ለውሂብ ማስተላለፎች ሕጋዊ ማዕቀፎች
ውጤታማ 16 ሴፕቴምበር 2024 | የታቆሩ ስሪቶች
በዓለም ዙሪያ አገልጋዮችን እንጠብቃለን እና እርስዎ ከሚኖሩበት አገር ውጭ ባሉ አገልጋዮችዎ ላይ መረጃዎ ሊሰናዳ ይችላል። አንዳንዶች ይበልጥ ከሌሎቹ ይልቅ ጥበቃ በሚሰጡበት ሁኔታ በተለያዩ አገሮች ውስጥ ያለው የውሂብ ጥበቃ ሕጎች ሊለያዩ ይችላሉ። የእርስዎ መረጃ የት እንደሚስተናገድ ከግምት ሳይገባ በየግላዊነት መመሪያው ውስጥ የተብራሩትን ተመሳሳይ ጥበቃዎች ተፈጻሚ እናደርጋለን። በተጨማሪም እንደ ከታች የተብራሩት ማዕቀፎች ያሉ ከውሂብ ማስተላለፍ ጋር የሚዛመዱ የተወሰኑ ሕጋዊ ማዕቀፎችን እናከብራለን።
የበቂነት ውሳኔዎች
የአውሮፓ ኮሚሽን ከአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ (አኢአ) ውጭ ያሉ የተወሰኑ አገሮች በበቂ ሁኔታ የግል መረጃን እንደሚጠብቁ ወስኗል፣ ይህ ማለት ውሂብ ከአውሮፓ ህብረት (አህ) እና ከኖርዌይ፣ ከሊችተንስታይን እና ከአይስላንድ ወደ እነዚያ አገራት መተላለፍ ይችላል ማለት ነው። ዩናይትድ ኪንግደም እና ስዊዘርላንድ ተመሳሳይ የበቂነት ዜዴዎችን ሥራ ላይ አውለዋል። እኛ በሚከተሉት የበቂነት ዘዴዎች ላይ እንተማመናለን፦
የአውሮፓ ሕብረት-አሜሪካ እና የስዊስ-አሜሪካ የውሂብ ግላዊነት ማዕቀፎች
በእኛ የውሂብ ግላዊነት ማዕቀፍ የዕውቅና ማረጋገጫ ውስጥ እንደተገለጸው በቅደም ተከተል ከአኢአ፣ ስዊዘርላንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም የግል መረጃ አሰባሰብን፣ አጠቃቀምን እና ይዞ ማቆየትን በተመለከተ በአሜሪካ የንግድ ክፍል እንደቀረበው ለአውሮፓ ህብረት-አሜሪካ እና የስዊዝ-አሜሪካ የውሂብ ግላዊነት ማዕቀፎች (ዲፒኤፍ) እና የአውሮፓ ህብረት-አሜሪካ ዲፒኤፍ የዩናይትድ ኪንግደም ቅጥያ ተገዢ ነን። Google LLC (እና በልቅነት ካልተገለሉ በስተቀር በሙሉ ባለቤትነት የያዛቸው የአሜሪካ ተዳዳሪ ድርጅቶች) ከዲፒኤፍ መርሆች ጋር በሕግ እንደሚዋሃድ የዕውቅና ማረጋገጫ ሰጥቷል። Google በእኛ የግላዊነት መመሪያ «የእርስዎን መረጃ ማጋራት» ክፍል ውስጥ በተገለጸው መሰረት ለውጫዊ ማሰናዳት በወደፊት ማስተላለፍ መርህ ስር እኛን በመወከል ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ለሚያጋራው ማንኛውም የግል መረጃዎ ኃላፊነት የሚወስድ ሆኖ ይቀጥላል። ስለ ዲፒኤፍ የበለጠ ለመረዳት እና የGoogle ዕውቅና ማረጋገጫን ለማየት እባክዎ የዲፒኤፍ ድር ጣቢያ የሚለውን ይጎብኙ።
ከእኛ ዲፒኤፍ የዕውቅና ማረጋገጫ ጋር በተገናኘ በእኛ የግላዊነት ተግባሮች ላይ ጥያቄ ካለዎት እንዲያነጋግሩን እናበረታታዎታለን። Google ለአሜሪካ የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን የምርመራ እና የማስፈጸም ስልጣን ተገዢ ነው። እንዲሁም ለእርስዎ አካባቢያዊ የውሂብ ጥበቃ ባለሥልጣን ቅሬታን ዋቢ ማድረግ ይችላሉ እና እኛ ስጋትዎን ለመፍታት ከእነሱ ጋር አብረን እንሠራለን። በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይበዲፒኤፍ መርሆዎች ዓባሪ I ላይ በተገለጸው መሰረት በሌሎች መንገዶች ያልተፈቱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ዲፒኤፍ አስገዳጅነት ያለው ሽምግልና እንዲካሄድ ጥሪ የማድረግ መብትን ያቀርባል።
መደበኛ የውል አንቀጾች
መደበኛ የውል አንቀጾች (ኤስሲሲዎች) ተገቢ የሆነ የውሂብ ጥበቃ መከላከያዎችን በማቅረብ ከአኢአ ወደ ሦስተኛ አገሮች ለሚደረጉ ለውሂብ ዝውውሮች መነሻ ሆነው ሊያገለግሉ የሚችሉ በወገኖች መካከል ያሉ የጽሁፍ ቃልኪዳኖች ናቸው። ኤስሲሲዎች በአውሮፓ ኮሚሽን ጸድቀዋል እና በሚጠቀሙባቸው ወገኖች መሻሻል አይችሉም (በአውሮፓ ኮሚሽን ሥራ ላይ የዋሉትን ኤስሲሲዎች እዚህ፣ እዚህ እና እዚህ ማየት ይችላሉ)። እንደነዚህ ያሉት አንቀጾች ከዩናይትድ ኪንግደም እና ከስዊዘርላንድ ውጭ ላሉ አገሮች ውሂብን ለማስተላለፍ ጸድቀዋል። እኛ አስፈላጊ በሚሆኑበት ቦታ እና በበቂነት ውሳኔ ባልተሸፈኑባቸው አጋጣሚዎች ውስጥ ለውሂብ ዝውውራችን ኤስሲሲዎች ላይ እንደተማመናለን። የኤስሲሲዎች ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ እኛን ማነጋገር ይችላሉ።
እንዲሁም Google Workspace፣ የGoogle ደመና መሰረተ ሥርዓት፣ የGoogle ማስታወቂያዎች እና ሌሎችንም የማስታወቂያዎች እና የመለኪያ ምርቶች ጨምሮ Google ኤስሲሲዎችን ከንግድ አገልግሎቶቹ ደንበኛዎች ጋር በሚደረጉ ውሎች ውስጥ ሊያካትት ይችላል። privacy.google.com/businesses ላይ የበለጠ ይወቁ።