ይሄ በማህደር የተቀመጠው የአገልግሎታችን ስሪት ነው። የአሁኑን ስሪት ወይም ሁሉም ያለፉ ስሪቶችን ይመልከቱ።

የGoogle የአገልግሎት ውል ስምምነት

ውጤታማ 31 ማርች 2020 | የታቆሩ ስሪቶች | ፒዲኤፍ አውርድ

በእነዚህ ውሎች ምን ሽፋን እንዳገኘ

ይህን የአገልግሎት ውል መዝለል እንደሚያምረዎት እናውቃለን፣ ነገር ግን እርስዎ የGoogle አገልግሎቶችን በመጠቀምዎ ከእኛ ምን መጠበቅ እንደሚችሉ፣ እና እኛ ከእርስዎ ምን እንደምንጠብቅ ማወቁ አስፈላጊ ነው።

እነዚህ የአገልግሎት ውሎች የGoogle ንግድ ሥራዎች እንዴት እንደሚከናወኑ፣ በእኛ ኩባንያ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ሕጎች እና እኛ ሁልጊዜ እውነት ናቸው ብለን የምናምንባቸውን የተወሰኑ ነገሮች ያንጸባርቃሉ። በመሆኑንም እርስዎ ከእኛ አገልግሎቶች ጋር መስተጋብር በሚፈጽሙበት ጊዜ Google ከእርስዎ ጋር ያለውን ዝምድና ለመበየን እንዲቻል እነዚህ የአገልግሎት ውሎች ያግዛሉ። ለምሳሌ፣ እነዚህ ውሎች የሚከተሉትን የርዕሰ ጉዳይ አርዕስቶች ያካትታሉ፦

አገልግሎቶቻችንን በመጠቀምዎ በእነዚህ ደንቦች እንደተስማሙባቸው ስለሚቆጠር ደንቦቹን መረዳት አስፈላጊ ነው።

ከእነዚህ ደንቦች በተጨማሪም እንዲሁም የግላዊነት መመሪያን እናትማለን። ምንም እንኳ የእነዚህ ደንቦች አካል ባይሆንም እንዴት መረጃዎን ማዘመን፣ ማቀናበር፣ ወደ ውጭ መላክ እና መሰረዝ እንደሚችሉ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እንዲያነብቧቸው እናበረታታዎታለን።

የአገልግሎት አቅራቢ

Google አገልግሎቶች የሚቀርቡት እና እርስዎ ውል ላይ እየገቡ ያሉት፦

Google LLC
በዴላዌር ግዛት፣ አሜሪካ፣ ህጎች እና መሠረት የተደራጀ እና በአሜሪካ ህጎች መሠረት የሚሠራ

1600 Amphitheatre Parkway
Mountain View, California 94043
አሜሪካ

የዕድሜ መስፈርቶች

እርስዎ የእርስዎን የGoogle መለያ ለማስተዳደር የሚያስፈልገው ዕድሜ በታች ከሆኑ፣ የGoogle መለያ ለመጠቀም የእርስዎ ወላጅ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት ፈቃድ ሊኖርዎት ይገባል። የእርስዎ ወላጅ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት እነዚህን ውሎች ከእርስዎ ጋር እባክዎ እንዲያነቡዋቸው ያድርጉዋቸው።

እርስዎ ወላጅ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት ከሆኑ እና የእርስዎ ልጅ አገልግሎቶቹን እንዲጠቀም ከፈቀዱለት፣ እነዚህ ውሎች በእርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ እንዲሁም የእርስዎ ልጅ በእነዚህ አገልግሎቶች ላይ ለሚኖረው እንቅስቃሴ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ።

አንዳንድ የGoogle አገልግሎቶች በእነርሱ አገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች እና መመሪያዎች ላይ በተብራራው መሠረት ተጨማሪ የዕድሜ መስፈርቶች አሏቸው።

ከGoogle ጋር የእርስዎ ግንኙነት

እነዚህ ውሎች በእርስዎ እና በGoogle መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግለጽ ያግዛሉ። ሰፋ ባለ አነጋጋር፣ የእኛን አገልግሎቶች እንዴት Google የንግድ ሥራ እንደሚሠራ እና እንዴት እኛ ገንዘብ እንደምናገኝ የሚያንጸባርቁትን እነዚህን ውሎች ለማክበር ከተስማሙ ለእርስዎ ፈቃድ እንሰጥዎታለን። «Google»፣ «እኛ»፣ «እኛን» እና «የእኛ» ስንል Google LLC እና የእሱ አጋሮች ማለታችን ነው።

