መግቢያ
የGoogle ተልዕኮ የዓለምን መረጃ ማደራጀት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ እና ጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ነው። የአካባቢ መረጃ በዚያ ተልዕኮ ውስጥ ጠቃሚ ሚና ይጫወታል። ከማሽከርከሪያ አቅጣጫዎች ጀምሮ የእርስዎ የፍለጋ ውጤቶች በእርስዎ አቅራቢያ ያሉ ነገሮችን ማካተታቸውን እስከማረጋገጥ፣ አንድ ምግብ ቤት በተለይ ሥራ የሚበዛበትን ጊዜ ለእርስዎ እስከማሳየት ድረስ የአካባቢ መረጃ በመላው Google ላይ ያሉዎትን የእርስዎን ተሞክሮዎች ይበልጥ ተዛማጅ እና አጋዥነት ያላቸው ሊያደርግ ይችላል።
እንዲሁም የአካባቢ መረጃ አንድን የድር ጣቢያ በትክክለኛው ቋንቋ እንደማቅረብ ወይም የGoogle አገልግሎቶችን ደህንነታቸው የተጠበቀ እንደሆኑ አድርጎ ማቆየት ባለ አንዳንድ ዋና የምርት ተግባራዊነት ላይ ያግዛል።
የGoogle የግላዊነት መመሪያ Google እርስዎ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን ሲጠቀሙ የአካባቢ መረጃን ጨምሮ እንዴት ውሂብን እንደሚጠቀም ይገልጻል። ይህ ገጽ Google ስለሚጠቀመው የአካባቢ መረጃ እና ሥራ ላይ ሊውልባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ያቀርባል። አንዳንድ የውሂብ ልማዶች ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ላሉ ተጠቃሚዎች ሊለያዩ ይችላሉ። በGoogle የግላዊነት ማስታወቂያ ለGoogle መለያዎች እና በFamily Link የሚተዳደሩ መገለጫዎች ለልጆች እና የGoogle የታዳጊ ግላዊነት መመሪያ ውስጥ የበለጠ ይወቁ።
Google የአካባቢ መረጃን እንዴት ይጠቀማል?
Google የአካባቢ መረጃን እንዴት እንደሚጠቀም ጥቅም ላይ እየዋለ ባለው አገልግሎት ወይም ባህሪ እና በሰዎች መሣሪያ እና የመለያ ቅንብሮች ላይ በመመስረት ይለያያል። Google የአካባቢ መረጃን የሚጠቀምባቸው አንዳንድ ቁልፍ መንገዶችን እነሆ።
ተሞክሮዎችን ጠቃሚ ለማድረግ
Google ሰዎች ከGoogle ምርቶች ጋር መስተጋብር ሲፈጥሩ እንደ ለአካባቢ ተዛማጅ እና ይበልጥ ፈጣን የሆኑ የፍለጋ ውጤቶችን፣ ለሰዎች የዕለት ተዕለት ጉዞዎች የትራፊክ ግምቶችን እና የሰውን አውድ ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ጥቆማዎችን ማቅረብ ያሉ ጠቃሚ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የአካባቢ መረጃን ሊጠቀም ወይም ሊያስቀምጥ ይችላል። ለምሳሌ የሆነ የፊልም ጊዜያትን እየፈለገ ያለ ሰው ማየት ሊፈልግ የሚችለው በሌላ ከተማ ውስጥ ሳይሆን በሰፈሩ ውስጥ ባሉ ቲያትሮች ላይ ያሉትን ፊልሞች ነው። በGoogle ካርታዎች ውስጥ የአካባቢ መረጃ ሰዎች ቦታቸውን በካርታ ላይ እንዲያገኙ እና ሊጎበኟቸው ወደሚፈልጓቸው ቦታዎች እንዲያስሱ ያግዛቸዋል።
ሰዎች የነበሩባቸውን ቦታዎች እንዲያስታውሱ ለማገዝ
ሰዎች የጊዜ መስመርን በመጠቀም ከመሣሪያዎቻቸው ጋር የሚሄዱባቸውን ቦታዎች ለማስታወስ መምረጥ ይችላሉ። የጊዜ መስመርን ለመጠቀም ሰዎች የነበሩባቸውን ቦታዎች እና የሄዱባቸውን አቅጣጫዎች ግላዊ ካርታ የሚፈጥረውን የGoogle መለያ ቅንብር የአካባቢ ታሪክ ማብራት ይችላሉ። የአካባቢ ታሪክን ለመጠቀም ከመረጡ የGoogle መተግበሪያዎችን ክፍት ሳያደርጉ ያሉባቸውን ጨምሮ የመሣሪያዎ ትክክለኛ አካባቢዎች በግላዊ ካርታ ላይ ይቀመጣሉ። ይህ መረጃ የጊዜ መስመር ውስጥ መታየት እና መሰረዝ ይችላል።
ሰዎች ነገሮችን በበለጠ ፍጥነት እንዲያገኙ እና ይበልጥ አጋዥ የሆኑ ውጤቶችን እንዲያገኙ ለማገዝ
የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ፣ ለምሳሌ ሰዎች የእንቅስቃሴ ውሂባቸውን እና እንደ አካባቢ ያሉ ተያያዥ ውሂቦችን እንዲያስቀምጡ የሚያስችል የGoogle መለያ ቅንብር ነው፣ ስለዚህ በመላ የGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ሲገቡ ተሞክሯቸውን የበለጠ ግላዊ ማድረግ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ፍለጋ ከዚህ ቀደም ከፈለጉት አጠቃላይ አካባቢ ጋር አግባብነት ያላቸውን ውጤቶች ሊያሳይ ይችላል።
ተጨማሪ አግባብነት ያላቸው ማስታወቂያዎችን ለማሳየት
የአካባቢ መረጃዎ Google ይበልጥ አግባብነት ያላቸውን ማስታወቂያዎች እንዲያሳይዎ ያግዘዋል። እንደ «በአቅራቢያዬ ያሉ የጫማ መደብሮች» የሆነ ነገር ሲፈልጉ የአካባቢ መረጃ በአቅራቢያዎ ያሉ የጫማ መደብሮች ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ሊያገለግል ይችላል። ወይም፣ የቤት እንስሳትን መድን እየፈለጉ ነው እንበል፣ አስተዋዋቂዎች በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ሊያሳዩ ይችላሉ። የአካባቢ መረጃ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የበለጠ ይረዱ።
ተሞክሮዎችን ይበልጥ ደህንነታቸው የተጠበቀ ለማድረግ
Google እንደ ያልተለመደ እንቅስቃሴን ወይም ከአዲስ ከተማ መግባት በማግኘት የመለያዎን ደህንነት ለመጠበቅ ያሉ አንዳንድ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ስለ አካባቢዎ መረጃ ይጠቀማል።
ማንነታቸው የተሰወሩ የማህበረሰብ አዝማሚያዎችን፣ ግምቶችን እና ለምርምር ለማሳየት
እንዲሁም Google ለምርመራ እና የማህበረሰብ አዝማሚያዎችን ለማሳየት የተሰበሰበ ማንነትን የማያሳውቅ የአካባቢ መረጃን ይጠቀማል።
የአካባቢ መረጃ ጥቅም ላይ የሚውልበትም ተጨማሪ መንገዶችን ለማየት የGoogle የግላዊነት መመሪያን ይጎብኙ።
አካባቢ በAndroid መሳሪያዬ እና መተግበሪያዎች ላይ እንዴት ነው የሚሰራው?
