በመመሪያዎቻችን መሰረት እና በግላዊነት ፖሊሲዎቻችን እና ሌሎች ተገቢነት ያላቸው የሚስጢራዊነት እና የደህንነት እርምጃዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ለተባባሪዎቻችን ወይም ሌሎች የታመኑ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን እኛ ለምንፈልገው ዓላማ እንዲያጠናክሩት እንሰጣለን።

  • ለህጋዊ ምክንያቶች

    ከGoogle ውጪ ላሉ ወደ ግል መረጃ በመድረስ፣ በመጠቀም፣ በማስቀመጥ ወይም ለሌሎች በመግለጽ ላይ ጥሩ እምነት ለምንጥልባቸው ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን በሚከተሉት ሁኔታዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እናጋራለን፦

    • ማናቸውንም ተገቢ ህግ፣ ደንብ፣ የህግ አካሄድ ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የሚያስፈልገውን መስፈርት አሟልተው ሲገኙ፤
    • ተገቢነት ያላቸውን የአገልግሎት ውሎች ሊፈጸም የሚችል የሕግ ጥሰትን ጨምሮ ለማስፈጸም፤
    • ለወንጀል ምርመራ፣ ለመከላከል ወይም በሌላ መልኩ የማጭበርበር ስራን ለማጋለጥ፣ ለደህንነት ወይም ቴክኒካዊ ጉዳዮች፤
    • ህግ በሚፈቅደውና በሚጠይቀው መልኩ በGoogle፣ የእኛ ተጠቃሚዎች ወይም የሕዝቡን መብቶች፣ ንብረቶች ወይም ደህንነቶች ላይ ሊደረስ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል።

እንደ አሳታሚዎች፣ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ወይም የተገናኙ ጣቢያዎች ካሉ አጋሮቻችን ጋር – በጣምራበግል ተለይቶ ሊታወቅ የማይችል መረጃ በይፋ ልናጋራ እንችላለን። ለምሳሌ፣ ስለአገልግሎቶቻችን አጠቃላይ አጠቃቀም በተመለከተ ያለውን አዝማሚያ ለማሳየት መረጃን በይፋ ልናጋራ እንችላለን። ለምሳሌ፣ ስለአገልግሎቶቻችን አጠቃላይ አጠቃቀም በተመለከተ ያሉትን አዝማሚያዎች ለማሳየት መረጃን በይፋ ልናጋራ እንችላለን።

Google ከሌላ ድርጅት ጋር ቢዋሃድ፣ ቢወረስ ወይም ንብረቱ ቢሸጥ፣ ማናቸውንም የግል መረጃ ምስጢራዊነት ጠብቀን እንቀጥላለን እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተጠቃሚዎችን የግል መረጃቸው ለሌላ ከመተላለፉ በፊት ወይም የሌላ የተለየ ግላዊነት መምሪያ ተገዢ ከመሆኑ በፊት ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው እናደርጋለን።

የመረጃ ደህንነት ጥበቃ

Google እና የእኛን ተጠቃሚዎች ያልተፈቀደለት ሰው አንዳያገኘው ወይም አንዳይለውጠው ይፋ ማድረግ ወይም የያዝነው መረጃ ከመበላሸት ለመጠበቅ ጠንክረን እንሰራለን። በተለይ፦

  • አብዛኛዎቹን አገልግሎቶቻችንን SSL በመጠቀም እንመሰጥራለን።
  • የእርስዎን የGoogle መለያ ሲደርሱበት Google Chrome ውስጥ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ እና አስተማማኝ የአሰሳ ባህሪይ እናቀርብልዎታለን።
  • የእኛን የመረጃ አሰባሰብ፣ አከመቻቸት እና ሂደት አካሄድ ልማዶች፣ አካላዊ የደህንነት እርምጃዎችን ጨምሮ ፈቃድ ካልተሰጠው ወደ ስርዓቶች መድረስን ለመከላከል ስንል እንገመግማለን።
  • የግል መረጃን ለእኛ ሂደት ለማስኬድ ሲሉ የግል መረጃን የሚፈልጉ የGoogle ሰራተኞች፣ ስራ ተቋራጮች እና ወኪሎች እንዲሁም በውል ሚስጢር እንዲጠብቁ ግዴታ ያለባቸውን ወደ ግል መረጃ መዳረሻ እንዳያገኙ እንገድባቸዋለን፣ እናም እነዚህን ግዴታዎችን ሳይወጡ ቢቀሩ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰደባቸው ወይም ስራቸው እንዲቋረጥ ሊደረግ ይችላል።

