ማስታወቂያዎች

ማስታወቂያ Google እና እርስዎ የሚጠቀሟቸውን አብዛኛዎቹ ድር ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች ነጻ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል። ማስታወቂያዎች በተቻለ መጠን አደጋ የሌለባቸው፣ የማይረብሹ እና ተገቢ እንዲሆኑ ተግተን እንሠራለን። ለምሳሌ፣ በGoogle ላይ ብቅ-ባይ ማስታወቂያዎችን አያዩም፣ እና በየዓመቱ መምሪያዎቻችንን የሚጥሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአታሚዎች እና የማስታወቂያ ሰሪዎች መለያዎችን እናቋርጣለን – ተንኮል-አዘል ዌር የያዙ ማስታወቂያዎች፣ የተጭበረበሩ ምርቶች ማስታወቂያዎች ወይም የግል መረጃዎን አላግባብ ለመጠቀም የሚሞክሩትንም ጨምሮ።

የGoogle የማስታወቂያ አገልግሎቶች በChrome እና Android ላይ በግላዊነት Sandbox ተነሳሽነት በኩል በመስመር ላይ ለሰዎች ግላዊነት በተሻለ ሁኔታ ጥበቃ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች የዲጂታል ማስታወቂያ አቅርቦት እና ልኬት የሚደግፉባቸውን አዳዲስ መንገዶች እየሞከሩ ነው። በChrome እና Android ውስጥ አግባብነት ያላቸው የግላዊነት Sandbox ቅንብሮችን ያነቁ ተጠቃሚዎች በአሳሻቸው ወይም ተንቀሳቃሽ መሣሪያቸው ላይ በተቀመጡ ርዕሶች ወይም ጥበቃ የሚደረግለት ታዳሚ ውሂብ መሠረት አግባብነት ያላቸው ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። እንዲሁም የGoogle የማስታወቂያ አገልግሎቶች በአሳሻቸው እና ተንቀሳቃሽ መሣሪያቸው ላይ የተቀመጠ የመገለጫ ባህሪን ሪፖርት የማድረግ ውሂብን በመጠቀም የማስታወቂያ አፈጻጸምን ሊለኩ ይችላሉ። በግላዊነት Sandbox ላይ ተጨማሪ መረጃ

Google እንዴት ኩኪዎችን በማስታወቂያ ላይ እንደሚጠቀምባቸው

ኩኪዎች ማስታወቂያ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ያግዛሉ። ኩኪዎች ባይኖሩ ኖሮ አንድ ማስታወቂያ ሰሪ ታዳሚዎቹን ለማግኘት ወይም ደግሞ ስንት ማስታወቂያዎች እንደታዩና ስንት ጠቅታዎች እንደተቀበሉ ለማወቅ ይበልጥ ይቸገሩ ነበር።

እንደ የዜና ጣቢያዎ እና ጦማሮች ያሉ ብዙ ድር ጣቢያዎች ማስታወቂያዎች ለጎብኚዎቻቸው ለማሳየት ከGoogle ጋር ባልደረባነት ይፈጥራሉ። ከባልደረቦቻችን ጋር በመስራት ኩኪዎች እንደ ተመሳሳዩን ማስታወቂያ ደጋግሞ እንዳያዩ ማቆም፣ ማጭበርበሪያ አግኝተን ጠቅ እንዳይደረግ ማቆም እና ይበልጥ ተገቢ ሊሆኑ የሚችሉትን ማስታወቂያዎች (እንደ በጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎች ያሉ) እንድናሳይ ልንጠቀምባቸው እንችላለን።

በእኛ ምዝግብ ማስታወሻ ውስጥ የምናቀርባቸውን ማስታወቂያዎች ምዝግብ እናከማቻለን። እነዚህ የአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች በተለይ የጠየቋቸውን ድሮች፣ የአይፒ አድራሻ፣ የአሳሽ አይነት፣ የአሳሽ ቋንቋ፣ የጥያቄዎ ቀንና ጊዜ እና አሳሽዎን በተለየ ሁኔታ ሊለይ የሚችል አንድ ወይም ተጨማሪ ኩኪስ ያካትታሉ። ይህንን ውሂብ የምናከማቸው ለበርካታ ምክንያቶች ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ በጣም ዋናዎቹ አገልግሎታችንን ማሻሻል እና የስርዓቶቻችንን ደህንነት መጠበቅ ናቸው። የአይፒ አድራሻውን (ከዘጠኝ ወራት በኋላ) ክፍል እና የኩኪ መረጃ (ከ18 ወራት በኋላ) በማስወገድ ይህንን የምዝግብ ማስታወሻ ውሂብ ስም እንሰውራለን።

