የGoogle የአገልግሎት ውል ስምምነት
ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፦ 14 ኤፕሪል 2014 (የተመዘገቡ ስሪቶችን አሳይ)
ወደ Google እንኳን በደህና መጣህ!
በምርቶቻችንን እና አገልግሎቶቻችን (ከዚህ በኋላ«አገልግሎቶች» ተብለው በሚጠሩት) ስለተጠቀምክ እናመሰግናለን። አገልግሎቶቹን ያቀረበው፣ አድራሻው በ1600 Amphitheatre Parkway፣ Mountain View፣ CA 94043፣ United States የሆነው ጉግል ኢንኮርፖሬትድ /Google Inc./ (ከዚህ በኋላ “Google” ተብሎ የሚጠራው) ነው።
አገልግሎቶቻችንን በምትጠቀምበት ወቅት በነዚህ ደንቦች እንደተስማማህ ይቆጠራል። እባክህ በጥንቃቄ አንብባቸው።
አገልግሎቶቻችን በጣም የተለያዩ ናቸው፣ ስለዚህም በአንዳንድ አገልግሎቶቻችን ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ፣ /የዕድሜ መስፈርትን ጨምሮ/ ተጨማሪ የውል ድንጋጌዎች ወይም የምርት አጠቃቀም ቅድመ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ ተጨማሪ ድንጋጌዎች አግባብነት ካለው አገልግሎት ጋር አብረው የሚቀርቡ ሲሆን፣ አገልግሎቱን የምትጠቀም ከሆነ ከኛ ጋር ያለህ ስምምነት አካል ይሆናሉ።
በአገልግሎቶቻችን ስለመጠቀም
አገልግሎቶቻችንን በምትጠቀምበት ጊዜ አብረው የሚቀርቡልህን ፖሊሲዎች/ደንቦች መከተል አለብህ።
አገልግሎቶቻችንን አላግባብ አትጠቀም። ለምሳሌ፤ በአገልግሎት አቅርቦታችን ላይ ጣልቃ አትግባ ወይም አገልግሎቱን ለማወክ አትሞክር፣ወይም አገልግሎቶቹን ለመስጠት ከምንጠቀምባቸው መንገዶች እና መመሪያዎች ውጭ በሆነ መንገድ አገልግሎቶቹን ለማግኘት አትሞክር። አገልግሎቶቻችንን አግባብነት ያለው ህግ በሚፈቅደው መሠረት መጠቀም ያለብህ ሲሆን፣ ይህም ምርቶችና አገልግሎቶችን ወደውጭ መላክ እና ከውጭ አስገብሮ መልሶ ወደውጭ መላክን ለመቆጣጠር የወጡ ሕጎችን እና ደንቦችን ይጨምራል። በውሎቻችን ወይም ፖሊሲዎቻችን የማትመራ ከሆነ ወይም የስነምግባር ጥሰት መፈፀምህን ከጠረጠርን ላንተ የምንሰጠውን አገልግሎት ለጊዜው ልናግድ ወይም ልናቋርጥ እንችላለን።
አገልግሎቶቻችንን በመጠቀምህ በአገልግሎቶቻችን ላይም ሆነ አገልግሎቶቹን በመጠቀም ባገኘኸው መረጃ ላይ ምንም ዓይነት የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት አይሰጥህም። ከባለቤቱ ፈቃድ ካላገኘህ ወይም በሕግ ካልተፈቀደ በቀር በአገልግሎታችንን ያገኘኸውን መረጃ/ይዘት መጠቀም አትችልም። እነዚህ የውል ድንጋጌዎች ማናቸውንም በአገልግሎቶቻችን ጥቅም ላይ የዋሉ የብራንዲንግ/ንግድ ምልክት ስራ ወይም ዓርማዎችን እንድትጠቀም መብት አይሰጡህም። እንድታያቸው የተደረጉ ማናቸውንም ወይም ከኛ አገልግሎት ጋር አብረው የቀረቡ ሕጋዊ ማሳሰቢያዎችን አታስወግድ/አታንሳ፣ እንዳይታዩ አታድርግ ወይም አትቀይር።
