እኛ የምንሰበስበውን ውሂብ Google እንዴት ይዞ እንደሚያቆይ

እርስዎ የGoogle አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ ውሂብን እንሰበስባለን። ምን እንደምንሰብስብ፣ ለምን እንደምንሰበስበው፣ እና እንዴት የእርስዎን መረጃ ማስተዳደር እንደሚችሉ በእኛ የግላዊነት መመሪያ ላይ ተብራርተዋል። ይህ ይዞ የማቆየት መመሪያ ለምን የተለያየ ዓይነት ውሂብን ለተለያየ ክፍለ ጊዜ ያክል ይዘን እንደምናቆይ ያብራራል።

አንዳንድ ውሂብ እርስዎ በፈለጉት ጊዜ ሊሰርዙት ይችላሉ፣ አንዳንድ ውሂብ በራስሰር ይሰረዛል እና አስፈላጊ ሲሆን እኛ ረዘም ላሉ ክፍለ ጊዜያት የምናቆየው አንዳንድ ውሂብም ይኖራል። እርስዎ ውሂብ ሲሰርዙ የእርስዎ ውሂብ ከእኛ አገልጋዮች ላይ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እና ሙሉ በሙሉ መወገዱን ወይም ማንነትን በማያሳውቅ ሁኔት ተጠብቆ መቆየቱን ለማረጋገጥ ሲባል የስረዛ መመሪያን እንከተላለን። Google እንዴት ውሂብን ማንነት እንደማያሳውቅ እንደሚያደርግ

እርስዎ እስከሚያስወግዱት ድረስ መረጃ ባለበት ተይዞ ይቆያል

በእርስዎ የGoogle መለያ ውስጥ የተከማቸን ውሂብ እንዲያስተካክሉ ወይም እንዲሰርዙ የሚያስችልዎትን የተለያዩ አገልግሎቶችን እናቀርባለን። ለምሳሌ፣ የሚከተለውን ማድረግ ይችላሉ፦

እርስዎ ለማስወገድ እስኪመርጡ ድረስ ይህን ውሂብ በእርስዎ የGoogle መለያ ውስጥ እናቆየዋለን። ወደ Google መለያ ሳይገቡ የእኛን አገልግሎቶች የሚጠቀሙ ከሆነ እንደ መሣሪያ፣ አሳሽ ወይም መተግበሪያ የመሳሰሉ የእኛን አገልግሎቶች ለመድረስ ከሚጠቀሙበት ጋር የተቆራኘ አንዳንድ መረጃን ለመሰረዝ የሚያስችልዎትን ችሎታ በተጨማሪ እንሰጥዎታለን።

ውሂብ ከተወሰነ ክፍለ ጊዜ በኋላ የአገልግሎት ጊዜው ያበቃል

በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ውሂብን ለመሰረዝ የሚያስችል መንገድን ከማቅረብ ይልቅ አስቀድሞ ለተወሰነ ጊዜ ያህል እናከማቸዋለን። ለእያንዳንዱ የውሂብ ዓይነት የተሰበሰበበት ምክንያት ላይ በመመርኮዝ ይዞ የማቆየት የጊዜ ገደቦችን እናቀናብራለን። ለምሳሌ፣ የእኛ አገልግሎቶች በብዙ ዓይነቶች የተለያዩ መሣሪያዎች ላይ በአግባቡ መታየታቸውን ለማረጋገጥ የአሳሽ ስፋትን እና ቁመትን እስከ 9 ወራት ድረስ እንዲቆይ ልናደርግ እንችላለን። እንዲሁም በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተወሰነ ውሂብን ማንነት ለመሰወር ወይም ማንነት ለመደበቅ እርምጃዎችን እንወስዳለን። ለምሳሌ የአይፒ አድራሻውን አካል ከ9 ወራት በኋላ እና የኩኪ መረጃን ከ18 ወራት በኋላ በማስወገድ በአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች ውስጥ ያለውን የማስታወቂያ ውሂብ ማንነት እንሰውራለን። እንዲሁም እንደ ከተጠቃሚዎች Google መለያዎች የተቋረጡ መጠይቆች ያለ የራስ ማንነት የተደበቀበት ውሂብን ለተወሰነ ጊዜ ልናቆይ እንችላለን።

