የGoogle የማስታወቂያ አገልግሎቶች በChrome እና Android ላይ በግላዊነት Sandbox ተነሳሽነት በኩል በመስመር ላይ ለሰዎች ግላዊነት በተሻለ ሁኔታ ጥበቃ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች የዲጂታል ማስታወቂያ አቅርቦት እና ልኬት የሚደግፉባቸውን አዳዲስ መንገዶች እየሞከሩ ነው። በChrome እና Android ውስጥ አግባብነት ያላቸው የግላዊነት Sandbox ቅንብሮችን ያነቁ ተጠቃሚዎች በአሳሻቸው ወይም ተንቀሳቃሽ መሣሪያቸው ላይ በተቀመጡ ርዕሶች ወይም ጥበቃ የሚደረግለት ታዳሚ ውሂብ መሠረት አግባብነት ያላቸው ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። እንዲሁም የGoogle የማስታወቂያ አገልግሎቶች በአሳሻቸው እና ተንቀሳቃሽ መሣሪያቸው ላይ የተቀመጠ የመገለጫ ባህሪን ሪፖርት የማድረግ ውሂብን በመጠቀም የማስታወቂያ አፈጻጸምን ሊለኩ ይችላሉ። በግላዊነት Sandbox ላይ ተጨማሪ መረጃ።
የእኛን አገልግሎቶች ከሚጠቀሙ ጣቢያዎች ወይም መተግበሪያዎች Google እንዴት መረጃን እንደሚጠቀም
ብዙ ድር ጣቢያዎች ይዘታቸውን ለማሻሻልና ነጻ እንደሆነ ለማቆየት የGoogle አገልግሎቶችን ይጠቀማሉ። የእኛን አገልግሎቶች ሲያካትቱ እነዚህ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች መረጃን ከGoogle ጋር ይጋራሉ።
ለምሳሌ፣ እንደ Google ትንታኔዎች ያሉ የትንታኔ መሣሪያዎችንም ጨምሮ እንደ AdSense ያሉ አገልግሎቶችን የሚጠቀም፣ የYouTube የቪዲዮ ይዘትን የሚያካትት ድር ጣቢያን ሲጎበኙ የእርስዎ የድር አሳሽ በራስ-ሰር የተወሰነ መረጃን ወደ Google ይልካል። ይህ እርስዎ የሚጎበኙትን የገጽ ዩአርኤል እና የእርስዎን አይፒ አድራሻ ያካትታል። በተጨማሪም በአሳሽዎ ላይ ኩኪዎችን ልናቀናብር ወይም አስቀድመው እዚህ ያሉ ኩኪዎችን ልናነብ እንችላለን። የGoogle ማስታወቂያ ስራ አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ መተግበሪያዎች እንዲሁም እንደ የመተግበሪያው ስም እና ልዩ የማስታወቂያ ለዪ ያለ መረጃ ለGoogle ማስታወቂያ ስራ ያጋራሉ።
Google የእኛን አገልግሎቶች ለማቅረብ፣ እነርሱን ለማንበር ኣና ለማሻሻል፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለመገንባት፣ የማስታወቂያ ማስነገር ሥራን ውጤታማነት ለመለካት፣ ከማጭበርበር እና አላግባብ መጠቀም ድርጊቶች ጥበቃ ለማድረግ፣ እና በGoogle እና በእኛ አጋሮች ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ የሚመለከቱዋቸውን ይዘት እና ማስታወቂያዎች ግላዊነት ለማላበስ በጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች የተጋራውን መረጃ ይጠቀምበታል። ለእነዚህ እያንዳንዳቸው ዓላማዎች እንዴት ውሂብን እንደምናስኬድ የበለጠ ለመረዳት የእኛን የግላዊነት መመሪያ እንዲሁም ስለ Google ማስታወቂያዎች፣ በማስታወቂያ ማስነገር ሥራ ዓውድ ውስጥ እንዴት የእርስዎ መረጃ ጥቅም ላይ እንደሚውል እንዴት ይህን መረጃ Google እንደሚያከማቸው የእኛን ማስታወቂያ ማስነገር ሥራ ገጽ ይመልከቱ።