ከእኛ ምን መጠበቅ እንደሚችሉ

ጠቃሚ የሆኑ አገልግሎቶችን በሰፋት ማቅረብ

በእነዚህ ውሎች ተገዢ የሆኑ የሚከተሉትን የሚያካትቱ መጠነ ሰፊ አገልግሎቶችን እናቀርባለን፦

  • ካርታዎች እና ጣቢያዎች (እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች)
  • መድረኮች (እንደ Google Play)
  • የተቀናጁ አገልግሎቶች (እንደ ካርታዎች የመሳሰሉ በሌሎች ኩባንያዎች መተግበሪያዎች ወይም ጣቢያዎች ላይ የተካተቱ)
  • መሣሪያዎች (እንደ Google Home)

የእኛ አገልግሎቶች አንድ ላይ እንዲሠሩ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው፣ በዚህም ከአንድ እንቅስቃሴ ወደ ቀጣዩ ለእርስዎ መንቀሳቀስን ቀላል ያደርጋሉ። ለምሳሌ፣ ካርታዎች በእርስዎ የGoogle ቀን መቁጠሪያ ላይ ለሚታይ ቀጠሮ እንዲሄዱ ሊያስታውስዎት ይችላል።

የGoogle አገልግሎቶችን ያሻሽሉ

አገልግሎቶቻችንን ለማሻሻል አዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ባህሪያትን በቋሚነት እየገነባን ነው። ለምሳሌ፣ አይፈለጌ መልዕክትን እና ተንኮል-አዘል ዌርን ለማግኘትና ለማገድ፣ እና እንደ ትይዩ ትርጉሞች ያሉ የፈጠራ ባህሪያትን ለእርስዎ ለማቅረብ ማሽን መማርን የሚጠቀም ሰው ሰራሽ ብልሃት ላይ መዋዕለ ነዋይ እናፈስሳለን። እንደ የዚህ ቀጣይነት ያለው መሻሻል አካል አንዳንድ ጊዜ ባህሪያትን እና ተግባራትን እናክላለን ወይም እናስወግዳለን፣ የአገልግሎቶቻችን ገደቦች እንጨምራለን ወይም እንቀንሳለን፣ እና አዲስ አገልግሎቶችን ማቅረብ እንጀምራለን ወይም የድሮዎቹን ማቅረብ እናቆማለን።

የእርስዎን በእኛ አገልግሎቶች ላይ ያለ አጠቃቀም በከፍተኛ ደረጃ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ተጨባጭ ለውጦችን ካደረግን ወይም አገልግሎትን መስጠት ካቆምን፣ በቂ ጊዜ ያለው በቅድሚያ የተሰጠ ማስታወቂያ እና የእርስዎን ይዘት ከእርስዎ የGoogle መለያ Google Takeoutን በመጠቀም፣ እንደ አላግባብ መጠቀምን ለመከላከል፣ ሕጋዊ ግዴታዎችን ከመወጣት ወይም ደህንነት እና የክወና ችግሮችን መፍትሔ መስጠት ካልሆነ በቀር ወደ ውጭ ለመላክ የሚችሉበትን ዕድል እንሰጥዎታለን።

ከእርስዎ እኛ ምን እንደምንጠብቅ

እነዚህን ደንቦች እና አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦችን ይከተሉ

እርስዎ በሚከተሉት ውስጥ ያሉብዎትን የእርስዎን ኃላፊነቶች እስከተወጡ ድረስ የእኛን አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ የምንሰጥዎት ፈቃድ ቀጣይነት ይኖረዋል፦

የተለመዱ ጥያቄዎችን መልስ ለመስጠት እና የእኛን አገልግሎቶች በመጠቀም ምን መጠበቅ እንደሚቻል ለመወሰን የተለያዩ መመሪያዎችን፣ የእገዛ ማዕከላትን እና ሌላ ግብዓቶችን ለእርስዎ አዘጋጅተን እንዲያገኟቸው እናደርጋለን። እነዚህ ግብዓቶች የግላዊነት መመሪያ፣ የቅጂ መብት የእገዛ ማዕከል፣ የደህንነት ማዕከል፣ እና ሌላ ከእኛ የመመሪያዎች ጣቢያ ሊደረስባቸው የሚችሉ ገጾችን ያካትታሉ።