የአካባቢ ፍለጋ ውጤቶችን ማግኘት፣ የመጓጓዣ ትንበያዎችን እና በአቅራቢያ ያሉ ምግብ ቤቶችን ከመሳሪያዎ አካባቢ ማግኘት ይችላሉ። የተንቀሳቃሽ ስልኮችዎ ወይም ጡባዊዎችዎ የAndroid መሳሪያ ቅንብሮች በመሳሪያዎ ላይ ያሉ የአካባቢ አገልግሎቶች አካባቢን እንደሚገምቱ እና እንዲሁም በመሳሪያዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ያንን አካባቢ መጠቀም የሚችሉ መሆን አለመሆኑን እና እንዴት እንደሚችሉ ለመቆጣጠር ያስችልዎታል።
የመተግበሪያዎችን የመሣሪያ አካባቢ አጠቃቀም እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ
የትኛዎቹ መተግበሪያዎች የመሣሪያውን አካባቢ ለመጠቀም ፈቃድ እንዳላቸው በAndroid መሣሪያዎ ቅንብሮች ውስጥ መቆጣጠር ይችላሉ። በቅንብሮች ውስጥ መተግበሪያው ትክክለኛ ወይም ግምታዊ አካባቢ መድረስ ይችል እንደሆነ እንዲመርጡ የሚያስችሉዎ መቆጣጠሪያዎች አሉዎት። መተግበሪያ የመሳሪያውን አካባቢ በማንኛውም ጊዜ፣ መተግበሪያው በአገልግሎት ላይ እያለ ብቻ፣ መተግበሪያው ሁልጊዜ መጠየቅ ካለበት ወይም በጭራሽ መድረስ ይችል እንደሆነ እንዲወስኑ የሚፈቅዱ መቆጣጠሪያዎችን አክለናል። የእነዚህ ቅንብሮች እና ቁጥጥሮች መገኘት መሳሪያዎ በሚያሄደው የAndroid ስሪት ይወሰናል። የበለጠ ለመረዳት።
የመሣሪያ አካባቢ እንዴት እንደሚሠራ
በመሳሪያዎ ቅንብሮች ላይ በመመስረት የAndroid መሳሪያዎች ጂፒኤስ፣ ዳሳሾች (እንደ የፍጥነት መለኪያ መሳሪያ፣ ጃይሮስኮፕ፣ ማግኔቶሜትር እና ባሮሜትር ያሉ)፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ ምልክቶች እና የWi-Fi ምልክቶችን ጨምሮ የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም አካባቢን ይገምታሉ። እነዚህ ግብዓቶች የሚቻለውን ትክክለኛ ቦታ ለመገመት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፣ ይህም በመሣሪያው ላይ አስፈላጊው ፈቃድ ላላቸው መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ይሰጣል። ስለ Android መሳሪያዎ የአካባቢ ቅንብሮች የበለጠ ይረዱ።
የሞባይል እና የWi-Fi አውታረ መረብ ምልክቶች በተለይ ጥቅጥቅ ባሉ የከተማ አካባቢዎች ወይም በቤት ውስጥ ሲሆኑ ጨምሮ የጂፒኤስ ምልክቶች በማይገኙበት ወይም ትክክለኛ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች Android የመሳሪያውን አካባቢ እንዲገምት ያግዛሉ። የGoogle አካባቢ ትክክለኝነት (ጂኤልኤ፣ የGoogle ስፍራ አገልግሎቶች በመባልም ይታወቃል) የመሳሪያውን የአካባቢ ግምት ለማሻሻል እነዚህን ምልክቶች የሚጠቀም የGoogle አገልግሎት ነው።
ይህን ይበልጥ ትክክለኛ አካባቢ ለማቅረብ፣ ሲበራ ጂኤልኤ ከጊዜያዊ ተዘዋዋሪ መሣሪያ ለዪን በመጠቀም ከAndroid መሳሪያዎ ላይ—ጂፒኤስ እና ስለ Wi-Fi መዳረሻ ነጥቦች፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረቦች እና የመሳሪያ ዳሳሾች መረጃን ጨምሮ—ከተወሰነ ሰው ጋር ያልተገናኘ የአካባቢ መረጃን በየጊዜው ይሰበስባል። ጂኤልኤ ይህን መረጃ Crowdsource የተደረጉ የWi-Fi ካርታዎች መዳረሻ ነጥቦችን እና የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ ማማዎችን ለመገንባት ጨምሮ የአካባቢን ትክክለኛነት እና አካባቢን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ይጠቀማል።
በAndroid መሳሪያዎ የአካባቢ ቅንብሮች ውስጥ ጂኤልኤን በማንኛውም ጊዜ ማጥፋት ይችላሉ። ጂኤልኤ ቢጠፋም የAndroid መሳሪያዎ አካባቢ መስራቱን ይቀጥላል እና መሳሪያው የመሣሪያውን አካባቢ ለመገመት በጂፒኤስ እና በመሳሪያ ዳሳሾች ላይ ብቻ የሚመረኮዝ ይሆናል።
Google እንዴት የእኔን መገኛ አካባቢ ያውቃል?