የእኛ የግላዊነት መመሪያ Google የእርስዎን መረጃ ለማሰናዳት — ለምሳሌ፣ መረጃዎን በእርስዎ ፈቃድ ጋር ወይም እንደ የተጠቃሚዎቻችን ፍላጎቶች ለማሟላት አገልግሎቶችን ማቅረብ፣ ማቆየት እና ማሻሻል ያሉ ህጋዊ ፍላጎቶችን ለማሳካት መረጃዎን ልናሰናዳ እንችላለን — የሚተማመንበት ህጋዊ መሠረትን ያብራራል።
አንዳንድ ጊዜ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ለእኛ ያጋሩት መረጃ ስናሰናዳ እነዚህ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች Google መረጃዎን እንዲያሰናዳ ከመፍቀዳቸው በፊት የእርስዎን ፈቃድ ይጠይቃሉ። ለምሳሌ፣ አንድ ጣቢያ የሚሰበስበውን መረጃ Google እንዲያሰናዳው ከመፍቀዱ በፊት ፈቃድ የሚጠይቅ ሰንደቅ ሊያሳይ ይችላል። ይህ ሲከሰት በGoogle ግላዊነት መመሪያው ውስጥ ከተገለጹት ህጋዊ መሠረቶች ይልቅ እርስዎ ለጣቢያው ወይም ለመተግበሪያው የሰጡትን የፈቃድ ዓላማ እናከብራለን። ፈቃድዎን መቀየር ወይም መሻር ከፈለጉ ይህን ለማድረግ የሚመለከተውን ጣቢያ ወይም መተግበሪያ መጎብኘት አለብዎት።
ማስታወቂያን ግላዊነት ማላበስ
የማስታወቂያ ግላዊነት ማላበስ ከበራ Google የእርስዎን ማስታወቂያዎች ይበልጥ ለእርስዎ ጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የእርስዎን መረጃ ይጠቀማል። ለምሳሌ የተራራ ብስክሌት የሚሸጥ የድርጣቢያ የGoogle ማስታወቂያ አገልግሎቶችን ሊጠቀም ይችል ይሆናል። እርስዎ ያንን ጣቢያ ከጎበኙ በኋላ በGoogle የሚስተናገዱ ማስታወቂያዎችን ከሚያሳይ የተለየ ጣቢያ የተራራ ብስክሊቶችን ማስታወቂያ ሊመለከቱ ይችሉ ይሆናል።
ማስታወቂያ ግላዊነትን ማላበስ ከጠፋ የማስታወቂያ መገለጫ ለመፍጠር ወይም Google ለእርስዎ የሚያሳይዎትን ማስታወቂያዎች ግላዊነት ለማላበስ Google የእርስዎን መረጃ አይሰበስብም ወይም አይጠቀምም። ማስታወቂያዎችን ይመለከታሉ ሆኖም ግን ጠቃሚ ላይሆኑ ይችላሉ። ማስታወቂያዎች አሁንም ድረስ እርስዎ በተመለከቱት የድር ጣቢያ ርዕሰ ጉዳይ ወይም እየተመለከቱ በነበሩት መተግበሪያ ላይ፣ አሁን ባሉት የእርስዎ የፍለጋ ቃላት ወይም በእርስዎ አጠቃላይ የመገኛ አካባቢ ላይ የተመረኮዙ ሊሆኑ ቢችሉም በእርስዎ ዝንባሌዎች፣ የፍለጋ ታሪክ ወይም የአሰሳ ታሪክ ላይ የተመረኮዙ አይሆኑም። እንደ የማስታወቂያ ማስነገር ሥራን ውጤታማነት ለመለካት እና የማጭበርበር ድርጊትን እና በደል ማድረስን ድርጊት ጥበቃ ለማድረግ ለመሳሰሉ ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት ሌሎች ዓላማዎች አሁንም ድረስ የእርስዎ መረጃ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
የGoogle አገልግሎቶችን ከሚጠቀም ድር ጣቢያ ወይም መተግበሪያ ጋር መስተጋብር ሲፈጥሩ Googleን ጨምሮ ከማስታወቂያ አቅራቢዎች ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን መመልከት ይፈልጉ እንደሆነ እንዲመርጡ ሊጠየቁ ይችላሉ። ምርጫዎ ምንም ሆነ ምን የእርስዎ የማስታወቂያ ግላዊነት ማላበሻ ቅንብር ከጠፋ ወይም የእርስዎ መለያ ለግላዊነት ለተላበሱ ማስታወቂያዎች ብቁ ካልሆነ Google እርስዎ የሚያዩዋቸውን ማስታወቂያዎች ግላዊነት አያላብስም።