ምንም እንኳ አገልግሎቶቻችንን እንዲጠቀሙ ፈቃድ ብንሰጠዎትም በአገልግሎቶቹ ውስጥ ያሉን ማናቸውም የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እንደያዝን እናቆያለን።

ሌሎችን ያክብሩ

አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን እርስዎ ከሌሎች ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያስችሉዎታል። ለሁሉም ሰው መከባበር ያለበት አካባቢ ማቆየት እንፈልጋለን፣ ይህ ማለት እርስዎ እነዚህን መሠረታዊ የስነ ምግባር ደንቦች መከተል አለብዎት ማለት ነው፦

  • ወደ ውጭ መላኪያ ቁጥጥር፣ ማዕቀቦች እና የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ህጎችም ጨምሮ የሚመለከታቸውን ህጎች ማክበር
  • የግላዊነት እና የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ጨምሮ የሌሎች መብቶችን ማክበር
  • ሌሎች ወይም ራስዎን መበደል ወይም መጉዳት (ወይም እንዲህ ያለ መበደል ወይም ጉዳት ማስፈራራት ወይም ማበረታታት) — ለምሳሌ፣ ሌሎችን በማሳሳት፣ በማጭበርበር፣ ስም በማጥፋት፣ በመተናኮስ ወይም በመከታተል
  • አገልግሎቶቹን አላግባብ አይጠቀሙ፣ አይጉዱ፣ በእነሱ ጣልቃ አይግቡ ወይም አያቋርጡ

የእኛ አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች እና መመሪያዎች ስለ ተገቢነት ያለው ምግባር እነዚያን አገልግሎቶች የሚጠቀም ማንኛውም ሰው መከተል አለበት ተጨማሪ ዝርዝሮችን ያቀርባሉ። ሌሎች እነዚህን ደንቦች እየተከተሉ አለመሆናቸውን ሲያገኙ ፣አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን አላግባብ መጠቀምን ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስችሉዎታል። አላግባብ መጠቀም ላይ ሪፖርት ሲደረግ እርምጃ ከወሰድን በችግሮች ሲያጋጥሙ እርምጃ መውሰድ ክፍል ውስጥ እንደተብራራው ፍትሐዊ የሆነ የማጣራት ሂደትን እናቀርባለን።

ይዘትዎን የመጠቀም ፈቃድ

አንዳንድ አገልግሎቶቻችን እርስዎ ይዘትዎን እንዲሰቅሉ፣ እንዲያስገቡ፣ እንዲያከማቹ፣እንዲልኩ፣ እንዲቀበሉ ወይም እንዲያጋሩ ለማስቻል የተነደፉ ናቸው። ማንኛውም ይዘት ወደ አገልግሎቶቻችን የማቅረብ ግዴታ የለብዎትም፣ እና ለማቅረብ የሚፈልጉትን ይዘት ለመምረጥ ነፃ ነዎት። ይዘትን ለመስቀል ወይም ለማጋራት ከመረጡ እባክዎ ይህን የማድረግ አስፈላጊዎቹ መብቶች እንዳለዎትና ይዘቱ ህጋዊ መሆኑን ያረጋግጡ።

ፈቃድ

የእርስዎ ይዘት የእርስዎ እንደሆነ ይዘልቃል፣ ይህም ማለት በእርስዎ ይዘት ውስጥ እርስዎ ሊኖርዎት የሚችሉ ማናቸውንም የአእምሯዊ ንብረት መብቶች እንደያዙ ይቀጥላሉ ማለት ነው። ለምሳሌ፣ እንደ እርስዎ የሚጽፏቸው ግምገማዎች በመሳሰሉ እርስዎ የሚፈጥሩት የፈጠራ ይዘት ውስጥ ያሉ እርስዎ ያለዎት አእምሯዊ ንብረት መብቶች። ወይም እነርሱ ፈቃድ ለእርስዎ ከሰጡዎት የሌላ ሰውን የፈጠራ ይዘት ለማጋራት መብት አለዎት።

የአዕምሯዊ ንብረት መብቶችዎ የይዘትዎ አጠቃቀማችንን የሚገድቡ ከሆነ ፈቃድዎ ያስፈልገናል። በዚህ ፈቃድ በኩል ይህን ፈቃድ ለGoogle ይሰጡታል።