እየተጠቀሙባቸው ባሉ ምርቶች እና በመረጧቸው ቅንብሮች ላይ የሚወሰን ሆኖ Google አንዳንድ ይበልጥ የሚጠቀሙባቸውን አገልግሎቶች እና ምርቶች የበለጠ አጋዥ ለማድረግ የተለያዩ አይነት የአካባቢ መረጃዎችን ሊጠቀም ይችላል።
ይህ የአካባቢ መረጃ እንደ የእርስዎ አይፒ አድራሻ ወይም ከመሳሪያዎ ካሉ የእውነተኛ ጊዜ ምልክቶች እና እንዲሁም በGoogle ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች ላይ ካለው የተቀመጠ እንቅስቃሴዎ ሊመጣ ይችላል። Google ስለ አካባቢዎ መረጃ የሚያገኝባቸው ዋና መንገዶችን እነሆ።
ከእርስዎ የአይፒ አድራሻ
አይፒ አድራሻ እንዲሁም የበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ ተብሎ የሚታወቀው በእርስዎ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ ለኮምፒውተርዎ ወይም መሣሪያዎ የሚመደብ ቁጥር ነው። የአይፒ አድራሻዎች በእርስዎ መሣሪያዎች እና በሚጠቀሙባቸው ድር ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመፍጠር ሥራ ላይ ይውላሉ።
እንደሌሎች የበይነመረብ አገልግሎቶች፣ Google አንዳንድ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ስላሉበት አጠቃላይ አካባቢ መረጃን ሊጠቀም ይችላል—አግባብነት ያላቸው ውጤቶች፣ ለምሳሌ አንድ ሰው ስንት ሰዓት እንደሆነ ለመጠየቅ ፍለጋ ሲያደርግ ወይም ያልተለመደ እንቅስቃሴን በማወቅ የመለያዎን ደህንነት መጠበቅ፣ ለምሳሌ ከአዲስ ከተማ በመለያ እንደመግባት ያሉ።
ልብ ይበሉ፦ መሳሪያዎች የበይነመረብ ትራፊክን ለመላክ እና ለመቀበል የአይፒ አድራሻ ያስፈልጋቸዋል። የአይፒ አድራሻዎች እንዲሁ በጂዮግራፊ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ይህ ማለት google.comን ጨምሮ የሚጠቀሟቸው ማናቸውም መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶች ወይም ድረ-ገጾች ስለ አጠቃላይ አካባቢዎ አንዳንድ መረጃዎችን ከአይፒ አድራሻዎ ሊረዱ እና ሊጠቀሙ ይችላሉ።
ከእርስዎ የተቀመጠ እንቅስቃሴ
ወደ Google መለያዎ ከገቡ እና የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴን ካበሩ በGoogle ድረ ገፆች፣ መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ላይ ያለው የእንቅስቃሴ ውሂብዎ በመለያዎ የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊቀመጥ ይችላል። አንዳንድ እንቅስቃሴ የGoogle አገልግሎቱን ሲጠቀሙ ስለነበሩበት አጠቃላይ አካባቢ መረጃን ሊያካትት ይችላል። አጠቃላይ አካባቢን በመጠቀም የሆነ ነገርን ሲፈልጉ የእርስዎ ፍለጋ ቢያንስ 3 ካሬ ኪሜ የሚሆን ቦታን ይጠቀማል ወይም ቦታው ቢያንስ የ1,000 ሰዎችን አካባቢ እስከሚወክል ድረስ ይዘረጋል። ይህ ግላዊነትዎን ለመጠበቅ ያግዛል።
በአንዳንድ ጉዳዮች ውስጥ ከዚህ ቀደም የፈለጉባቸው ቦታዎች ለፍለጋዎ ተዛማጅ የሆነ አካባቢን ለመገመት ሥራ ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ለምሳሌ በቼልሲ ውስጥ ሆነው የቡና መጠጫ ቦታዎችን ከፈለጉ Google በወደፊት ፍለጋዎች ውስጥ ለቼልሲ ያሉ ውጤቶችን ሊያሳይዎት ይችላል።
የእርስዎን የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ የእኔ እንቅስቃሴ ላይ ማየት እና መቆጣጠር ይችላሉ።
ወደ Google መለያዎ ካልገቡ Google የበለጠ ተዛማጅ ውጤቶችን እና ምክሮችን ለማቅረብ በሚጠቀሙበት መሣሪያ ላይ ለቀድሞ ፍለጋዎች የተወሰነ የአካባቢ መረጃን ሊያከማች ይችላል። ፍለጋን ማበጀትን ካጠፉ፣ Google አካባቢዎን ለመገመት የቀደመ የፍለጋ እንቅስቃሴን አይጠቀምም። እንዴት በግላዊነት መፈለግ እና ማሰስ እንደሚችሉ የበለጠ ይረዱ።
ካስቀመጧቸው የቤት ወይም የሥራ አድራሻዎች
እንደ ቤትዎ ወይም ሥራዎ ያሉ ለእርስዎ ጠቃሚ የሆኑ ቦታዎችን በGoogle መለያዎ ላይ ለማስቀመጥ ሊመርጡ ይችላሉ። የቤትዎን ወይም የስራ አድራሻዎን ካቀናበሩ፣ ነገሮችን በቀላሉ እንዲሰሩ፣ ለምሳሌ መመሪያዎችን ማግኘት ወይም ወደ ቤትዎ ወይም ስራዎ በቅርበት ውጤቶችን እንዲያገኙ እና የበለጠ ጠቃሚ ማስታወቂያዎችን ሊያሳዩዎት ይችላሉ።
በእርስዎ Google መለያ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ የቤትዎን ወይም የሥራ አድራሻዎን ማርትዕ ወይም መሰረዝ ይችላሉ።
ከእርስዎ መሣሪያ
የGoogle መተግበሪያዎች እንዴት አካባቢን ከመሣሪያዎ እንደሚጠቀሙ