የማስታወቂያ ቅንብሮችዎን በመጎብኘት እኛ ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ምን መረጃ እንደምንጠቀም መቆጣጠር ይችላሉ።
በእነዚህ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ በGoogle የሚሰበሰበውን መረጃ እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ
የGoogle አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ጣቢያዎችን እና መተግበሪያዎችን ሲጎበኙ ወይም መስተጋብር ሲፈጽሙ በእርስዎ መሣሪያ የሚጋራውን መረጃ መቆጣጠር የሚችሉባቸው አንዳንድ መንገዶች እነሆ፦
- የማስታወቂያ ቅንብሮች በGoogle አገልግሎቶች ላይ (እንደ Google ፍለጋ ወይም YouTube የመሳሰሉ)፣ ወይም የGoogle ማስታወቂያ አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ የGoogle ያልሆኑ የድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ የሚመለከቷቸውን ማስታወቂያዎች ለመቆጣጠር ይግዝዎታል። ማስታወቂያዎች እንዴት ግላዊነት እንደሚላበሱ፣ ከማስታወቂያ ግላዊነት ማላበስ መርጦ ስለመውጣት ኣና የተወሰኑ ማስታወቂያ አስነጋሪዎችን ማገድን በተመለከተ በተጨማሪ የበለጠ መረዳት ይችላሉ።
- ወደ የእርስዎ የGoogle መለያ በመለያ የገቡ ከሆነ በእርስዎ የመለያ ቅንብሮች ላይ የሚመረኮዝ ሆኖ፣ የእኔ እንቅስቃሴ እርስዎ የGoogle አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ እርስዎ ከጎበኟቸው ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ የምንሰበስበውን መረጃ ጨምሮ የተፈጠረውን ውሂብ ለመገምገም እና ለመቆጣጠር እንዲችሉ ያስችልዎታል። በቀን እና ርዕስ ማሰስ፣ እና ከፊል ወይም ሙሉ እንቅስቃሴዎን መሰረዝ ይችላሉ።
- ብዙ ጣቢያዎች ጎብኚዎች እንዴት ከጣቢያዎቻቸው ወይም መተግበሪያዎቻቸው ጋር እንደሚሳተፉ ለመረዳት Google ትንታኔዎችን ይጠቀማሉ። ትንታኔዎችን በአሳሽዎ ላይ መጠቀም ካልፈለጉ የGoogle ትንታኔዎች አሳሽ ተጨማሪ መጫን ይችላሉ። ስለGoogle ትንታኔዎች እና ግላዊነት የበለጠ ይረዱ።
- በChrome ውስጥ ያለው ማንነት የማያሳውቅ ሁነታ ድረ-ገጾች እና ፋይሎች በአሳሽዎ ታሪክ ውስጥ ሳይመዘገቡ ድሩን እንዲያስሱ ያስችልዎታል። ሁሉንም ማንነት የማያሳውቁ መስኮቶችዎን እና ትሮችዎን ከዘጉ በኋላ ኩኪዎች ይሰረዛሉ፣ እና የእርስዎ ዕልባቶች እና ቅንብሮች እስኪሰርዟቸው ድረስ ይከማቻሉ። ስለኩኪዎች የበለጠ ይረዱ። በChrome ወይም በሌላ የግል አሰሳ ሁነታ ማንነትን የማያሳውቅ ሁነታን መጠቀም የGoogle አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ድረ-ገጾችን ሲጎበኙ የውሂብ መሰብሰብን አይከለክልም፣ እና Google አሁንም እነዚህን አሳሾች ተጠቅመው ድር ጣቢያዎችን ሲጎበኙ ውሂብ ሊሰበስብ ይችላል።
- በርካታ አሳሾች Chromeን ጨምሮ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን እንዲያግዱ ያስችልዎታል። በእርስዎ አሁን ባለው አሳሽ ውስጥ ያሉ ማናቸውንም ኩኪዎችን በተጨማሪ ማጽዳት ይችላሉ። ስለ በChrome ውስጥ ኩኪዎችን ማስተዳደር በተመለከተ የበለጠ ይረዱ።