የእርስዎ Google መለያ እስከሚሰረዝ ድረስ ተይዞ የሚቆይ መረጃ

ተጠቃሚዎች ከእኛ ባህሪያት ጋር እንዴት መስተጋብር እንደሚፈጥሩ እና የእኛን አገልግሎቶች እንዴት ማሻሻል እንደምንችል እኛን ለማገዝ ጠቃሚ ከሆነ የተወሰነ ውሂብን የእርስዎ የGoogle መለያ ለሚኖረው ዕድሜ ያህል ይዘትን እናቆያለን። ለምሳሌ፣ በGoogle ካርታዎች ላይ የፈለጉትን አድራሻ ከሰረዙ መለያዎ አሁንም የአቅጣጫዎች ባህሪውን እንደተጠቀሙ ሊያከማች ይችላል። በዚህ መንገድ Google ካርታዎች ወደፊት የአቅጣጫዎችን ባህሪ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ከማሳየት ሊቆጠብ ይችላል።

ለተወሰኑ ዓላማዎች ለተራዘመ ክፍለ ጊዜያት ተይዞ የሚቆይ መረጃ

አንዳንድ ጊዜ የንግድ ሥራ እና ሕጋዊ ግዴታዎች ለተወሰኑ ዓላማዎች ለተራዘመ ክፍለ ጊዜ የተወሰነ መረጃን ይዘን እንድናቆይ ያስገድዱናል። ለምሳሌ፣ Google ለእርስዎ ክፍያን ሲያስተናግድ ወይም እርስዎ ለGoogle ክፍያን ሲፈጽሙ ለታክስ ወይም ለሒሳብ ሥራ ዓላማዎች በሚፈልገው መጠን ረዘም ላሉ ክፍለ ጊዜያት ይህን ውሂብን ይዘን እናቆያለን። አንዳንድ የተወሰነ ውሂብን ለተወሰኑ ክፍለ ጊዜያት ይዘን ልናቆይ የምንችልባቸው ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

ለደህንነት አስተማማኝ እና የተሟላ ስረዛ መደረጉን ለማረጋገጥ

በእርስዎ የGoogle መለያ ውስጥ ውሂብን ሲሰርዙ፣ ከምርቱ እና ከእኛ ሥርዓቶች ላይ ውሂቡን የማስወገዱን ሂደት ወዲያውኑ እንጀምራለን። በመጀመሪያ፣ ከእይታ ላይ ማስወገድ ላይ ዒላማ እናደርጋለን እንዲሁም ውሂቡ የእርስዎን የGoogle ተሞክሮ ግላዊነት ለማላበስ ከእንግዲህ ጥቅም ላይ ሊውል አይችልም። ለምሳሌ፣ ከእርስዎ የእኔ እንቅስቃሴ ዳሽቦርድ ላይ የተመለከቱትን ቪዲዮ ከሰረዙ YouTube ወዲያውኑ ለዚያ ቪዲዮ የእርስዎን የመመልከት ሂደት ማሳየትን ያቆማል።

ከዚህ በመቀጠል ከእኛ የማከማቻ ሥርዓቶች ላይ ውሂቡን ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ እና በተሟላ ሁኔታ ለመሰረዝ የተዘጋጀ የሥራ ሂደትን እናስጀምራለን። ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ የውሂብ ስረዛ የእኛን ተጠቃሚዎች እና ደንበኞች በድንገት ውሂብ እንዳይጠፋባቸው ጥበቃ ለማድረግ አስፈላጊ ነው። ከእኛ አገልጋዮች ላይ ውሂብን አሟልቶ መሰረዝ ለተጠቃሚ የአእምሮ ሰላም ያንኑ ያክል አስፈላጊ ነው። ይህ ሂደት በአጠቃላይ አነጋገር ከስረዛ በኋላ ወደ 2 ወራት ገደማ ጊዜ ይወስዳል። ይህ ብዙውን ጊዜ ውሂብ ሳይታሰብ ከተወገደ መልሶ ለማግኘት የሚያስፈልገውን የአንድ ወር ጊዜን ያካትታል።

ውሂብ የሚሰረዝበት እያንዳንዱ የGoogle ማከማቻ ሥርዓት ለደህንነት አስተማማኝ የሆነ እና የተሟላ ስረዛ የሚሆን የየራሱ የስረዛ ሂደት አለው። ይህ ሁሉም ውሂብ መሰረዙን ለማረጋገጥ ወይም በስህተቶች ምክንያት ለተፈጠረ ስረዛ መልሶ ማግኛን ጊዜ ለመፍቀድ እንዲቻል የሚያስችሉ አጭር ማዘግያ ጊዜዎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ በሥርዓቱ ላይ በተደጋጋሚ ማለፍን ሊያካትት ይችል ይሆናል። በመሆኑም ለደህንነት አስተማማኝ በሆነ መንገድ እና ሙሉ በሙሉ ውሂብን ለመሰረዝ ተጨማሪ ትርፍ ጊዜ ሲያስፈልግ ስረዛ ተጨማሪ ረዥም ጊዜን ሊወስድ ይችል ይሆናል።