መሳሪያዎች እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች ያሉ የGoogle መተግበሪያዎችን ጨምሮ ትክክለኛው አካባቢዎ ለመተግበሪያዎች የሚገኝ መሆኑን ለመቆጣጠር ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ቅንብሮች ወይም ፈቃዶች አሏቸው። የዚህ ዓይነቱ ትክክለኛ አካባቢ እንደ Google ካርታዎች ባሉ መተግበሪያዎች ውስጥ አቅጣጫዎችን ለመስጠት ወይም በአቅራቢያ ያሉ ጠቃሚ የፍለጋ ውጤቶችን እንዲያገኙ ይጠቅማል። ለምሳሌ፣ ትክክለኛ የአካባቢ ቅንብሮች ወይም ፈቃዶች ሲበሩ እንደ የአካባቢ ቦታዎች እና የአየር ሁኔታ መረጃ ላሉ ነገሮች የበለጠ ተዛማጅ የፍለጋ ውጤቶችን ያገኛሉ።
ሁለቱም iOS እና Android እርስዎ ማብራት ወይም ማጥፋት የሚችሏቸው የመተግበሪያ የአካባቢ ፈቃዶች ቅንብሮች አሏቸው። በአካባቢ ላይ የተመሰረቱ ባህሪያትን እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ መተግበሪያዎች የእርስዎን አካባቢ እንዲጠቀሙ መፍቀድ ይችላሉ። መተግበሪያዎች በቀላሉ አጋዥ ውጤቶችን ለእርስዎ መስጠት ወይም አካባቢን የማዘመን አስፈላጊነትን በማስወገድ ባትሪን መቆጠብ እንዲችሉ አንዳንዴ የእርስዎን ትክክለኛ አካባቢ ማከማቸት ለእነሱ አስፈላጊ እንደሆነ ያስታውሱ።
እንደ የእኔን መሣሪያ አግኝ ያሉ አንዳንድ መተግበሪያዎች ወይም እንደ የአካባቢ ማጋራት ያሉ የተወሰኑ ባህሪያትን መጠቀም ከፈለጉ በዳራ ውስጥ የመሣሪያዎ አካባቢ ሊያስፈልጋቸው ይችላል።
በAndroid መሳሪያዎ ላይ አካባቢ እንዴት እንደሚሰራ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
እንዴት የአካባቢ ታሪክ እና የድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴ በGoogle መለያዬ ውስጥ ይቀመጣሉ?
በሚቀጥሉት ወራት እና በ2024 ውስጥ በመቀጠል፣ የአካባቢ ታሪክ ቅንብር ይለወጣል። የአሁኑ የአካባቢ ታሪክ ተጠቃሚዎች ይህ ለውጥ በመለያቸው ላይ ተጽዕኖ ሲያሳድር ማሳወቂያ እየተሰጣቸው ነው እናም አንዴ ማሳወቂያ ከተሰጣቸው በኋላ በመለያቸው እና በመተግበሪያ ቅንብሮች ውስጥ የጊዜ መስመር የሚለውን ስም ማየት ይጀምራሉ። ቀድሞውኑ የጊዜ መስመርን ለሚጠቀሙ፣ በቀጥታ የጊዜ መስመርን ያነቁ ተጠቃሚዎችን ጨምሮ፣ በዚህ ገጽ ላይ የቀረበው መረጃ በአካባቢ ታሪክ ውስጥ ስላለው የአካባቢ ውሂብ ለጊዜ መስመር አጠቃቀማቸው ይሠራል። የበለጠ ለመረዳት።
የአካባቢ ታሪክ እና የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ
የአካባቢ ታሪክ እና የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ አካባቢን የሚጠቀሙ የGoogle መለያ ቅንብሮች ናቸው። የእያንዳንዳቸውን አጠቃላይ እይታ እነሆ። ሌሎች ባህሪያት ወይም ምርቶች እንዲሁም የአካባቢ መረጃን ሊሰበስቡ ወይም ሊያከማቹ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ።
የአካባቢ ታሪክ
የአካባቢ ታሪክን ካበሩ እርስዎ የነበሩባቸውን ቦታዎች እና የሄዱባቸውን አቅጣጫዎች እና ጉዞዎች እንዲያስታውሱ የሚያግዘውን ግላዊ ካርታ የጊዜ መስመርን ይፈጥራል።
የአካባቢ ታሪክ በነባሪነት ጠፍቷል። የአካባቢ ታሪክን ካበሩ የአካባቢ ሪፖርት ማድረጊያ ቅንብርን ላበራ ለእያንዳንዱ ብቁ ተንቀሳቃሽ መሳሪያ ትክክለኛ ቦታዎ በመደበኝነት ይቀመጣል። እነዚህ የመሣሪያ አካባቢዎች የGoogle መተግበሪያዎች ጥቅም ላይ በማይውሉበት ጊዜም እንኳ የእርስዎን የጊዜ መስመር ለመገንባት ያገለግላሉ።
የGoogle ተሞክሮዎችን ለሁሉም ሰው የበለጠ ጠቃሚ ለማድረግ የአካባቢ ታሪክን ለሚከተሉት መጠቀም ይቻላል
- ስምማንነቱ በተሰወረ የአካባቢ መረጃ ላይ በመመስረት እንደ የታወቁ ጊዜዎች እና የአካባቢ ግንዛቤዎች ያሉ መረጃዎችን ለማሳየት
- መጭበርበር እና አላግባብ መጠቀምን ለመለየት እና ለመከላከል
- የማስታወቂያዎች ምርቶችን ጨምሮ የGoogle አገልግሎቶችን ማሻሻል እና መገንባት
እንዲሁም የአካባቢ ታሪክ በአንድ ማስታወቂያ ምክንያት ሰዎች መደብሮቻቸውን የመጎብኘት ዕድላቸው ምን ያህል እንደሆነ ለመገመት ንግዶችን ማገዝ ይችላል።
በማንኛውም ጊዜ በእርስዎ የጊዜ መስመር ውስጥ የተቀመጠውን ነገር መገምገም፣ ማርትዕ እና መሰረዝ ይችላሉ። የአካባቢ ታሪክን ካበሩ ለማየት የእርስዎን የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ይጎብኙ። እዚያ የአካባቢ ታሪክ ቅንብሩን መቆጣጠር እና የትኛዎቹ መሣሪያዎች አካባቢያቸውን ሪፖርት እያደረጉ እንደሆነ መቆጣጠር ይችላሉ።
የእርስዎ ትክክለኛ አካባቢ እንደ የአካባቢ ታሪክ ቅንብር አካል ምን ያህል ጊዜ እንደሚሰበሰብ ይለያያል። ለምሳሌ፣ በGoogle ካርታዎች ውስጥ አሰሳን እየተጠቀሙ ከሆነ፣ በደቂቃ ብዙ ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል። ነገር ግን ስልክዎን በንቃት እየተጠቀሙ ካልሆነ በየጥቂት ሰዓቱ አንድ ጊዜ ሊሆን ይችላል።
የአካባቢ ታሪክ ለምን ያህል ጊዜ ተቀምጧል የሚለው በቅንብሮችዎ ላይ ይመረኮዛል—ይህ ውሂብ አንድ ጊዜ ለ3፣ 18 ወይም 36 ወራት ከቆየ በኋላ በራስ-ሰር እንዲሰረዝ መምረጥ ወይም እስከሚሰርዙት ድረስ ውሂቡን ማቆየት ይችላሉ።
