የቃላት ፍቺ

ልዩ ለዪዎች

ልዩ ለዪ አሳሽን፣ መተግበሪያን ወይም መሣሪያን ለይቶ ለማወቅ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል የቁምፊዎች ኅብረቁምፊ ነው። የተለያዩ ለዪዎች በዘላቂነታቸው፣ በተጠቃሚዎች ዳግም ሊጀመሩ መቻላቸው፣ እና እንዴት ሊደረስባቸው እንደሚቻል ላይ ይለያያሉ።

ልዩ ለዪዎች ለደህንነት እና ማጭበርበርን ለመያዝ፣ እንደ የእርስዎ የኢሜይል ገቢ መልዕክት ሳጥን ያሉ አገልግሎቶችን ለማሳመር፣ የእርስዎ ምርጫዎችን ለማስታወስ እና ተገቢ ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ ጨምሮ ለተለያዩ ዓላማዎች ሥራ ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ በኩኪዎች ውስጥ የተቀመጡ ልዩ ለዪዎች ጣቢያዎች በእርስዎ አሳሽ ውስጥ በተመራጭ ቋንቋዎ እንዲያሳዩ ያግዛቸዋል። አሳሽዎ ሁሉንም ኩኪዎች እንዳይቀበል ወይም አንድ ኩኪ እየተላከ ሳለ እንዲያመለክት ማዋቀር ይችላሉ። እንዴት Google ኩኪዎችን እንደሚጠቀም የበለጠ ይረዱ።

በሌሎች የመሣሪያ ስርዓቶች ላይ ከአሳሾች በተጨማሪ የተወሰነ መሣሪያ ወይም በዚያ መሣሪያ ላይ ያለን መተግበሪያን ለይቶ ለማወቅ ልዩ ለዪዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለምሳሌ፣ እንደ የማስታወቂያ መታወቂያ ያለ ልዩ ለዪ በAndroid መሣሪያዎች ላይ ተዛማጅ ማስታወቂያን ለማቅረብ በእርስዎ የመሣሪያ ቅንብሮች ውስጥ ሊቀናበር ይችላል። እንዲሁም ልዩ ለዪዎች በአምራቹ ለምሳሌ እንደ የተንቀሳቃሽ ስልክ ኢኤምኢአይ ቁጥር ያለ (አንዳንድ ጊዜ ሁለንተናዊ ልዩ መታወቂያ ወይም ዩዩአይዲ በመባል የሚታወቅ) ለአንድ መሣሪያ በውስጡ ሊካተት ይችላል። ለምሳሌ፣ የአንድ መሣሪያ ልዩ ለዪ አገልግሎታችን ለመሣሪያዎ ለማበጀት ወይም ከአገልግሎቶቻችን ጋር የተገናኙ የመሣሪያ ችግሮችን ለመተንተን ልዩ ለዪዎች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

መሣሪያ

መሣሪያ ማለት የGoogle አገልግሎቶችን ለመድረስ ሥራ ላይ ሊውል የሚችል ኮምፒውተር ነው። ለምሳሌ፣ የዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ጡባዊዎች፣ ዘመናዊ ድምጽ ማጉያዎች እና ዘመናዊ ስልኮች በሙሉ እንደ መሣሪያዎች ይቆጠራሉ።

ምስጢራዊ የግል መረጃ

ይሄ ከምሥጢራዊ የሕክምና እውነታዎች፣ የዘር ወይም የጎሣ ምንጮች፣ ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ እምነቶች ወይም ጾታዊ ተፈጥሮዎች ጋር የሚያያዝ ለየት ያለ የግል መረጃ ምድብ ነው።