አገልግሎቶቻችን የሚያሳዩዋቸው አንዳንድ ይዘቶች/መረጃዎች የGoogle አይደሉም። ለዚህ አይነት ይዘት/መረጃ ኃላፊነቱን የሚወስደው መረጃውን ያቀረበው አካል ብቻ ነው። መረጃው/ይዘቱ ሕገወጥ መሆኑን ወይም የኛን ፖሊሲዎች እንደሚጥስ ለማወቅ ስንል ይዘቱን ልንገምግም እንችላለን፣ የኛን ፖሊሲዎች ወይም ሕግን እንደሚጥስ በተጨባጭ ያመንንበትን ይዘት/መረጃ ልናስወግድ ወይም እንዳይታይ ልንከለክል እንችላለን። ይህ ማለት ግን የግድ ሁልጊዜ በድረ ገጻችን የሚቀርቡ መረጃዎችን ይዘት እንገመግማለን ማለት አይደለም፣ እንደምንገመግምም ማሰብ የለብህም።
አገልግሎቶቻችንን በምትጠቀምበት ወቅት የአገልግሎት ማስታወቂያዎች፣ አስተዳደራዊ መልእክቶች እና ሌላ መረጃ ልንልክልህ እንችላለን። እንዚህን መረጃዎች ካልፈለግህ ላለመቀበል/ለመተው ትችላለህ።
ከአገልግሎተቻችን ውስጥ አንዳንዶቹ በተንቀሳቃሽ ስልክ መሳሪያዎች ላይ ይገኛሉ። እንደዚህ አይነት አገልግሎቶችን እርስዎን በሚያውክ እና የትራፊክ እና የደህንነት ህጎችን እንዳያከብሩ በሚከለክልዎት መንገድ አይጠቀሙ።
የGoogle መለያህ
አንዳንዶቹን አገልግሎቶቻችንን ለመጠቀም የGoogle መለያ ሊያስፈልግህ ይችላል። የራስህን የGoogle መለያ መፍጠር ትችላለህ፣ ወይም የGoogle መለያ በአስተዳዳሪው ሊሰጥህ የሚችል ሲሆን፣ አስተዳዳሪውም ለምሳሌ አሰሪህ ወይም የትምህርት ተቋምህ ሊሆን ይችላል። በአስተዳዳሪ በተሰጠ የGoogle መለያ የምትጠቀም ከሆነ፣ የተለዩ ወይም ተጨማሪ የአገልግሎት ደንቦች ተፈጻሚ ሊሆኑብህ ይችላሉ፤ እናም አስተዳዳሪህ ያንተን አድራሻ ሊከፍተው ወይም እንዳትጠቀምበት ሊያደርገው ይችላል።
የእርስዎን የGoogle መለያ ለመጠበቅ የእርስዎን ይለፍ ቃል በሚስጥር ያስቀምጡ። በGoogle መለያዎ ላይ ወይም በእሱ በኩል ለሚከሰቱ እንቅስቃሴዎች ሃላፊነቱ የእርስዎ ነው። የGoogle መለያ የእርስዎን ይለፍ ቃል በሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ላይ ላለመጠቀም ይሞክሩ። በማናቸውም ፈቃድ ባልተሰጠው መንገድ የእርስዎ ይለፍ ቃል ወይም የGoogle መለያዎ ጥቅም ላይ እንደዋለ ከአወቁ፣ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።
የግላዊነት እና የቅጂ መብት ጥበቃ