ከግምት ውስጥ ያስገቡ
የአካባቢ ታሪክን ካጠፉ
- Google ማንኛውንም ያስቀመጡትን የቆየ የአካባቢ ታሪክ ውሂብ እስከሚሰርዙት ድረስ ማከማቸቱን ይቀጥላል ወይም ኣንደ እርስዎ የራስ-ሰር ስረዛ ቅንብሮች አካል ከመረጡት የጊዜ ወቅት በኋላ የሚሰረዝ ይሆናል።
- የአካባቢ ታሪክን ማጥፋት የአካባቢ መረጃ እንዴት በድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ወይም በሌሎች የGoogle ምርቶች እንደሚቀመጥ ወይም ሥራ ላይ እንደሚውል ላይ ተጽዕኖ አያሳድርም፣ ለምሳሌ በእርስዎ አይፒ አድራሻ ላይ በመመስረት። አሁንም የአካባቢ መረጃን የሚያስቀምጡ ሌሎች ቅንብሮች ሊኖሩዎት ይችላሉ።
የአካባቢ ታሪክን ካበሩ ለማየት የእርስዎን የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ይጎብኙ። የበለጠ ለመረዳት።
የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ
የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ በካርታዎች፣ ፍለጋ እና ሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ተሞክሮዎን የበለጠ ግላዊነትን የተላበሰ ለማድረግ ሥራ ላይ ይውላል። እንዲሁም በእርስዎ የማስታወቂያዎች ቅንብሮች ላይ በመመስረት ይበልጥ ተዛማጅ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ሥራ ላይ መዋል ይችላል። የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ወደ መለያዎ በገቡበት ቦታ ሁሉ በመላው መሣሪያዎችዎ ላይ ይሠራል።
የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ሲበራ Google በመላው የGoogle አገልግሎቶች ላይ ስለሚያደርጓቸው ነገሮች ውሂብን በመለያዎ የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ውስጥ ያስቀምጣል። ይህ የGoogle አገልግሎትን እንደተጠቀሙበት አጠቃላይ አካባቢ ያለ ተያያዥ መረጃን ያካትታል።
ለምሳሌ፣ የአየር ሁኔታ መረጃን ከፈለጉ እና ከመሳሪያዎ የተላከ የአካባቢ ውጤቶችን ካገኙ፣ ይህ እንቅስቃሴ፣ ሲፈልጉ መሳሪያዎ የነበረበትን አጠቃላይ አካባቢ ጨምሮ፣ ወደ ድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴዎ ተቀምጧል። መሣሪያዎ የላከው ትክክለኛ አካባቢ አልተከማቸም፣ የቦታው አጠቃላይ አካባቢ ብቻ ነው የተከማቸው። ለወደፊቱ ፍለጋ Google ይበልጥ አግባብነት ያለው አካባቢን እንዲወስን ለማገዝ የተቀመጠው አካባቢ ከአይፒ አድራሻው ወይም ከመሳሪያዎ ሊመጣ ይችላል። ይህ የተቀመጠ ቦታ ከ30 ቀናት በኋላ ከድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴዎ በራስ-ሰር ይሰረዛል።
የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ውሂብ Google ለእርስዎ ተዛማጅ የሆኑ አጠቃላይ አካባቢዎችን እንዲረዳ እና እንደ ፍለጋ ያሉ ነገሮችን ሲያደርጉ ለእነዚያ ቦታዎች ውጤቶችን እንዲያካትት ያግዘዋል።
የእርስዎን የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች በመጎብኘት አካባቢን እና ሌሎች መረጃዎችን በድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴዎ መገምገም እና መሰረዝ ወይም ማጥፋት ይችላሉ። የድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴን ማጥፋት የወደፊት የእንቅስቃሴ ውሂብዎን ማስቀመጥን ያስቆማል።
ከግምት ውስጥ ያስገቡ
የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴን ሲያጠፉ
- አሁንም የተቀመጠ እንቅስቃሴ ሊኖርዎ ይችላል፣ ይህም እስከሚሰርዙት ድረስ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል። ይህን በማንኛውም ጊዜ መሰረዝ ይችላሉ። የእርስዎ የተቀመጠ የአካባቢ መረጃ አሁንም ከ30 ቀናት በኋላ በራስ-ሰር ይሰረዛል።
- የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴን ማጥፋት የአካባቢ መረጃ እንደ የአካባቢ ታሪክ ባሉ ሌሎች ቅንብሮች እንዴት እንደሚቀመጥ ወይም ሥራ ላይ እንደሚውል ላይ ተጽዕኖ አያሳድርም። አሁንም አይፒ አድራሻን ጨምሮ እንደ ሌሎች ቅንብሮች አካል የተቀመጡ ሌሎች የአካባቢ መረጃ ዓይነቶች ሊኖሩዎት ይችላል።
የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴን ካበሩ ለማየት የእርስዎን የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ይጎብኙ። የበለጠ ለመረዳት
Google የራስ ማንነት የተደበቀበትን ወይም ማንነት የተሰወረበትን የአካባቢ መረጃን እንዴት ይጠቀማል?