ይህ የግላዊነት መመሪያ ሲተገበር

የግላዊነት መምሪያችን በሁሉም በGoogle Inc. እና ተባባሪዎቹ እንዲሁም በሌሎች ጣቢያዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች (እንደ ማስታወቂያ ማስነገር አገልግሎቶች ያሉ) ተፈጻሚ ሲሆን ይህን የግላዊነት መምሪያ የማያካትቱ የተለዩ የግላዊነት መምሪያዎችን የያዙ አገልግሎቶችን ግን አያካትትም።

የእኛ የግላዊነት መምሪያ በሌሎች ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች እንዲሁም በፍለጋ ውጤቶችዎ ላይ ሊታዩ የሚችሉ ምርቶችን ወይም ጣቢያዎችን፣ የGoogle አገልግሎቶችን የሚያካትቱ፣ ወይም ሌሎች ከእኛ አገልግሎቶች ጋር የተገናኙ ጣቢያዎችን ጨምሮ ተፈጻሚ አይሆንም። የግላዊነት መምሪያችን የእኛን አገልግሎቶች የሚያስተዋውቁ እና ኩኪዎች፣ ፒክስል ስያሜዎችን እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ተዛማጅነት ያላቸውን ለማስተናገድ እና ለማቅረብ የሚጠቀሙ ሌሎች ኩባንያዎች እና ድርጅቶች የመረጃ ልማዶችን አያካትትም።

ከአስተዳዳሪ ባለስልጣናት ጋር ማክበር እና መተባበር

ከግላዊነት መመሪያችንን ጋር ምን ያክል እንዳከበርን በየጊዜው ግምገማ እናደርጋለን። በተጨማሪም ከበርካታ የራስ መቆጣጠሪያ ማዕቀፎችን እንከተላለን። መደበኛ የጽሑፍ ቅሬታዎች ስንቀበል፣ ክትትል እንዲያደርግ ቅሬታውን ያቀረበውን ሰው እናገኘዋለን። የግል ውሂብን ማስተላለፍ በተመለከተ የቀረበ ማናቸውንም ቅሬታዎች ከተጠቃሚዎቻችን ጋር በቀጥታ መፍታት ሳንችል ስንቀር ተገቢነት ካለቸው ቁጥጥር አድራጊ ባለስልጣኖች፣ የአካባቢ ውሂብ ደህንነት አስጠባቂ ባለስልጣኖች ጋር በጋራ እንሰራለን።

ለውጦች

የግላዊነት መምሪያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለወጥ ይችላል። በግልጽ የተቀመጠ ፈቃድዎን ሳናገኝ በዚህ ግላዊነት መምሪያ ላይ ያሉዎን መብቶች አንቀንስም። ማናቸውንም የግላዊነት መምሪያ ለውጦች በዚህ ገጽ ላይ የምንለጥፍ ሲሆን የተደረጉት ለውጦች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ዓይነት ከሆኑ፣ የበለጠ ዋጋ የሚሰጠው ማሳወቂያ (ለተወሰኑ አገልግሎቶች፣ የግላዊነት መምሪያ ለውጦች ኢሜይል ማሳወቂያን ጨምሮ) እንልካለን። ለግምገማ እንዲረዳዎ የዚህን የግላዊነት መምሪያ የቀድሞ እትሞች በቤተ-ማህደር እናስቀምጣቸዋለን።