የማስታወቂያ ኩኪዎቻችን

ባልደረባዎቻችን ማስታወቂያዎቻቸውን እና ድር ጣቢያዎቻቸውን እንዲያቀናብሩ ለማገዝ AdSense፣ AdWords፣ Google ትንታኔ እና የተለያዩ በDoubleClick ስም የሚሰሩ አገልግሎቶችን ጨምሮ ብዙ አገልግሎቶችን እናቀርባለን። በGoogle አገልግሎቶችም ሆነ በሌሎች ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ ከእነዚህ ምርቶች ውስጥ አንዱን የሚጠቀም ገጽ ሲጎበኙ ወይም ማስታወቂያ ሲመለከቱ የተለያዩ ኩኪዎች ወደ አሳሽዎ ሊላኩ ይችላሉ።

እነዚህ ከgoogle.com፣ ከdoubleclick.net፣ ከgooglesyndication.com ወይም ከgoogleadservices.com ጨምሮ ከጥቂት የተለያዩ ጎራዎች ወይም ከእኛ አጋሮች ጣቢያዎች ሊቀናበሩ ይችላሉ። አንዳንድ የማስታወቂያ ምርቶቻችን ባልደረባዎቻችን ሌሎች አገልግሎቶች ከእኛው ጋር አጣምረው (እንደ የማስታወቂያ መለኪያ እና ሪፖርት አገልግሎት ያለ) እንዲጠቀሙባቸው ያስችሏቸዋል፣ እና እነዚህ አገልግሎቶች የራሳቸውን ኩኪዎች ለአሳሽዎ ሊልኩ ይችላሉ። እነዚህ ኩኪዎች ከጎራዎቻቸው ነው የሚቀናበሩት።

በGoogle ጥቅም ላይ ስለሚውሉ የኩኪ አይነቶች እና ስለባልደረባዎቻችን ተጨማሪ ዝርዝሮች፣ እና እንዴት እንደምንጠቀምባቸው ይመልከቱ።

የማስታወቂያ ኩኪዎችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ

የሚያዩዋቸው የGoogle ማስታወቂያዎች ለማስተዳደር እና ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለማጥፋት የማስታወቂያ ቅንብሮችን መጠቀም ይችላሉ። ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ቢያጠፉም እንደ ከአይፒ አድራሻዎ የተገኙ አጠቃላይ አካባቢዎ፣ ከአሳሽዎ ዓይነት እና ከፍለጋ ቃላትዎ በመሳሰሉት ምክንያቶች ላይ ተመስርተው ማስታወቂያዎችን ማየት ይችላሉ።

እንዲሁም ለመስመር ላይ ማስታወቂያ የሚሰሩባቸው የብዙ ኩባኒያዎች ኩኪዎችን አሜሪካ ላይ በተመሠረተው aboutads.info ምርጫዎች ገጽ ወይም በአውሮፓ ህብረት ላይ የተመሠረተው የመስመር ላይ ምርጫዎችዎ ላይ ማቀናበር ይችላሉ።

በመጨረሻም ኩኪዎችን በድር አሳሽዎ ላይ ማቀናበር ይችላሉ።

በማስታወቂያ ላይ የሚያገልግሉ ሌሎች ቴክኖሎጂዎች

የGoogle ማስታወቂያ ስርዓቶች እንደ የበይነተገናኝ ማስታወቂያ ቅርጸቶች ማሳየት ላሉ ተግባራት Flash እና ኤች ቲ ኤም ኤል 5ን ጨምሮ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ አጠቃላይ አካባቢዎን ለማወቅ የአይ ፒ አድራሻውን ልንጠቀም እንችላለን። እንዲሁም እንደ የመሣሪያዎ ሞዴል፣ የአሳሽ አይነት፣ በመሣሪያዎ ውስጥ እንደ የፍጥነት መለኪያ መሣሪያዎች ያሉ አነቃቂ መለኪያ መሣሪያዎች ባሉ መረጃዎች ላይ ተመስርተን ማስታወቂያ ልንመርጥም እንችላለን።

