የGoogle አጋሮች እነማን ናቸው?
Google ከንግድ ተቋማት እና ድርጅቶች ጋር በተለያዩ መንገዶች አብሮ ይሠራል። እነዚህን የንግድ ተቋማት እና ድርጅቶች እንደ «አጋሮች» እንጠቅሳቸዋለን። ለምሳሌ 2 ሚሊዮን የGoogle ያልሆኑ የድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከGoogle ጋር አብረው በአጋርነት ይሠራሉ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አጋሮች በGoogle Play ላይ የእነርሱን መተግበሪያዎች ለማተም በአጋርነት ይሠራሉ። ሌሎች አጋሮች Google የእኛን አገልግሎቶች ደህንነት እንዲጠብቅ ያግዛሉ፤ ስለ ደህንነት ስጋቶች የተመለከቱ መረጃዎች የእርስዎ መለያ በሌላ እንደተነጠቀ ሆኖ ካመንን እርስዎን እንድናሳውቅ ያግዙናል (የእርስዎን መለያ ደህንነት ለመጠበቅ እርስዎ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እኛ እርስዎን ማገዝ በምንችልበት ደረጃ ላይ)።
ከአጋሮች ይልቅ እንደ «ውሂብ አስተናጋጆች» ካሉ የታመኑ ንግድ ድርጅቶች ጋር እንደምንሠራ ልብ ይበሉ፤ ይህም ማለት በእኛ መመሪያዎች ላይ በመመርኮዝ የእኛን አገልግሎቶች ለመደገፍ እና በእኛ የግላዊነት መመሪያ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው የምሥጢራዊነት እና የደህንነት እርምጃዎች ተገዢ በመሆን እነርሱ በእኛ ምትክ መረጃን ያስኬዳሉ። የGoogle የግላዊነት መመሪያ እኛ እንዴት የውሂብ አስተናጋጆችን እንደምንጠቀም በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ አለው።
ካልጠየቁን በስተቀር እንደ የእርስዎ ስም ወይም ኢሜይል ያለ እርስዎን በግል ለማስታወቂያ አስነጋሪ አጋሮች የሚያስለይ መረጃን አናጋርም። ለምሳሌ፣ በአቅራቢያ ያለ የአበባ መሸጫ ማስታወቂያ ከተመለከቱና የ«ለመደወል መታ አድርግ» አዝራሩን ከመረጡ ጥሪዎን እናገናኘውና ስልክ ቁጥርዎን ለአበባ መሸጫው ልናጋራው እንችላለን።
ከአጋሮች ጨምሮ Google ስለሚሰበስበው መረጃ በግላዊነት መመሪያ ውስጥ ተጨማሪ ማንበብ ይችላሉ።