የተወሰኑ ምርት ልማዶች

የሚከተሉት ማሳወቂያዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ከተወሰኑ የGoogle ምርቶች እና አገልግሎቶች ጋር ያሉ ልዩ የተወሰኑ የግላዊነት ልማዶችን ያብራራሉ፦

ተጨማሪ ጠቃሚ ከግላዊነት እና ከደህንነት ጋር የሚዛመዱ ይዘቶች በGoogle መመሪያዎች እና የመርህ ገጾች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፣ በሚከተሉትም ውስጥም ጨምሮ፦

«የግል መረጃዎ መዳረሻ»

ለምሳሌ፣ በGoogle ዳሽቦርድ አማካኝነት አንዳንድ ከGoogle መለያዎ ጋር የተጎዳኘ ውሂብ በፍጥነትና በቀላሉ መመልከት ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ።

«በጣም ጠቃሚ ሆነው የሚያገኟቸው ማስታወቂያዎች»

ለምሳሌ፣ ስለጓሮ አትክልት ያሉ ድር ጣቢያዎችን እና ጦማሮችን በተደጋጋሚነት የሚጎበኙ ከሆኑ ድሩን ሲያስሱ ከጓሮ አትክልት ጋር የሚዛመዱ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ።

«የማስታወቂያ አገልግሎቶች»

ለምሳሌ፣ ማስታወቂያዎቻችንን የሚያሳዩ ስለጓሮ አትክልት ያሉ ድር ጣቢያዎችን እና ጦማሮችን በተደጋጋሚነት የሚጎበኙ ከሆኑ ድሩን ሲያስሱ ከዚህ ዝንባሌ ጋር የሚዛመዱ ማስታወቂያዎችን ማየት ሊጀምሩ ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ።

«መረጃ መሰብሰብ»

ይሄ እንደ የእርስዎ አጠቃቀም ውሂብ እና ምርጫዎች፣ የGmail መልዕክቶች፣ የG+ መገለጫ፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ የአሰሳ ታሪክ፣ የካርታ ፍለጋዎች፣ ሰነዶች ወይም ሌሎች በGoogle የተስተናገዱ ይዘቶች ያሉ መረጃዎችን ያካትታል። ተጨማሪ ይወቁ።

«የግል መረጃን ጨምሮ ከአንድ አገልግሎት የመጣ የግል መረጃ ከሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ከመጣ የግል መረጃ ጋር ያዋህዳል»

ለምሳሌ፣ ወደ የእርስዎ Google መለያ ገብተው ከሆነና Google ላይ ሲፈልጉ ከይፋዊው ድር የተገኙ የፍለጋ ውጤቶችን ከገጾች፣ ፎቶዎች እና ከጓደኛዎችዎ የGoogle+ ልጥፎች ጋር ማየት ይችላሉ፣ እና እርስዎ የሚያውቋቸው ሰዎች ወይም እርስዎን በGoogle+ ላይ የሚከተሉ ሰዎች የእርስዎን ልጥፎች እና መገለጫ በውጤቶቻቸው ላይ ሊያዩ ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ።

«ከሰዎች ጋር ይገናኙ»

ለምሳሌ፣ እንደ Gmail ባሉ ሌሎች የGoogle ምርቶች ላይ ባለዎት የሰዎች ግንኙነት ላይ የተመሠረቱ ሊያውቋቸው የሚችሏቸው ወይም በGoogle+ ላይ ግንኙነት መፍጠር የሚፈልጓቸው የሰዎች አስተያየት ጥቆማዎችን ማግኘት ይችላሉ፣ እና ከእርስዎ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የእርስዎን መገለጫ እንደ የአስተያየት ጥቆማ ሊያዩት ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ።

«ክሬዲት ካርድ»