ምን ሽፋን እንዳገኘ

የእርስዎ ይዘት በአዕምሯዊ ንብረት መብቶች የተጠበቀ ከሆነ ይህ ፈቃድ ለየእርስዎ ይዘት ሽፋን ይሰጣል።

ምንድነው ያልተሸፈነው

  • ይህ ፈቃድ የእርስዎ የግላዊነት መብቶች ላይ ተጽዕኖ አያሳርፍም — ሾለ የእርስዎ የአእምሯዊ ንብረት መብቶች ብቻ የሚመለከት ነው
  • ይህ ፈቃድ እንደዚህ ዓይነቶቹን ይዘት ሽፋን አይሰጥም፦
    • ለአካባቢ ንግድ ሼል አድራሻ እርማቶች የመሳሰሉ እርስዎ የሚያቀርቡት በይፋ ሊታይ የሚችል ተጨባጭ መረጃ። ያ መረጃ ሁሉም ሰው ለመጠቀም ነፃ ነው ተብሎ እንዲሁ ስለሚታመን ፈቃድ አያስፈልገውም።
    • የእኛን አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚያቀርቧቸው ሐሳቦች የመሳሰሉ እርስዎ የሚሰጡት ግብረመልስ ግብረመልስ ከአገልግሎት ጋር የተገናኙ የመልዕክት ልውውጦች የሚለው ከዚህ በታች ባለው ክፍል ውስጥ ሽፋን ተሰጥቶታል።

ወሰን

ይህ ፈቃድ እንደሚከተለው ነው፦

  • ዓለም አቀፍ፣ ይህም ማለት በየትኛውም ዓለም የሚሠራ ነው
  • ማንንም አያገልም፣ ይህም ማለት የእርስዎን ይዘት ፈቃድ ለሌሎች አሳልፈው መስጠት ይችላሉ
  • ከባለቤትነት ክፍያ ነፃ፣ ይህም ማለት ለዚህ ፈቃድ የሚከፈሉ ምንም ክፍያዎች የሉም

መብቶች

ይህ ፈቃድ Google የሚከተለውን እንዲያደርግ ይፈቅድለታል፦

  • ይዘትዎን ማስተናገድ፣ ማባዛት፣ ማሰራጨት፣ ለሌላ ማሳወቅ እና መጠቀም — ለምሳሌ፣ ይዘትዎን በስርዓቶቻችን ላይ ለማስቀመጥና እርስዎ ከሄዱበት ቦታ ሁሉ ተደራሽ ለማድረግ
  • ያትሙ፣ በይፋ ያከናውኑ ወይም በይፋ የእርስዎን ይዘት ያሳዩ፣ ለሌሎች እንዲታይ ያደርጉት እንደሆነ
  • እንደ ዳግም ቅርጸት ወይም መተርጎም የመሳሰለ በእርስዎ ይዘት ላይ በመመርኮዝ የተሠሩ ሥራዎችን ማሻሻል እና መፍጠር
  • እነዚህን መብቶች ለሚከተለው እንደገና አሳልፈህ ስጥ፦
    • ሌሎች ተጠቃሚዎች አገልግሎቶቹ እንደታሰቡት እንዲሠሩ ለማድረግ እንዲፈቅዱ፣ ለምሳሌ እርስዎ ከመረጡዋቸው ሰዎች ጋር ፎቶዎችን ማጋራት እንዲችሉ ማብቃት
    • ከእነዚህ ደንቦች ጋር ወጥ የሆኑ ስምምነቶችን ከእኛ ጋር የተፈራረሙ ተዋዋዮቻችን፣ ከታች ባለው የዓላማ ክፍል ላይ ለተገለጹት የተወሰኑ ዓላማዎች ብቻ ነው።