የGoogle ግላዊነት ፖሊሲዎች እኛ እንዴት የግል መረጃህንን እንደምናስተናግድ እና አገልግሎቶቻችንን ስትጠቀም እንዴት ግላዊነትህን እንደምንጠብቅ ያብራራሉ። አገልግሎቶቻችንን በመጠቀምህ፣ Google እንደዚህ ያለውን የግል መረጃ በግላዊነት ፖሊሲያችን መሰረት ሊጠቀምበት እንደሚችል ተስማምተሃል ማለት ነው።
የቅጂ መብት ጥሰቶችን የሚመለከቱ አቤቱታዎች ሲቀርቡልን ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን፤ በተደጋጋሚ የቅጂ መብት የሚጥሱ ሰዎችን አድራሻዎችም በዩኤስ አሜሪካ ዲጂታል ሚሊኒየም የቅጂ መብት ሕግ ላይ በተቀመጠው ስርዓት መሰረት እንዲቋረጡ/እንዲዘጉ እናደርጋለን።
የቅጂ መብት ባለቤቶች በኢንተርኔት አጠቃቀም ወቅትየአእምሮ ንብረታቸውን ማስጠበቅ እንዲችሉ የሚያግዝ መረጃ እንሰጣለን። ማንም ሰው የቅጂ መብቶችህን እየጣሰ እንደሆነ ከጠረጠርክና ለኛ ማሳወቅ ከፈለግክ፣ በኛ እገዛ ማዕከል ውስጥ ስለአቤቱታ አቀራረብ እና Google ለሚቀርቡ አቤቱታዎች የሚሰጠውን የምላሽ አሰጣጥ ፖሊሲ በተመለከተ መረጃ ማግኘት ትችላለህ።
በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ስለሚገኙ ያንተ መረጃዎች/ይዘቶች
አንዳንድ አገልግሎታችን ይዘት እንዲሰቅሉ፣ እንዲያስገቡ፣ እንዲያከማቹ፣ እንዲልኩ ወይም እንዲቀበሉ ያስችሉዎታል። በዚያ ይዘት ላይ ያለዎት ማናቸውም የአእምሮ ንብረት መብቶችን በሙሉ ባለቤት እንደሆኑ ይቀጥላሉ። በአጭሩ፣ የእርስዎ የሆኑ ነገሮች የእርስዎ እንደሆኑ ይቆያሉ።
ይዘት ወደ አገልግሎታችን ወይም በእሱ በኩል ሲሰቅሉ፣ ሲያስገቡ፣ ሲያከማቹ፣ ሲልኩ ወይም ሲቀበሉ Google (እና አብረናቸው የምንሰራ) እንዲጠቀም፣ እንዲያስተናግድ፣ እንዲያከማች፣ እንዲያባዛ፣ እንዲቀይር፣ የመነጩ ስራዎችን (እንደ ከትርጉሞች፣ ከለውጥ ስራዎች ወይም ይዘትዎ ከአገልግሎታችን ጋር በተሻለ ሁኔታ እንዲሰሩ ከሌሎች የምናደርጋቸው ለውጦች የመጡ አይነት) እንዲፈጥር፣ ለሌሎች እንዲሰጥ፣ እንዲያትም፣ በይፋ እንዲያሳይ እና እንደዚህ ያለ ይዘት እንዲያሰራጭ አለምአቀፋዊ የሆነ ፍቃድ እየሰጡት ነው። በዚህ ፍቃድ የሚሰጧቸው መብቶች ለተገደበ የአገልግሎታችንን ማሰራት፣ ማስተዋወቅ እና ማሻሻል፣ እና እንዲሁም አዳዲስ አገልግሎቶችን የመቅረጽ ዓላማ ብቻ ጥቅም የሚውሉ ብቻ ናቸው። አንተ የሰጠኸን ፈቃድ አገልግሎቶቻችንን መጠቀም ብታቆም እንኳ (ለምሳሌ፣ ወደ Google ካርታዎች ያከልከው የንግድ ስራ ዝርዝር) ጸንቶ ይቀጥላል። በአንዳንድ አገልግሎቶችቻችን ላይ ያሉት ደንቦች ለአገልግሎቱ ያቀረብከውን መረጃ በቀጥታ እንድታገኘው እና ከፈለግክም እንድታነሳው/እንድታስወግደው አማራጭ መንገዶችን ይሰጡሃል። በተጨማሪም፣ በአንዳንድ አገልግሎቶቻችን ላይ የሚገኙት ደንቦችእና የአጠቃቀም መንገዶች አገልግሎቶቹን ስትጠቀም በምታቀርበው/በምትሰጠው መረጃ ላይ ያለንን የመጠቀም መብት የሚገድቡ ወይም የሚያጠቡ ናቸው። ወደ አገልግሎቶቻችን ለሚያስገቡት ማንኛውም ይዘት ይህን ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችሉ አስፈላጊዎቹ መብቶች እንዳሉዎት እርግጠኛ ይሁኑ።