በአሁኑ ጊዜ ሲመዘገቡ ክሬዲት ካርድ የማንጠይቅ ሲሆን፣ የGoogle መለያ ለመክፈት የሚችሉበት ዕድሜ ላይ እንዳልደረሱ የሚያመለክት የልደት ቀን ካስገቡ በኋላ መለያዎ የተሰናከለ እንደሆነ ዕድሜዎን በትንሽ የክሬዲት ካርድ ግብይት በማረጋገጥ የዕድሜ መስፈርቶቻችን የሚያሟሉ መሆንዎን የሚያረጋጡበት አንድ መንገድ ነው። ተጨማሪ ይወቁ።

«አዳዲስ ይገንቡ»

ለምሳሌ፣ የGoogle ፊደል ማረሚያ ሶፍትዌር የተገነባው ተጠቃሚዎች የራሳቸውን የፊደል አጻጻፍ ያረሙበት ቀዳሚ ፍለጋዎችን በመተንተን ነው። ተጨማሪ ይወቁ።

«የመሣሪያ ለዪዎች»

የመሣሪያ ለዪዎች አገልግሎቶቻችንን ለመድረስ የትኛውን ልዩ መሣሪያ እየተጠቀሙ እንደሆኑ Google እንዲያውቅ ያስችለዋል፣ ይህም አገልግሎታችንን ለመሣሪያዎ ለማበጀት ወይም ከአገልግሎቶቻችን ጋር የተያያዙ ማናቸውንም የመሣሪያ ችግሮችን ለመተንተን ሊያገለግል ይችላል። ተጨማሪ ይወቁ።

«መሣሪያ-ተኮር መረጃ»

ለምሳሌ፣ ከዴስክቶፕዎ ሆነው Google Playን ሲጎበኙ Google ይህን መረጃ ተጠቅሞ ግዢዎችዎ በየትኛዎቹ መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲሆኑ እንዲወስኑ ሊያግዝዎ ይችላል። ተጨማሪ ይወቁ።

«የተጠቃሚ ተሞክሮዎን ማሻሻል»

ለምሳሌ፣ ኩኪዎች እንዴት ተጠቃሚዎች ከአገልግሎቶቻችን ጋር መስተጋብር እንደሚፈጥሩ እንድንተነትን ያስችሉናል። ተጨማሪ ይወቁ።

ልክ እንደ ሌሎች የቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ኩባንያዎች ሁሉ Google የተጠቃሚ ውሂብ አሳልፎ እንዲሰጥ በመላው ዓለም ካሉ መንግስታት እና ፍርድ ቤቶች በየጊዜው ጥያቄዎች ይድርሱታል። ተጨማሪ ይወቁ።

«የትክክለኛው አካባቢዎ መረጃ ሊሰበሰብ እና ሊሰራበት ይችላል»

ለምሳሌ፣ Google ካርታዎች የአሁኑ አካባቢዎን መሃል ላይ አድርጎ የካርታዎች እይታውን ሊያስተካክል ይችላል። ተጨማሪ ይወቁ።

«በአግባቡ ላይሰራ ይችላል»

ለምሳሌ፣ በአንድ አሳሽ ላይ ብዙ የGoogle ሰነዶችን እንዲከፍቱ የሚያስችልዎ «lbcs» የሚባል ኩኪ እንጠቀማለን። ተጨማሪ ይወቁ።

«ስልክ ቁጥር»

ለምሳሌ፣ አንድ ስልክ ቁጥር እንደ የመልሶ ማግኛ አማራጭ አድርገው ካስገቡ፣ የይለፍ ቃልዎን የረሱ እንደሆነ፣ Google የይለፍ ቃሉን ዳግም እንዲያስጀምሩት የሚያስችልዎ ኮድ የያዘ የጽሑፍ መልዕክት ሊልክልዎ ይችላል። ተጨማሪ ይወቁ።

«Googleን እና ተጠቃሚዎቻችንን መጠበቅ»