አካባቢ

የGoogle የማስታወቂያ ምርቶች ከተለያዩ ምንጮች ስለአካባቢዎ መረጃ ሊቀበሉ ወይም ሊያውቁ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ አጠቃላይ አካባቢዎን ለማወቅ የአይፒ አድራሻዎን ልንጠቀም እንችላለን፤ ትክክለኛውን አካባቢዎ ከተንቀሳቃሽ ስልክዎ ልንቀበል እንችላለን፤ አካባቢዎን ከፍለጋ መጠይቆችዎ ልንገምት እንችላለን፣ እና እርስዎ የሚጠቀሙባቸው ድር ጣቢያዎች ወይም መተግበሪያዎች የአካባቢዎን መረጃ ለእኛ ሊልኩ ይችላሉ። Google የስነ-ሕዝብ መረጃን ለማወቅ፣ እርስዎ የሚያዩዋቸውን የማስታወቂያዎች ተገቢነት ለማሻሻል፣ የማስታወቂያ ሥራ አፈጻጸምን ለመለካት እና የተዋሃደ ስታቲስቲክስን ለማስታወቂያ ሰሪዎች ሪፖርት ለማድረግ የአካባቢ መረጃን በማስታወቂያ ምርቶቹ ውስጥ ይጠቀማል።

የሞባይል መተግበሪያዎች የማስታወቂያ ለዪዎች

የኩኪ ቴክኖሎጂ ላይገኝባቸው በሚችሉ አገልግሎቶች ውስጥ (ለምሳሌ፦ በሞባይል መተግበሪያዎች ውስጥ) ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ ከኩኪዎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ተግባራትን የሚያከናውኑ ቴክኖሎጂዎችን ልንጠቀም እንችላለን። ማስታወቂያዎችን በእርስዎ ሞባይል መተግበሪያዎች እና ሞባይል አሳሽ ላይ ማስታወቂያዎችን ለማስተባበር ሲባል አንዳንድ ጊዜ Google በተመሳሳዩ መሣሪያ ላይ የማስታወቂያ ሥራ ኩኪን በሞባይል መተግበሪያዎች ላይ ጥቅም ላይ ከዋለው ለይቶ ማወቂያ ጋር ያገናኛል። ይህ ለምሳሌ እርስዎ በሞባይል አሳሽዎ ላይ ድረ-ገጽን የሚያስጀምር በመተግበሪያ ውስጥ ያለን ማስታወቂያ በሚመለከቱበት ጊዜ ሊያጋጥም ይችላል። ይህ እንዲሁም ለማስታወቂያ ሰሪዎች ስለማስታወቂያ ዘመቻዎቻቸው ስኬታማነት በተመለከተ እኛ የምንሰጣቸውን ሪፖርቶች እንድናሻሽል ያግዘናል።

በመሣሪያዎ ላይ የሚያዩዋቸው ማስታወቂያዎች በማስታወቂያ መታወቂያው ላይ ተመስርተው ግላዊነት የተላበሱ ሊሆኑ ይችላሉ። በAndroid መሳሪያዎች ላይ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

  • የአሁኑን መታወቂያ በአዲስ የሚተካውን የመሣሪያዎን የማስታወቂያ መታወቂያ ዳግም ያስጀምሩት። መተግበሪያዎች አሁንም ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ሊያሳዩዎት ይችላሉ፣ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ ለእርስዎ አግባብነት ያላቸው ወይም አስደሳች ላይሆኑ ይችላሉ።
  • የማስታወቂያ መታወቂያውን የሚሰርዘው እና አዲስ የማይመድበውን የመሣሪያዎን የማስታወቂያ መታወቂያ ይሰርዙ። መተግበሪያዎች አሁንም ማስታወቂያዎችን ሊያሳዩዎት ይችላሉ፣ ነገር ግን ለእርስዎ አግባብነት ያላቸው ወይም አስደሳች ላይሆኑ ይችላሉ። በዚህ የማስታወቂያ መታወቂያ ላይ ተመስርተው ማስታወቂያዎችን አያዩም፣ ነገር ግን አሁንም ማስታወቂያዎችን እንደ ለመተግበሪያዎች ያጋሩት መረጃ ባሉ ሌሎች ምክንያቶች ላይ በመመስረት ማየት ይችላሉ።