በራስ-ሰር የሚሰሩ ስርዓቶቻችን እንደ ብጁ የፍለጋ ውጤቶች፣ የተበጁ ማስታወቂያዎች እና የአይፈለጌ መልዕክት እና የተንኮል-አዘል ዌር ማወቅ ያሉ በግል ለእርስዎ ተገቢ የሆኑ ባህሪያትን ለማቅረብ ይዘትዎን (ኢሜይሎችም ጭምሮ) ይተነትናሉ። ይህ ትንታኔ የሚከሰተው ይዘቱ ሲላክ፣ ሲደርስ ወይም ሲከማች ነው።
የGoogle መለያ ከአለዎት የእርስዎን የመገለጫ ስም፣ የመገለጫ ፎቶ እና በGoogle ወይም ከእርስዎ የGoogle መለያ ጋር በተገናኙ የሶስተኛ ወገን መገግበሪያዎች ላይ የሚወስዷቸውን እንቅስቃሴዎች (እንደ+1 ዎች፣ የጻፏቸው ግምገማዎች እና የለጠፏቸው አስተያየቶችን) ማስታወቂያዎች እና በሌሎች ንግድ ነክ አገባቦችን ጨምሮ በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ልናሳያቸው እንችላለን። በእርስዎ Google መለያ ውስጥ ማጋራትን ለመገደብ ያደረጉትን ምርጫ እና የታይነት ደረጃ ቅንብሮችዎን እናከብራለን። ለምሳሌ፣ የእርስዎ ስም እና ፎቶ በማስታወቂያዎች ውስጥ እንዳይታዩ አድርገው ቅንብሮችዎን መምረጥ ይችላሉ።
Google እንዴት ይዘትን እንደሚጠቀም እና እንደሚያከማች፣ እንዲሁም በተወሰኑ አገልግሎቶች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ተጨማሪ የውል ግዴታዎችን በተመለከተ ከGoogle የግላዊነት ፖሊሲ የበለጠ መረጃ ማግኘት ትችላለህ። ስለአገልግሎቶቻችን ግብረመልስ ወይም አስተያየት ከሰጠህ፣ ግብረመልስህን ወይም አስተያየትህን ያለፈቃድህ ልንጠቀምበት እንችላለን።
በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ስለሚገኝ ሶፍትዌር
አንድ አገልግሎትን ለመጠቀም ከድረገጽ የሚገኝ የሚወርድ ሶፍትዌር የሚያስፈልግ ከሆነ ወይም ሶፍትዌሩ በአገልግሎቱ ውስጥ የተካተተ እንደሆነ፣ በሶፍትዌሩ ላይ ማሻሻያ ከተደረገበት ወይም አዳዲስ ይዘቶች ሲኖሩት ሶፍትዌሩ ራሱን በራሱ ሊያሻሽል ይችላል። አንዳንድ አገልግሎቶች ደግሞ እንዲህ አይነት አውቶማቲክ የማሻሻል ሁኔታችን እንድታስትካክል ይፈቅዱልሃል።