ዓላማ

ይህ ፈቃድ ለሚከተለው ዓላማ የተወሰነ ነው፦

  • አገልግሎቶቹን ማንቀሳቀስ እና ማሻሻል፣ ይህም ማለት አገልግሎቶቹ እንደታሰቡት እንዲሠሩ መፍቀድ እና አዳዲስ ባህሪያትን ወይም ተግባራትን መፍጠር ማለት ነው። ይህ የእርስዎን ይዘት ለመተንተን ልሾሰር ሥርዓቶችን እና ስልተ ቀመሮቸን መጠቀምን ያካትታል፦
    • ለአይፈልጌ መልዕክት፣ ተንኮል-አዘል ዌር፣ እና ሕገወጥ ይዘት
    • እንደ በGoogle ፎቶዎች ውስጥ ተዛማጅ ፎቶዎችን አብሮ ለማስቀመጥ መቼ አዲስ አልበም እንደሚሰራ መወሰን ያሉ በውሂብ ውስጥ ያሉ ስርዓተ-ጥለቶችን ማወቅ
    • እንደ ምክሮችን እና ግላዊነት የተላበሱ የፍለጋ ውጤቶችን፣ ይዘትን እና ማስታወቂያዎችን ማቅረብ ያሉ አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ ለማበጀት (ይህም በየማስታወቂያዎች ቅንብሮች ውስጥ መቀየር ወይም ማጥፋት ይችላሉ)
    ይህ ትንታኔ የሚከሰተው ይዘቱ ሲላክ፣ ሲደርስ ወይም ሲከማች ነው።
  • አገልግሎቶቹን ለማስተዋወቅ እርስዎ በይፋ ያጋሩትን ይዘት በመጠቀም። ለምሳሌ፣ የGoogle መተግበሪያን ለማስተዋወቅ፣ እርስዎ የጻፉትን ግምገማ ልንጠቅስ እንችል ይሆናል። ወይም Google Playን ለማስተዋወቅ፣ በPlay መደብር ውስጥ እርስዎ የሚያቀርቡትን መተግበሪያ ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታ ልናሳይ እንችል ይሆናል።
  • ከእነዚህ ደንቦች ጋር ወጥ በሆነ መልኩ ለGoogle አዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አገልግሎቶችን መገንባት

የቆይታ ጊዜ

ይህ ፈቃድ የእርስዎ ይዘት በአዕምሯዊ ንብረት መብቶች የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ ይዘልቃል።

በዚህ ፈቃድ ሽፋን ያለውን ማናቸውንም ይዘት ከእኛ አገልግሎቶች ካስወገዱ፣ የእኛ ሥርዓቶች ያንን ይዘት አግባብነት ባለው ጊዜ ልዩነት ውስጥ በይፋ የማይገኝ እንዳይሆን ያደርጋሉ። ሁለት እዚህ ላይ የማይካተቱ ሁኔታዎች አሉ፦

  • ይዘትዎን ከማስወገድዎ በፊት አስቀድመው ለሌሎች ካጋሩት። ለምሳሌ፣ አንድ ፎቶ ለጓደኛ ካጋሩና ይህ ጓደኛ የእሱን ቅጂ ከሰሩ ወይም ዳግም ካጋሩት ይህ ፎቶ በጓደኛዎ የGoogle መለያ ላይ መታየቱ ሊቀጥል ይችላል፣ ከGoogle መለያዎ ቢያስወግዱትም እንኳ።
  • በሌሎች ኩባንያዎች አገልግሎቶች በኩል የእርስዎን ይዘት እንዲገኝ ካደረጉ፣ Google ፍለጋን ጨምሮ የፍለጋ ሞተሮች እንደ የእነርሱ የፍለጋ ውጤቶች የእርስዎን ይዘት ማግኘታቸውን እና ማሳየታቸውን መቀጠል የመቻል ዕድል አላቸው።

የGoogle አገልግሎቶችን መጠቀም

የGoogle መለያህ

እነዚህን የዕድሜ መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆነ ለእርስዎ ምቾት ሲባል የGoogle መለያ መፍጠር ይችላሉ። አንዳንድ አገልግሎቶች እንዲሠሩ እርስዎ የGoogle መለያ እንዲኖርዎት ይጠይቃሉ — ለምሳሌ፣ Gmailን ለመጠቀም፣ የእርስዎን ኢሜይል ለመላክ እና ለመቀበል የሚችሉበት ቦታ እንዲኖርዎት የGoogle መለያ እንዲኖርዎት ያስፈልጋል።

በእርስዎ የGoogle መለያ ላይ የእርስዎን የGoogle መለያ ደህንነቱ እንዲጠበቅ ለማድረግ አግባብነት ያላቸውን እርምጃ መውሰድ ጨምሮ ኃላፊነቱን እርስዎ ይወስዳሉ እና የደህንነት ፍተሻን በመደበኛነት እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን።