በAndroid መሳሪያዎ ላይ ባለው የማስታወቂያ መታወቂያ ላይ ለውጦችን ለማድረግ ከታች ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።

Android

የመሣሪያዎን የማስታወቂያ መታወቂያ ዳግም ያስጀምሩ

የመሣሪያዎን የማስታወቂያ መታወቂያ ዳግም ለማስጀመር፦

  1. በAndroid መሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች ይሂዱ።
  2. ግላዊነት > ማስታወቂያዎችን መታ ያድርጉ።
  3. የማስታወቂያ መታወቂያን ዳግም አስጀምር የሚለውን መታ ያድርጉ እና ለውጦችዎን ያረጋግጡ።
የመሳሪያዎን የማስታወቂያ መታወቂያ ይሰርዙ

የመሳሪያዎን የማስታወቂያ መታወቂያ ለመሰረዝ፦

  1. በAndroid መሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች ይሂዱ።
  2. ግላዊነት > ማስታወቂያዎችን መታ ያድርጉ።
  3. የማስታወቂያ መታወቂያ ሰርዝ የሚለውን መታ ያድርጉ እና ለውጦችዎን ያረጋግጡ።

የማስታወቂያ መታወቂያዎ ዳግም ይጀመራል ወይም ይሰረዛል፣ ነገር ግን መተግበሪያዎች ሌሎች የለዪዎች ዓይነቶችን በመጠቀም የራሳቸው ቅንብሮች ሊኖራቸው ይችላል፣ ይህም በሚያዩዋቸው የማስታወቂያ ዓይነቶች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

በአንዳንድ የቆዩ የAndroid ስሪቶች ላይ

የAndroid መሳሪያዎ ስሪት 4.4 ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ፦

  1. ቅንብሮችን ይክፈቱ
  2. ግላዊነት > የላቀ > ማስታወቂያዎችን መታ ያድርጉ።
  3. ከማስታወቂያዎችን ግላዊነት ማላበስ መርጠው መውጣትን ያብሩ እና ለውጦችዎን ያረጋግጡ።

iOS

iOS ያላቸው መሣሪያዎች የApple’s Advertising Identifierን ይጠቀማሉ። ይህን ለይቶ አዋቂ መጠቀምን በተመለከተ እርስዎ ስላሉዎት ምርጫዎች የበለጠ ለመረዳት በእርስዎ መሣሪያ ላይ የቅንብሮች መተግበሪያውን ይጎብኙ።

የተገናኘ ቲቪ/በላያቸው ላይ

ለተገናኘ ቲቪ የማስታወቂያ ለዪዎች

የተገናኙ ቲቪዎች የኩኪ ቴክኖሎጂ የማይገኙበት ሌላ አካባቢ ነው፣ እና በምትኩ፣ Google ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ በማስታወቂያ ላይ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በተዘጋጁ የመሣሪያ ለዩዎች ላይ ይተማመናል። ብዙ የተገናኙ የቲቪ መሳሪያዎች ከተንቀሳቃሽ መሳሪያ ለዪዎች ጋር በተግባር ተመሳሳይ የሆነ የማስታወቂያ ለዪን ይደግፋሉ። እነዚህ ለዪዎች የተገነቡት ተጠቃሚዎች እነሱን ዳግም እንዲያስጀምሩ ወይም ግላዊነት ከተላበሰ ማስታወቂያ ሙሉ ለሙሉ መርጠው እንዲወጡ አማራጭ ለመስጠት ነው።