የGoogleአገልግሎት አካል የሆነን ሶፍትዌር በሚመለከት፣ ዓለምአቀፍ፣ ከባለቤትነት ክፍያ ነጻ የሆነ፣ ለሌላ ተላልፎ የማይሰጥ እና ምንም ገደብ የሌለበት በሶፍትዌሩ በግል የመጠቀም ፈቃድ Google ይሰጥሃል። ይህ ፈቃድ ብቸኛ ዓላማው በGoogle የሚሰጡ አገልግሎቶችን በውስጣቸው ያሉት ውሎች በሚፈቅዱት መሰረት እንድትጠቀምባቸው ለማስቻል ነው። ነገር ግን ማናቸውንም የአገልግለቶቻችን አካል የሆነን ወይም በሶፍትዌሩ የተካተተ ነገርን መቅዳት፣ ማሻሻል፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወይም ማከራየት አትችልም እንዲሁም ገደቦቹን ሕግ ካልፈቀደ በቀር ወይም ከኛ በጽሑፍ የተሰጠ ፈቃድ ከሌለህ በቀር ሶፍትዌሩን ወደ ኋላ መልሶ የመስራት ምህንድስና (reverse engineering) ወይም የምንጭ ኮዱን ለማውጣት መሞከር አትችልም።
የክፍት ምንጭ ሶፍትዌር ለኛ በጣም አስፈላጊ ነው። በኛ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ የዋሉ አንዳንድ ሶፍትዌሮች እኛ እንድታገኘው በምናደርገው የክፍት ምንጭ ፈቃድ አማካይነት ሊቀርቡ ይችላሉ። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በፈቃዱ ላይ ያሉት ድንጋጌዎች ከላይ የጠቀስናቸውን የአገልግሎት ደንቦች የሚሽሩ ሊሆኑ ይችላሉ።
አገልግሎቶቻችንን ማሻሻል ወይም ማቋረጥ
አገልግሎቶቻችንን በየጊዜው በወጥነት እየለወጥን እና እያሻሻልን ነው። አንዳንድ አጠቃቀሞችን እና የአጠቃቀም መንገዶችንና መሳሪያዎችንልናክል ወይም ልናስወግድ እንችላለን፣ እንዲሁም አንድን አገልግሎት ለተወሰነ ጊዜ ልናግድ ወይም ሙሉ በመሉ ልናቆም እንችላለን።
ምንም እንኳን ስትለየን ቅር ቢለንም፣ በፈለግከው ጊዜ አገልግሎቶቻችንን መጠቀም ማቋረጥ ትችላለህ። Googleም ላንተ አገልግሎቶችን መስጠቱን ሊያቋርጥ፣ ወይም በማናቸውም ጊዜ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ አዳዲስ ገደቦችን ሊጥል ይችላል።
የራስህ ውሂብ ባለቤት አንተው እንደመሆንህ፣ መረጃዎችህን የማግኘት መብትህን ማስጠበቅ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን። አንድን አገልግሎት ካቋረጥን፣ አቅም በፈቀደ መጠን፣ በቅድሚያ ማሳሰቢያ እንዲደርስህ እናደርጋለን እናም ከአገልግሎትም መረጃ የማግኘት ዕድል እንዲኖርህ እናደርጋለን።
የዋስትና ማረጋገጫችን እና ማሳሰቢያዎቻችን
አገልግሎቶቻችንን በንግዱ ዓለም በሚጠበቀው የብቃት እና ጥንቃቄ ደረጃ እንሰጣለን፣ እናም በነርሱ መጠቀሙን አስደሳች ሆኖ ታገኘው ዘንድ ምኞታችን ነው። ነገር ግን ስለአገልግሎቶቻችንን ቃል ልንገባባቸው የማናችለው አንዳንድ ነገሮቸ አሉ።
በነዚህ የውል ድንጋጌዎች/ደንቦች ወይም በተጨማሪ የውል ቃሎች በግልጽ ካልተቀመጠ በቀር፣ GOOGLEም ሆነ አቅራቢዎቹ ወይም አከፋፋዮች ስለአገልግሎቶቹ የሚሰጡት ዝርዝር ዋስትና የለም። ለምሳሌ፣ በአገልግሎቶቹ ያለውይ ይዘት/መረጃ በሚመለከት፣ አገልግሎቶቹ መስራታቸውን/በስራ ላይ መዋል መቻላቸውን አስተማማኝነታቸውን፣ አገልግሎቶቹን ማቅረብ መቻላችንን ወይም ፍላጎትህን ለማሟላት ስላለው ብቃት ምንም ዓይነት ዋስትና አንሰጥም። አገልግሎቶቻችንን «እንዳሉ/ባሉበት ሁኔታ» ብቻ እናቀርባለን።