Google የሰዎችን ግላዊነት ለማሻሻል ለማገዝ ስየራስ ማንነት የተደበቀበትን ወይም ማንነት የተሰወረበትን የአካባቢ መረጃን ይጠቀማል። ማንነት የተሰወረበት መረጃ በአጠቃላይ ከማንኛውም ግለሰብ ጋር ሊዛመድ አይችልም። የራስ ማንነት የተደበቀበት መረጃ እንደ ሰው መለያ፣ ስም ወይም ኢሜይል አድራሻ ካሉ በግል ሊለይ ከሚችል መረጃ ይልቅ እንደ የቁጥሮች ሕብረቁምፊ ካለ ለይቶ ማወቂያ ጋር ሊተሳሰር ይችላል። የራስ ማንነት የተደበቀበትን ወይም ማንነት የተሰወረበትን የአካባቢ መረጃ Google በምርቶቹ እና አገልግሎቶቹ ውስጥ እንደ ማስታወቂያ ወይም አዝማሚያዎች ላሉ ዓላማዎች ሊጠቀምበት ይችላል።
ተጠቃሚዎች ከአካባቢ መረጃ ጋር የተገናኙ የተወሰኑ የራስን ማንነት መደበቂያ ለዪዎችን ዳግም ማስጀመር ይችሉ ይሆናል። ለምሳሌ ሰዎች በAndroid መሣሪያዎቻቸው ላይ የማስታወቂያ መታወቂያዎችን ዳግም በማስጀመር የተወሰኑ የራስን ማንነት መደበቂያ ለዪዎችን ዳግም ማስጀመር ይችላሉ። በተጨማሪም ተጠቃሚዎች በመሣሪያዎቻቸው ላይ አካባቢን መሰረት ያደረገ አገልግሎት እና ትክክለኛነትን ለማሻሻል ሊጠቀሙበት ለሚችሉት የመሣሪያ ቅንብር GLA ያለውን ጨምሮ Google የተጠቃሚ ግለኝነትን ለማሻሻል የተወሰኑ የራስን ማንነት መደበቂያ ለዪዎችን ዳግም ያስጀምራል።
በተናጥል፣ Google ማንነት የተሰወረበትን የአካባቢ መረጃን ሊጠቀም ይችላል። ለምሳሌ፣ ሰዎች በGoogle ካርታዎች ውስጥ ያሉ ቦታዎችን ለምሳሌ፣ ምግብ ቤት ወይም መናፈሻ ቦታ ላይ መታ ማድረግ እና በአካባቢው ያሉ የእነዚያ ቦታዎች አዝማሚያዎችን ማየት ይችላሉ። እንደ የታወቁ ጊዜዎች ያሉ አዝማሚያዎችን ለመገንባት የሚያገለግል የአካባቢ መረጃ አንድን ግለሰብ ለመለየት ጥቅም ላይ ሊውል አይችልም። Google ትክክለኛ እና ማንነት የተሰወረበት የንግድ መረጃን ለማቅረብ በቂ መረጃ ከሌለው Google ላይ አይታይም።
እንዲሁም Google ዘግተው ለወጡ ሰዎች የፍለጋ ማበጀት ቅንብርን፣ የYouTube ቅንብሮችን እና የማስታወቂያ ቅንብሮችን ጨምሮ ከአሳሻቸው ወይም መሣሪያቸው ጋር የተያያዘ መረጃን እንዲያስተዳድሩ ሌሎች መንገዶችን ያቀርብላቸዋል። የበለጠ ለመረዳት
ስለGoogle የአካባቢ መረጃ አጠቃቀም የGoogle የግላዊነት መመሪያ ውስጥ የበለጠ ይወቁ። Google እንዴት የተሰበሰበ ውሂብን ይዞ እንደሚያቆይ እና Google እንዴት የውሂብን ማንነት እንደሚሰውር የበለጠ ይወቁ።
የአካባቢ መረጃ በGoogle ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?