የሚከተሉት የ«ማስታወቂያዎች» ቅንብሮች በሚከተለው ወጥ በሆነ ቋንቋ በቲቪዎች ላይ ይገኛሉ፦

  • የማስታወቂያ መታወቂያን ዳግም ያስጀምሩ
  • የማስታወቂያ መታወቂያ ይሰርዙ
  • ከማስታወቂያዎችን ግላዊነት ማላበስ መርጠው ይውጡ (ማብራት ወይም ማጥፋት)
  • በGoogle ማስታወቂያዎች (ወደ ስለ የGoogle ማስታወቂያን ግላዊነት ማላበስ የሚወስዱ አገናኞች)
  • የእርስዎ የማስታወቂያ መታወቂያ (ረጅም ሕብረቁምፊ)

እነዚህ የማስታወቂያ ቅንብሮች በGoogle ቲቪ እና በAndroid TV ላይ በቅደም ተከተል በሚከተሉት መንገዶች ይገኛሉ።

Google ቲቪ

ወጥ የሆነ የማስታወቂያዎች ዱካ፦

  1. ቅንብሮች
  2. ግላዊነት
  3. ማስታወቂያዎች

Android TV

የማስታወቂያ ቅንብሮች በቲቪ አምራቹ/ሞዴሉ ላይ በመመስረት ለAndroid TV ከሁለት አጠቃላይ ዱካዎች በአንዱ ይታያሉ። በAndroid TV ላይ አጋሮች የቅንብሮችን ዱካ የማላመድ ነፃነት አላቸው። ብጁ የቲቪ ልምዳቸውን በተሻለ መንገድ ለማስማማት የትኛውን መንገድ እንደሚጠቀሙ የአጋሩ ፈንታ ነው፣ ነገር ግን ከታች ያሉት ወደ የማስታወቂያ ቅንብሮች የሚወስዱ የተለመዱ ዱካዎች አሉ።

ዱካ ሀ፦

  1. ቅንብሮች
  2. ስለ
  3. ሕጋዊ መረጃ
  4. ማስታወቂያዎች

ዱካ ለ፦

  1. ቅንብሮች
  2. የመሳሪያዎች ምርጫዎች
  3. ስለ
  4. ሕጋዊ መረጃ
  5. ማስታወቂያዎች
የGoogle ያልሆኑ መሳሪያዎች

ብዙ የተገናኙ የቲቪ መሳሪያዎች ለማስታወቂያ ለዪዎችን ይደግፋሉ እና ተጠቃሚዎች ግላዊነት ከተላበሰ ማስታወቂያ መርጠው እንዲወጡ መንገዶችን ይሰጣሉ። የእነዚህ መሳሪያዎች ሙሉ ዝርዝር እና ተጠቃሚዎች መርጠው መውጣት የሚችሉባቸው መንገዶች እዚህ በአውታረ መረብ ማስታወቂያ ተነሳሽነት ድህረ ገጽ ላይ እንደተዘመኑ ይቀመጣሉ፦ https://thenai.org/opt-out/connected-tv-choices/

የማያቸውን የGoogle ማስታወቂያዎች የሚወስነው ምንድነው?

የትኛውን ማስታወቂያ እንደሚመለከቱ ለመወሰን ብዙ ውሳኔዎች ተወስነዋል።

አንዳንድ ጊዜ የሚያዩት ማስታወቂያ በአሁኑ ወይም የድሮ አካባቢዎ ላይ የተመሠረተ ነው። የእርስዎ አይፒ አድራሻ አብዛኛውን ጊዜ ጥሩ የግምታዊ አካባቢዎ አመላካች ነው። በዚህም በእርስዎ የYouTube.com መነሻ ገጽ ላይ በአገርዎ የሚወጣ ፊልም የሚያስተዋውቅ ማስታወቂያን ሊያዩ ይችላሉ ወይም ለ«ፒዛ» የሚደረግ ፍለጋ በእርስዎ ያሉበት ከተማ ያሉ የፒዛ ቦታዎችን ውጤቶች መልሶ ሊሰጥ ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ የሚያዩት ማስታወቂያ በአንድ ገጽ አውድ ላይ የተመሠረተ ነው። ስለአትክልት ስፍራ ኩትኮታ ጠቃሚ ምክሮችን የያዘ ገጽ እየተመለከቱ ከሆኑ የአትክልት ስፍራ መሣሪያዎች ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ።