በአንዳንድ ሀገሮች ያሉ ህጎች፣ እንደ ገበያ ላይ የመዋል ብቃት ፣ ለተወሰነ ዓላማ ወይም አገልግሎት ብቁ መሆንን እና አገልግሎቱ የአእምሯዊ መብቶችን የማይጥስ መሆኑን የመሳሰሉ በሚመለከት ዋቢነት/ዋስትና እንዲሰጥ ያዛሉ። በሕግ እስከሚፈቅደው ድረስ ለአገልግሎቱ ዋስትና/መድን አንሰጥም።
ከአገልግሎቶቻችን ጋር የተያያዘ የህግ ኃላፊነት
ሕጉ በፈቀደ መጠን፣ GOOGLE፣ እና የGOOGLE አቅራቢዎች እና አከፋፋዮች፣ ለጠፋ ትርፍ፣ ለታጣ ገቢ ወይም መረጃ እንዲሁም የገንዘብ ኪሳራ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ፣ ልዩ፣ አንድን ጉዳት ተከትሎ በመጣ ሌላ ጉዳት ኃላፊ አይሆንም፣ በተጨማሪም በቅጣት ወይም በማስተማሪያነት በሚከፈል ካሳ ምክንያት ለሚመጣ ጉዳት ተጠያቂ አይሆኑም።
ሕጉ በሚፈቅደው መጠን፣ በህግ/በውስጠ ታዋቂ ለአግልግሎቱ የሚሰጥ ዋስትናን ጨምሮ ከላይ በተጠቀሱት የውል ድንጋጌዎች መሰረት ለሚቀርብ ክስ GOOGLE፣ አቅራቢዎቹ እና አከፋፋዮቹ ፣ያለባቸው ኃላፊነት፣ አገልግሎቶቹን ለመጠቀም ከከፈልከው ገንዘብ የማይበልጥ ካሳ መክፈል /ወይም እኛ ከመረጥን አገልግሎቱን በድጋሚ ለአንተ ማቅረብ/ ይሆናል።
በማናቸውም ሁኔታ GOOGLE፣ አቅራቢዎቹ እና አከፋፋዮቹ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ አስቀድሞ ሊገመት ለማይችል ማናቸውም ኪሳራ ወይም ጉዳት ተጠያቂ አይሆኑም።
የአገልግሎቶቻቸንን ንግድ ነክ አጠቃቀም
አገልግሎቶቻችንን በአንድ የንግድ ተቋም ስም የምትጠቀም ከሆነ፣ የንግድ ተቋሙም እነዚህን ውሎች እንደተቀበላቸው ይቆጠራል። በአገልግሎቶች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለሚነሳ ማናቸውም አቤቱታ፣ ክስ ወይም እርምጃ ወይም እንዲሁም እነዚህን ውሎች ባለማክበር፣ ማለትም ከአቤቱታዎች፣ ከኪሳራዎች፣ ጉዳቶች፣ ክሶች፣ ፍርዶች፣ የፍርድቤት ወጪዎች እና የጠበቃዎች ክፍያዎችን ጨምሮ ለሚነሳ ተጠያቂነት ተቋሙ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ለGoogle እና ተባባሪዎቹ፣ ሃላፊዎቹ፣ ወኪሎቹ እና ሰራተኞቹ በመሉ ዋስትና እና ማረጋገጫ ይሰጣል።
ስለነዚህ ውሎች