የGoogle የግላዊነት መመሪያ Google የሚሰበስበውን የአካባቢ መረጃ ጨምሮ የተጠቃሚ ውሂብን ይዞ የማቆየት ልማዶቻችንን ይገልጻል። የአካባቢ መረጃ ምን እንደሆነ፣ እንዴት ሥራ ላይ እንደሚውል እና ሰዎች እንዴት ቅንብሮቻቸውን እንደሚያዋቅሩ በሚሉት ላይ በመመስረት የሚሰበሰበው ለተለያዩ የጊዜ ወቅቶች ነው።
አንዳንድ የአካባቢ መረጃ እስከሚሰርዙት ድረስ ከGoogle መለያዎ ጋር ይቀመጣል
- ይዞ ማቆየትን እና ስረዛን መቆጣጠር፦ ሁለቱም የአካባቢ ታሪክ እና የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ውሂብን ከ3፣ 18 ወይም 36 ወራት በኋላ በራስ-ሰር እንዲሰርዙ የሚያስችሉዎት የራስ-ሰር ስረዛ አማራጮች አላቸው። እንዲሁም የጊዜ መስመርን እና የእኔ እንቅስቃሴን በመጎብኘት ይህን ውሂብ ማየት እና በምርጫዎ መሰረት የተወሰነ እንቅስቃሴን ወይም ጅምላ ውሂብን መሰረዝ ይችላሉ። በማንኛውም ጊዜ እነዚህን ቅንብሮች ማሻሻል ወይም የራስ-ሰር ስረዛ አማራጭዎን መለወጥ ይችላሉ።
- የአካባቢ መረጃን ማስቀመጥ፦ በGoogle ምርት ወይም አገልግሎት ላይ በመመስረት የአካባቢ መረጃ ወደ Google መለያዎ ሊቀመጥ ይችላል። ለምሳሌ በፎቶዎች ውስጥ ያሉ ቦታዎችን መለያ መስጠት ወይም በካርታዎች ውስጥ የቤት ወይም የሥራ አድራሻ ማከል ይችላሉ። ይህን የአካባቢ መረጃ መሰረዝ ይችላሉ።
ውሂብን ሲሰርዙ ውሂቡን መልሶ ማግኘት ከእንግዲህ የማይቻል እንዲሆን Google ከመለያዎ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እና ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድበትን መመሪያ ይከተላል። በመጀመሪያ የሚሰርዙት እንቅስቃሴ ከዕይታ ይወገዳል እና የእርስዎን የGoogle ተሞክሮ ግላዊነት ለማላበስ ከእንግዲህ ሥራ ላይ አይውልም። ከዚያም Google ውሂቡን ከGoogle የማከማቻ ሥርዓቶች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እና ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ የተነደፈ ሂደትን ይጀምራል። Google እንዴት የተሰበሰበ ውሂብን ይዞ እንደሚያቆይ የበለጠ ይወቁ።
ከተወሰነ የጊዜ ወቅት በኋላ የአገልግሎት ጊዜው የሚያበቃ መረጃ
ለሌላ የአካባቢ መረጃ፣ በGoogle እንዴት ውሂብን እንደሚይዝ ላይ እንደተገለጸው Google—በእጅ ከመሰረዝ ይልቅ—ከመሰረዙ በፊት ውሂብን ለተወሰነ ጊዜ የሚያከማችበት ጊዜ አለ። ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እና ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ የሚፈጀው ጊዜ እንደ የውሂብ አይነት ይወሰናል፣ ለምሳሌ፦
- Google የአይፒ አድራሻውን ከ9 ወራት በኋላ እና የኩኪ መረጃን ከ18 ወራት በኋላ በማስወገድ በአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች ውስጥ ያለውን የማስታወቂያ ውሂብ ማንነት ይሰውራል።
- Google ከ30 ቀናት በኋላ በአይፒ ላይ የተመሰረተ አካባቢን እና የመሣሪያ አካባቢን ከእርስዎ የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ይሰርዛል።
ለተወሰኑ ዓላማዎች ለተራዘመ ክፍለ ጊዜያት ተይዞ የሚቆይ መረጃ
በየGoogle የግላዊነት መመሪያ ላይ እንደተገለጸው፣ «አንዳንድ መረጃዎች እንደ ደህንነት፣ ማጭበርበር እና አላግባብ መጠቀምን መከላከል ወይም የፋይናንስ መዝገብ አያያዝ ላሉ ህጋዊ ንግድ ወይም ህጋዊ ዓላማዎች አስፈላጊ ሲሆን ረዘም ላለ ጊዜ እናቆየዋለን»። ስለእኛ የማቆየት ልምምዶች የበለጠ ይረዱ
የአካባቢ መረጃ እንዴት ነው ለማስታወቂያዎች ጥቅም ላይ የሚውለው?
ይበልጥ አግባብነት ያላቸውን ማስታወቂያዎች ለማሳየት እንዲያግዝ
የሚያዩዋቸው ማስታወቂያዎች በአካባቢዎ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ ይችላሉ። በአጠቃላይ፣ በGoogle ላይ ያሉ ማስታወቂያዎች ከሚታዩባቸው ምርቶች ጋር አንድ አይነት የአካባቢ መረጃን ይጠቀማሉ። ለምሳሌ፣ በእርስዎ ቅንብሮች ላይ በመመስረት፣ በፍለጋ እና በሌሎች የGoogle ወለሎች ላይ ያሉ ማስታወቂያዎች በመሣሪያዎ አካባቢ፣ በአይ ፒ አድራሻዎ፣ በቀደመው እንቅስቃሴዎ፣ ወይም በGoogle መለያዎ ላይ ባለው የቤት እና የሥራ አድራሻዎ ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ ዲበ ውሂብ (ለምሳሌ፣ የአሳሽ ሰዓት ሰቅ፣ ጎራ፣ የገጽ ይዘት፣ የአሳሽ አይነት፣ የገጽ ቋንቋ) የእርስዎን ሀገር ወይም እርስዎ የሚፈልጉትን አጠቃላይ አካባቢ ለመገመት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ከአይ ፒ አድራሻዎ፣ ከVPN፣ ከየተኪ ፕሮቶኮል ወይም ከሌሎች የአውታረ መረብ መረጃዎች የምናገኛቸው የአካባቢ ምልክቶች በተጨማሪ በዚህ ዲበ ውሂብ ላይ መተማመን እንችላለን።