ስልተ-ቀመር

ችግር-ፈቺ ክወናዎችን ማከናውን ላይ አንድ ኮምፒውተር የሚከተላቸው ሂደት ወይም የደንቦች ስብስብ።

በግል የማይለይ መረጃ

ይህ መረጃ ስለተጠቃሚዎች የተመዘገበ መረጃ ነው፣ እናም ካሁን በኋላ በግል የሚለይ ተጠቃሚ አያንጸባርቅም ወይም አይጠቅስም።

አይ. ፒ. አድራሻ

ከበይነመረቡ ጋር የተገናኘ እያንዳንዱ መሳሪያ የበይነመረብ ፕሮቶኮል (አይ ፒ) አድራሻ ተብሎ የሚታወቅ ቁጥር ተብሎ ይመደባል። እነዚህ ቁጥሮች አብዛኛውን ጊዜ በጂኦግራፊያዊ ብሎኮች ውስጥ ይመደባሉ። ብዙውን ጊዜ አንድ መሣሪያ ከበይነመረቡ ጋር የሚገናኝበትን ቦታ ለመለየት የአይ ፒ አድራሻን መጠቀም ይቻላል። የአካባቢ መረጃን እንዴት እንደምንጠቀም የበለጠ ይወቁ።

ኩኪዎች

ኩኪ ማለት አንድ ድር ጣቢያ ሲጎበኙ ወደ ኮምፒውተርዎ የሚላክ የቁምፊዎች መደዳ የያዘ ትንሽ ፋይል ነው። ጣቢያውን እንደገና ሲጎበኙት ኩኪው ያንን ጣቢያ አሳሽዎ እንዲያውቀው ያስችለዋል። ኩኪዎች የተጠቃሚ ምርጫዎችና ሌላ መረጃ ሊያከማቹ ይችላሉ። አሳሽዎ ሁሉንም ኩኪዎች እንዳይቀበል ወይም አንድ ኩኪ እየተላከ ሳለ እንዲያመለክት ማዋቀር ይችላሉ። ይሁንና አንዳንድ የድር ጣቢያ ባህርያት ያለ ኩኪዎች በአግባቡ ላይሠሩ ይችላሉ። እርስዎ የአጋሮቻችን ጣቢያዎች ወይም መተግበሪያዎች በሚጠቀሙበት ጊዜ እንዴት ኩኪዎችን እንደሚጠቀም እና Google ኩኪዎችን ጨምሮ ውሂብን እንዴት እንደሚጠቀም ተጨማሪ ይረዱ።

የላኪ ዩአርኤል

የጠቃሽ ዩአርኤል (ዩኒፎርም ሪሶርስ ሎኬተር) በአንድ ድር አሳሽ ወደ መድረሻ ድረ-ገጽ የሚተላለፍ መረጃ ነው፣ በተለይ ወደዚያ ገጽ የሚወስድ አገናኝ ጠቅ ሲያደርጉ። የጠቃሹ ዩአርኤል አሳሹ የጎበኘው የመጨረሻው ድረ-ገጽ ዩአርኤል ይዟል።

የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫ

የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫ በአንድ መሣሪያ ላይ ያለ የውሂብ ክምችት ነው። ለምሳሌ፣ አንድ የድር መተግበሪያ የበይነመረብ ግንኙነት ሳይኖር ማሄድ እና ፈጣን የይዘት መጫንን በማንቃት የመተግበሪያውን አፈጻጸም ማሻሽል ይችላል።

የሽያጭ ተባባሪ አካላት

አጋር ማለት በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ የሸማች አገልግሎቶች የሚሰጡትን Google Ireland Limited፣ Google Commerce Ltd፣ Google Payment Corp እና Google Dialer Inc ኩባንያዎችን ጨምሮ የGoogle የኩባንያዎች ቡድን አካል የሆነ ሕጋዊ አካል ነው.። በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ የንግድ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ኩባንያዎችን በተመለከተ የበለጠ ይረዱ።

የአሳሽ ድር ማከማቻ

የአሳሽ ድር ማከማቻ ድር ጣቢያዎች ውሂብ በአንድ መሣሪያ ላይ ባለ አሳሽ ላይ እንዲያከማቹ ያግዛል። በ«አካባቢያዊ ማከማቻ» ሁነታ ላይ ሥራ ላይ ሲውል ውሂብ በተለያዩ ክፍለ-ጊዜዎች ላይ እንዲከማች ያስችላል። ይህ አሳሽ ተዘግቶ ዳግም ከተከፈተ በኋላ እንኳ ውሂብን ሰርስሮ ማውጣት የሚቻል ያደርገዋል። ኤችቲኤምኤል 5 አንድ የድር ማከማቸትን የሚያመቻች ቴክኖሎጂ ነው።

የአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች

አገልጋዮቻችን ልክ እንደአብዛኛዎቹ ድር ጣቢያዎች ጣቢያዎቻችን ሲጎበኙ ያደረጓቸው የጠየቅዋቸው ገጾች በራስ-ሰር ይዘግባሉ። እነዚህ «የአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች» በተለይ የጠየቅዋቸው ድሮች፣ የአይ.ፒ. አድራሻ፣ የአሳሽ አይነት፣ የአሳሽ ቋንቋ፣ የጥያቄህ ቀንና ጊዜ እና አሳሽዎን በተለየ ሁኔታ ሊለይ የሚችል አንድ ወይም ተጨማሪ ኩኪስ ያካትታሉ።

«መኪናዎች» ለሚል የተለመደ የምዝግብ ግቤት ይህን ይመስላል፦

123.45.67.89 - 25/Mar/2003 10:15:32 -
http://www.google.com/search?q=cars -
Chrome 112; OS X 10.15.7 -
740674ce2123e969
  • 123.45.67.89 ተጠቃሚው በበይነመርብ አገልግሎት አቅራቢው የተመደበለት የአይፒ አድራሻ ነው፤ በተጠቃሚው አገልግሎት የሚወሰን ሆኖ ተጠቃሚው ከበይነመረቡ ጋር በተገናኘ ቁጥር በአገልግሎት አቅራቢው የተለየ አድራሻ ሊሰጠው ይችላል።
  • 25/Mar/2003 10:15:32 የመጠይቁ ቀን እና ሰዓት ነው።
  • http://www.google.com/search?q=cars የፍለጋ መጠይቁን ጨምሮ የተጠየቀው ዩአርኤል ነው።
  • Chrome 112; OS X 10.15.7 ሥራ ላይ የዋሉት አሳሽና ሥርዓተ ክወና ነው።
  • 740674ce2123a969 ለዚሁ ኮምፒውተር በGoogle ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኝ የተመደበለት ልዩ የኩኪ መታወቂያ ነው። (ኩኪዎች በተጠቃሚዎች ሊሰረዙ ይችላሉ። ተጠቃሚው Googleን ከጎበኘበት የመጨረሻ ጊዜ ኩኪውን ከኮምፒውተሩ ከሰረዙት ተጠቃሚው በሚቀጥለው ጊዜ Googleን ከዚያው ኮምፒውተር ሲጎበኙ ለተጠቃሚው የሚመደብ ልዩ የኩኪ መታወቂያ ይሆናል)።

የግል መረጃ

ይህ እርስዎን በግል የሚለይ እንደ የእርስዎ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ ወይም የክፍያ መረጃ፣ ወይም ሌላ እንደ ከGoogle መለያዎ ጋር የምናጎዳኘው መረጃ ያሉ Google በምክንያታዊነት እንደዚህ ካለ መረጃ ጋር ሊያገናኝ የሚችል ውሂብ ያለ ለእኛ የሚያቀርቡት መረጃ ነው።

የፒክሰል መለያ

የፒክሴል መለያ እንደ የድር ጣቢያዎች ዕይታ ወይም ኢሜይል ሲከፈት ያለ የተወሰነ እንቅስቃሴን ለመከታተል ዓላማ በድር ጣቢያ ወይም በኢሜይል አካል ውስጥ የሚቀመጥ የቴክኖሎጂ ዓይነት ነው። የፒክሴል መለያዎች አብዛኛውን ጊዜ ከኩኪዎች ጋር በጣምራነት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

የGoogle መለያ

Google መለያ በመመዝገብና አንዳንድ የግል መረጃ (በተለይ የእርስዎ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ እና አንድ የይለፍ ቃል) ለእኛ በመስጠት አንዳንድ አገልግሎቶቻችንን ሊደርሱባቸው ይችላሉ። ይሄ የመለያ መረጃ የGoogle አገልግሎቶች ሲደርሱባቸው እርስዎን ለማረጋገጥና መለያዎን በሌሎች ከሚደረጉ ያልተፈቀደ መድረስ ለመጠበቅ ስራ ላይ ይውላል። በማንኛውም ጊዜ በእርስዎ የGoogle መለያ ቅንብሮች በኩል የእርስዎን መለያ ማርትዕ ወይም መሰረዝ ይችላሉ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