እነዚህን የውል ድንጋጌዎችም ሆነ እና በተጨማሪ በአገልግሎቱ ላይ ተፈጻሚነት ያላቸውን ሌሎች የውል ድንጋጌዎች፣ ለምሳሌ ህግ በሚለወጥበት ወይም አገልግሎቶቻችን በሚሻሻሉበት/በሚቀየሩበት ጊዜከለውጦቹ ጋር ለማጣጣም ልናሻሽላቸው እንችላለን። ውሎቹን በየጊዜው ልትምለከታቸው ይገባል። በነዚህ ደንቦች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን በሚመለከት ማሳሰቢያዎችን በዚህ ገጽ እንለጥፋለን። የተሻሻሉ ተጨማሪ ደንቦችን በተመለከተ አገልግሎት ላይ ማሳሰቢያ እንለጥፋለን። ለውጦቹ ወደኋላ ሄደው ተፈጻሚ የማይደረጉ ሲሆን፣ ከተለጠፉበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አራት ቀናት ውስጥ ተፈጻሚ አይሆኑም። ሆኖም ግን፣ አንድ አገልግሎት አዲስ ተግባር ሲኖረው ይህን የተመለከቱ ለውጦች ወይም በሕግ ምክንያት የተደረጉ ለውጦች ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናሉ። በአንድ አገልግሎት ላይ የተሻሻሉ ደንቦችን የማትስማማባቸው ከሆነ፣ አገልግሎቱን መጠቀም ማቆም አለብህ።
በነዚህ የውል ድንጋጌዎች እና በተጨማሪነት በሚወጡ ድንጋጌዎች መካከል ግጭት የሚኖር ከሆነ፣ ግጭቱ በተጨማሪነት በወጡት ድንጋጌዎች መሠረት እንዲፈታ ይደረጋል።
እነዚህ የውል ድንጋጌዎች የሚገዙት በGoogle እና ባንተ መካከል ያለውን ግንኙነት ነው። ስለሆነም ለሶስተኛ ወገኖች ምንም ዓይነት የተጠቃሚነት መብቶችን አይሰጡም።
በነዚህ ድንጋጌዎች የማትገዛ ከሆነ እና ጥሰት ስትፈፅም እርምጃ ወዲያውኑ ሳንወስድ ብንቀር፣ እርምጃ ባለባለመውሰዳችንን ያለንን ማንኛውንም መብት (ለምሳሌ ወደፊት እርምጃ ለመውሰድ) ያለ መብት አሳልፈን ሰጥተናል ወይም ትተናል ማለት አይደለም።
ከውል ድንጋጌዎቹ መካከል አንዱ የማይጸና/ተፈጻሚነት የማይኖረው ቢሆን ይህ በሌሎቹ የውል ድንጋጌዎቹ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖም አይኖርም።
የአለም አቀፍ የግለሰብ ህግን/የህጎች ግጭትን ከሚመለከቱ ጉዳዮች በስተቀር ከነዚህ የውል ድንጋጌዎች ወይም በአገልግሎቶች የሚነሳን ማናቸውም አለመግባባት/ክስ ላይበአሜሪካን የካሊፎርኒያ ግዛት ህጎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ከነዚህ ውሎች ወይም አገልግሎቶች የሚነሱ ማናቸውም ክሶችና አቤቱታዎች በካሊፎርኒያ የሚገኘው የሳንታ ክላራ ካውንቲ የፌደራል ወይም የክልልፍርድ ቤቶች ብቻ የሚታይ ሲሆን በዚህ ጉዳይ እነዚህ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ስልጣን አንተ እና Google እንደተስማማችሁ ታረጋግጣላችሁ።
Googleን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል መረጃ ለማግኘት፣ እባክህ የኛን የመገኛ ገጽ ጎብኝ።