አንዳንድ ጊዜ በእርስዎ መተግበሪያ እንቅስቃሴ ወይም በGoogle አገልግሎቶች ላይ ያለ እንቅስቃሴዎ ላይ የተመሠረተ ማስታወቂያ በድር ላይ፤ በድር እንቅስቃሴዎ ላይ የተመሠረተ የውስጠ-መተግበሪያ ማስታወቂያ፤ ወይም በሌላ መሣሪያ ላይ ባለዎት እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረተ ማስታወቂያ ሊመለከቱ ይችላሉ።

አንዳንድ ጊዜ የሚያዩት ማስታወቂያ በGoogle የሚቀርብ ነገር ግን በሌላ ኩባንያ የተመረጠ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ በአንድ የጋዜጣ ድር ጣቢያ ላይ ተመዝግበው ሊሆኑ ይችላሉ። ለጋዜጣው ከሰጡት መረጃ ተንተርሶ የትኛዎቹ ማስታወቂያዎች እንደሚያሳየዎት ላይ ውሳኔዎችን ሊወስን ይችላል፣ እና እነዚያን ማስታወቂያዎች ለማቅረብ የGoogle ማስታወቂያ አቅራቢ ምርቶችን ሊጠቀም ይችላል።

በተጨማሪም፣ እንደ የኢሜይል አድራሻዎ ያለ ለማስታወቂያ ሰሪዎች ባቀረቡት እና ማስታወቂያ ሰሪዎቹ ለGoogle ባጋሩት መረጃ ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎችን ፍለጋ፣ Gmail እና YouTube ጨምሮ በGoogle ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ።

ለምንድነው የተመለከትኳቸውን ምርቶች የGoogle ማስታወቂያዎችን የማየው ያለሁት?

ከዚህ ቀደም የተመለከቷቸው ምርቶች ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። የጎልፍ ክለቦችን የሚሸጥ አንድ ድር ጣቢያ ጎብኝተው፣ ነገር ግን በመጀመሪያ ጉብኝትዎ እነዚያን ክለቦች አልገዙም እንበል። የድር ጣቢያ ባለቤቱ ተመልሰው መጥተው ግዢዎን እንዲያጠናቅቁ ሊያበረታታዎት ይፈልግ ይሆናል። Google የድር ጣቢያዎች አስተዳዳሪዎች ማስታወቂያዎቻቸው ገጾቻቸውን የጎበኙ ሰዎችን እንዲያነጣጥሩ የሚያስችሉ አገልግሎቶችን ያቀርባል።

ይሄ እንዲሠራ Google ወይም አስቀድሞ በአሳሽዎ ውስጥ ያለውን ኩኪ ማንበብ አለበት ወይም የጎልፍ ጣቢያውን ሲጎበኙ አንድ ኩኪ በአሳሽዎ ውስጥ ማስቀመጥ አለበት (አሳሽዎ ይሄ እንዲደረግ ይፈቅዳል ብለን ከወሰድን)።

ከጎልፍ ጋር ምንም ግንኙነት ላይኖረው የሚችል ከGoogle ጋር የሚሰራ ሌላ ጣቢያ ሲጎበኙ የእነዚያ ጎልፍ ክለቦች ማስታወቂያ ሊያዩ ይችላሉ። ያ የሆነው አሳሽዎ ተመሳሳዩን ኩኪ ለGoogle ስለሚልክ ነው። በምላሹም ያንን ኩኪ ተጠቅመን እነዚያን የጎልፍ ክለቦች እንዲገዙ ሊያበረታታዎት የሚችል ማስታወቂያ ልናቀርብልዎ እንችላለን።

እንዲሁም በኋላ ላይ Google ላይ የጎልፍ ክለቦችን ሲፈልጉ ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት Google ወደ የጎልፍ ጣቢያው ያደረጉትን ጉብኝት ሊጠቀምበት ይችላል።

በእርግጥ በዚህ ዓይነቱ ማስታወቂያ ላይ ገደቦች አሉን። ለምሳሌ፣ ማስታወቂያ ሰሪዎች እንደ የጤና መረጃ ወይም ኃይማኖታዊ እምነቶች ባሉ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መረጃ ላይ ተመስርተው ታዳሚ እንዳይመርጡ እንከለክላለን።

ስለGoogle ማስታወቂያዎች ተጨማሪ ይወቁ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