የአካባቢ መረጃን መጠቀም የሚያዩዋቸውን ማስታወቂያዎች ላሉበት ቦታ ወይም ለእርስዎ ተዛማጅ ለሆኑ ቦታዎች ይበልጥ ተዛማጅ ለማድረግ ያግዛል። ለምሳሌ የመሣሪያዎ የአካባቢ ቅንብር ከበራ እና በGoogle ላይ በአቅራቢያዎ ያሉ ምግብ ቤቶችን ከፈለጉ የአሁኑ የመሣሪያ አካባቢዎ በአካባቢዎ ያሉ ምግብ ቤቶችን ማስታወቂያዎች ለእርስዎ ለማሳየት ሥራ ላይ ሊውል ይችላል። እንዲሁም አካባቢዎ በGoogle ላይ እንዳሉ ማስታወቂያዎች አካል ሆኖ በአቅራቢያ ያሉ ንግዶችን ርቀት ለእርስዎ ለማሳየት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
Google ያለፈውን አሰሳዎን ወይም የመተግበሪያ እንቅስቃሴዎን (እንደ ፍለጋዎችዎ፣ የድር ጣቢያ ጉብኝቶችዎ፣ ወይም በYouTube ላይ የተመለከቷቸው ቪድዮዎች) እና እንደ የድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴ ቅንብር የተቀመጡ አጠቃላይ አካባቢዎችን በመጠቀም የበለጠ ጠቃሚ ማስታወቂያዎችን ሊያሳይዎ ይችላል። ለምሳሌ፣ Google ላይ በአቅራቢያ ወተት የት እንደሚገዛ ከፈለጉ አውቶቡስዎን ወይም ባቡርዎን እየጠበቁ ሳሉ Google ፍለጋን በተደጋጋሚ በሚያስሱበት አጠቃላይ አካባቢ የሸቀጣሸቀጥ መደብሮችን ማስታወቂያ ሊያዩ ይችላሉ።
አስተዋዋቂዎች በንግዶቻቸው ዙሪያ እንዳሉ አገራት፣ ከተሞች ወይም ክልሎች ባሉ አጠቃላይ አካባቢዎች ላይ ብቻ ማስታወቂያዎችን ማነጣጠር ይችላሉ።
በእኛ የማሳያ አውታረ መረብ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእገዛ ማዕከል የሚለውን ይጎብኙ።
አስተዋዋቂዎች አፈጻጸምን እንዲለኩ ለማገዝ
እንዲሁም Google የGoogle አገልግሎቶች እንዴት ሥራ ላይ እንደሚውሉ ለመረዳት ለትንታኔ እና ለልኬት የአካባቢ መረጃን ሊጠቀም ይችላል። ለምሳሌ የአካባቢ ታሪክን ለማብራት ከመረጡ Google ሰዎች በመስመር ላይ ማስታወቂያዎች ምክንያት መደብሮቻቸውን የመጎብኘት ዕድል ካላቸው አስተዋዋቂዎች እንዲገምቱ ለማገዝ ይህን ውሂብ ይጠቀማል። ከአስተዋዋቂዎች ጋር የሚጋሩት ማንነትን የማያሳውቁ ግምቶች ብቻ እንጂ የግል መረጃ አይደለም። ይህን ለማድረግ Google እንደ የማስታወቂያ ጠቅታዎች ያለ የእርስዎን የመስመር ላይ እንቅስቃሴ ውሂብ ከአስተዋዋቂዎች መደብሮች ጋር ወደተያያዘ የአካባቢ ታሪክ ውሂብ ያገናኛል። የአካባቢ ታሪክዎ ከአስተዋዋቂዎች ጋር አይጋራም።
የGoogle ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለማሻሻል
እንዲሁም Google የማስታወቂያዎች ምርቶቹን ለማሻሻል የአካባቢ መረጃን ይጠቀማል። እንዲሁም በመለያዎ ውስጥ ለተቀመጠ ተዛማጅ እንቅስቃሴ ያለ አጠቃላይ አካባቢን ጨምሮ መስተጋብር ስለሚፈጥሩባቸው ማስታወቂያዎች ያለ ውሂብ ሊሰበሰብ እና የዘመናዊ ጨረታ መሣሪያዎችን በሚያያሽሉ የmachine learning ሞዴሎች ውስጥ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል። የመለያ ውሂብዎ ከአስተዋዋቂዎች ጋር አይጋራም።
የእኔ አካባቢ መረጃ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እንዴት መቆጣጠር እችላለሁ?
የእኔ የማስታወቂያ ማዕከል ውስጥ የGoogle መቆጣጠሪያን የተጠቀሙባቸውን ቦታዎች በመድረስ ከዚህ ቀደም የGoogle ድረ ገፆችን እና መተግበሪያዎችን የተጠቀሙባቸው አጠቃላይ አካባቢዎችዎ በየትኞቹ ማስታወቂያዎች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ መቆጣጠር ይችላሉ።
Googleን የተጠቀሙባቸው አካባቢዎች ሲበሩ
ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ማላበስ እና Googleን የተጠቀሙባቸው ቦታዎች በሚበሩበት ጊዜ Google ከእርስዎ የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ጋር የተቀመጠውን ውሂብ ማስታወቂያዎችዎን ግላዊነት ለማላበስ የGoogle ድረ ገፆችን እና መተግበሪያዎችን ከተጠቀሙባቸው አጠቃላይ አካባቢዎች ጋር በማያያዝ ይጠቀመዋል።
Googleን የተጠቀሙባቸው አካባቢዎች ሲጠፉ
ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ማላበስ ወይም Googleን የተጠቀሙባቸው ቦታዎች በሚጠፉበት ጊዜ Google ከእርስዎ የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ ጋር የተቀመጠውን ውሂብ ማስታወቂያዎችዎን ግላዊነት ለማላበስ የGoogle ድረ ገፆችን እና መተግበሪያዎችን ከተጠቀሙባቸው አጠቃላይ አካባቢዎች ጋር በማያያዝ አይጠቀምም። Googleን የተጠቀሙባቸው ቦታዎች በሚጠፉበት ጊዜም እንኳ በGoogle መለያዎ ውስጥ እንደ ቤትዎ እና ሥራዎ ባቀናበሯቸው አሁን ያሉበት አካባቢ እና ቦታዎች ላይ በመመስረት ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ።
በተጨማሪም፣ ዘግተው ከወጡ፣ በመሳሪያዎ እና የመተግበሪያ ቅንብሮችዎ ላይ በመመስረት ማስታወቂያዎችን ለማሳየት Google አሁን ያሉበትን ቦታ ከአይፒ አድራሻዎ ወይም ከመሳሪያዎ ሊጠቀም ይችላል።
ዘግተው ሲወጡ ለግል የተበጁ ማስታወቂያዎችን እንዴት ማብራት እና ማጥፋት እንደሚችሉ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።