ለምሳሌ፣ ፍቃድ ስላልተሰጠው የኢሜይልዎ መዳረስ ካሳሰበዎት፣ በGmail ውስጥ ያለው «የመጨረሻው የመለያ እንቅስቃሴ» እንደ መልዕክትዎን የደረሱ የአይፒ አድራሻዎች፣ ተጓዳኙን አካባቢ እንዲሁም ሰዓት እና ቀን ያሉ በኢሜይልዎ ላይ ስለነበሩ የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎች መረጃ ያሳየዎታል። ተጨማሪ ይወቁ።

«ማጋራት»

ለምሳሌ፣ በGoogle+ አማካኝነት ብዙ የማጋሪያ አማራጮች አሉዎት። ተጨማሪ ይወቁ።

«በበለጠ ፍጥነት እና ቅለት ለሌሎች ማጋራት»

ለምሳሌ፣ የሆነ ሰው አስቀድሞ እውቂያ ሆኖ ከሆነ በአንድ የGmail መልዕክት ውስጥ እሱን ማከል ከፈለጉ Google ስሙን እራሱ ያጠናቅቅልዎታል። ተጨማሪ ይወቁ።

«መስመር ላይ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ሰዎች»

ለምሳሌ፣ በ«ለ»፣ «ካርቦን ቅጂ» ወይም «ስውር ካርቦን ቅጂ» ላይ አንድ አድራሻ ሲተይቡ Gmail በእርስዎ የእውቂያዎች ዝርዝር ውስጥ ያሉ አድራሻዎችን ይጠቁማል። ተጨማሪ ይወቁ።

«ነገሮችን ለሚያውቋቸው ሰዎች ማጋራት ቀላል ለማድረግ»

ለምሳሌ፣ ከሆነ ሰው ጋር በGmail በኩል ከተገናኙና እሱን ወደ አንድ የGoogle ሰነድ ወይም በGoogle ቀን መቁጠሪያ ውስጥ ባለ አንድ ክስተት ላይ ማከል ከፈለጉ ስሙን መተየብ ሲጀምሩ Google እራሱ በማጠናቀቅ ቀላል ያደርገዋል። ተጨማሪ ይወቁ።

«ማስታወቂያዎቻችን ይመልከቱ እና ከእነሱ ጋር መስተጋብር ይፍጠሩ»

ለምሳሌ፣ ማስታወቂያዎችን ለአንድ ገጽ ማቅረባችን ወይም አለማቅረባችን እና ያ ማስታወቂያ በተጠቃሚዎች የመታየት ዕድሉ ምን ያህል እንደሆነ (ለምሳሌ ተጠቃሚዎች ወደ ያላሸበለሉበት የገጹ ክፍል ላይ መሆኑን ሳይሆን) በመደበኝነት ለማስታወቂያ ሰሪዎች ሪፖርት እናደርጋለን። ተጨማሪ ይወቁ።

«የተጠቃለለ በግል የማያስለይ መረጃ በይፋ ልናጋራ እንችላለን»

ብዙ ሰዎች የሆነ ነገር መፈለግ ሲጀምሩ ይሄ በዚያ ጊዜ ላይ ስላሉ ለየት ያሉ አዝማሚያዎች በጣም ጠቃሚ የሆነ መረጃ ሊያቀርብ ይችላል። ተጨማሪ ይወቁ።

«ይበልጥ ተገቢ የሆኑ የፍለጋ ውጤቶች»

ለምሳሌ፣ የጓደኛዎችዎን ፎቶዎች፣ ልጥፎች፣ ወይም ተጨማሪ ነገሮች በማካተት ፍለጋ ለእርስዎ ይበልጥ ተገቢ እና ሳቢ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን።

ተጨማሪ ይወቁ

«ይዘትዎን ማስወገድ»

ለምሳሌ፣ የእርስዎን የድር ታሪክጦማርእርስዎ ባለቤት የሆኑበት የGoogle ጣቢያየYouTube ሰርጥየGoogle+ መገለጫ ወይም መላውን የGoogle መለያ መሰረዝ ይችላሉ።

ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን በየGoogle አዝማሚያዎች እና የYouTube አዝማሚያዎች ላይ ማየት ይችላሉ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