የእኛ አገልግሎቶች በተጨማሪ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ አደጋዎች መልሶ ማገገም እንዲቻል ለማገዝ እንደ ሌላ የጥበቃ ሽፋን የተመሣጠረ የምትኬ ማከማቻን ይጠቀማሉ። ውሂብ በእነዚህ ሥርዓቶች ላይ እስከ 6 ወራት ድረስ ሊቆይ ይችላል።

እንደ ማናቸውም የስረዛ ሂደት ሁሉ እንደ መደበኛ የተለመደ የማንበር ሂደት፣ ያልተጠበቁ መውጣቶች፣ ሳንካዎች ወይም በእኛ ፕሮቶኮሎች ውስጥ የሚያጋጥሙ መሰናከሎች በሂደቶች እና በዚህ አንቀጽ ላይ በተገለጹ የጊዜ ቅጽሮች ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። እንዲህ ያሉ ችግሮች ሲኖሩ ፈልጎ ለማወቅ እና ችግሮቹን ለመቅረፍ የተዘጋጁ ሥርዓቶችን እንጠቀማለን።

ደህንነት፣ ማጭበርበር እና አላግባብ መጠቀም ድርጊትን ለመከላከል

መግለጫ

እርስዎን፣ ሌሎች ሰዎችን እና Googleን ከማጭበርበር፣ አላግባብ መጠቀም እና ያልተፈቀደ መዳረሻ ለመጠበቅ።

መላ ምቶች

ለምሳሌ Google የማስታወቂያ ማጭበርበር ድርጊትን እየፈጸመ እንደሆነ ከጠረጠረ።

የፋይናንስ መዝገብን ለመያዝ

መግለጫ

Google የእርስዎን ክፍያ ሲያስተናግድ ወይም እርስዎ ለGoogle ክፍያ ሲፈጽሙ ጨምሮ Google ለፋይናንስ ግብይት አንድ አካል ሲሆን። እንደ ሒሳብ አያያዝ፣ የግጭት አፈታት እና ከግብር፣ ፀረ ማጭበርበር ድርጊት፣ ፀረ በሕገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ ማድረግ ድርጊት እና ሌሎች የፋይናንስ ደንቦች ተገዢ ለመሆን ለመሳሰሉ ዓላማዎች ብዙውን ጊዜ ይህን መረጃ ለተራዘመ ጊዜ ይዞ ማቆየት ያስፈልግ ይሆናል።

መላ ምቶች

ለምሳሌ ከPlay መደብር መተግበሪያዎችን ወይም ምርቶችን ከGoogle መደብር ሲገዙ።

በሕጋዊ ወይም የደንብ ግዴታዎች ለመገዛት

መግለጫ

ማንኛውም የሚመለከተው ሕግ፣ ደንብ፣ ሕጋዊ ሂደት ወይም ተፈጻሚነት ያለው የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም ወይም ጥሰቶች ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን መመርመር ጨምሮ የሚመለከተውን የአገልግሎት ውል ለማስፈጸም ሲያስፈልግ።

መላ ምቶች

ለምሳሌ Google ሕጋዊ የፍርድ ቤት መጥሪያ ወይም ትእዛዝ ሲቀበል።

የእኛን አገልግሎቶች ቀጣይነት ለማረጋገጥ

መግለጫ

ለእርስዎ እና ለሌሎች ተጠቃሚዎች የአገልግሎት ቀጣይነትን ለማረጋገጥ።

መላ ምቶች

ለምሳሌ ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር መረጃን ሲጋሩ (እንደ ለሌላ ሰው ኢሜይል ሲልኩ)፣ ከእርስዎ Google መለያ ላይ ይህን መሰረዝ በተቀባዮች የተያዙ ቅጂዎችን አያስወግድም።

ከGoogle ጋር የሚኖሩ ቀጥታ የመልዕክት ልውውጦች

መግለጫ

ከGoogle ጋር በደንበኛ ድጋፍ መስጫ ሰርጥ፣ በግብረ መልስ መስጫ ቅጽ፣ ወይም የሳንካ ሪፖርት በኩል በቀጥታ የመልዕክት ለውጥ አድርገው ከነበረ Google የነዚህን መልዕክት ልውውጦች ምክንያታዊ የሆኑ ሪኮርዶች ይዞ ሊያቆይ ይችላል።

መላ ምቶች

ለምሳሌ እንደ Gmail ወይም Drive በመሰለ የGoogle መተግበሪያ ውስጥ እርስዎ ግብረ መልስ ሲልኩ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