አንድ ድርጅትን በመወከል የGoogle አገልግሎቶችን መጠቀም

እንደ ንግዶች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ እና ትምህርት ቤቶች ያሉ ብዙ ድርጅቶች የእኛን አገልግሎቶች ይጠቀሙባቸዋል። አንድ ድርጅትን በመወከል የእኛን አገልግሎቶች ለመጠቀም፦

  • ፈቀዳ ያለው የዚህ ድርጅት ተወካይ በእነዚህ ደንቦች መስማማት አለበት
  • የድርጅትዎ አስተዳዳሪ አንድ የGoogle መለያን ለእርስዎ ሊመደብ ይችላል። ይህ አስተዳዳሪ እርስዎ ተጨማሪ ደንቦችን እንዲከተሉ ሊፈለግብዎ እና የGoogle መለያዎን ሊደርሱ ወይም ሊያሰናክሉ ይችላሉ።

አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ ለማቅረብ አንዳንድ ጊዜ የአገልግሎት ማስታወቂያዎችን እና ሌላ መረጃን ልንልክልዎ እንችላለን። እኛ ከእርስዎ ጋር እንዴት መልዕክት እንደምንለዋወጥ የበለጠ ለመረዳት የGoogle ግላዊነት መመሪያን ይመልከቱ።

እንደ አገልግሎቶቻችንን ለማሻሻል ያሉ የአስተያየት ጥቆማዎች ያለ ግብረመልስ ለእኛ ለመስጠት ከመረጡ ለእርስዎ ምንም ግዴታ ሳይኖርብን በግብረመልስዎ ላይ ተመርስተን እርምጃ ልንወስድ እንችላለን።

በGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ያለ ይዘት

የእርስዎ ይዘት

የእኛ አንዳንድ አገልግሎቶች የእርስዎን ይዘት በይፋ የሚገኝ እንዲሆን ለማድረግ እንዲችሉ ዕድሉን ይሰጥዎታል — ለምሳሌ፣ እርስዎ የጻፉትን የምርት ወይም የምግብ ቤት ግምገማ መለጠፍ ወይም እርስዎ የፈጠሩትን የጦማር ልጥፍ መስቀል ይችሉ ይሆናል።

የሆነ ሰው የእርስዎን አዕምሯዊ ንብረት መብቶች እየጣሰ እንደሆነ ካሰቡ የጥሰቱን ማሳወቂያ ይላኩልን እና አግባብ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን። ለምሳሌ፣ በእኛ የቅጂ መብት እገዛ ማዕከል ላይ እንደተገለጸው የተደጋጋሚ የቅጂ መብት ጣሺዎች Google መለያዎችን እናግዳለን ወይም እንዘጋለን።

የGoogle ይዘት

የእኛ አንዳንድ አገልግሎቶች ለምሳሌ በGoogle ካርታዎች ውስጥ የሚያዩዋቸው አብዛኛዎቹ የሚታዩ ሥዕሎች — ንብረትነቱ የGoogle የሆነ ይዘትን ያካትታሉ። የGoogle ይዘትን በእነዚህ ውሎች እና በማናቸውም አገልግሎት-ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች በሚፈቀደው መሠረት ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሆኖም ግን በእኛ ይዘት ውስጥ ያለን ማናቸውም የአዕምሯዊ ንብረት መብት ያለውን ይዘት ልናስቀር እንችላለን። የእኛን ማናቸውም ታዋቂ ምርት አሠራር፣ አርማዎች፣ ወይም ሕጋዊ ማስታወቂያዎች አያስወግዱ፣ እንዲድበሰበሱ አያድርጉ ወይም አይቀይሩ። የእኛ የታወቂ ምርት አሠራር ወይም አርማዎች መጠቀም የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ የGoogle ታዋቂ ምርት ፈቃዶችን ገጽ ይመልከቱ።

ሌላ ይዘት

በመጨረሻም፣ አንዳንድ አገልግሎቶቻችን የሌሎች ሰዎች ወይም የድርጅቶች የሆነ የይዘት መዳረሻ ሊሰጡዎ ይችላሉ — ለምሳሌ፣ አንድ የመደብር ባለቤት ስለራሳቸው ንግድ የሰጡት መግለጫ፣ ወይም በGoogle ዜና ላይ የሚታይ የአንድ ጋዜጣ ዘገባ። ይህን ይዘት ያለዚያ ሰው ወይም ድርጅት ፈቃድ፣ ወይም ደግሞ በህግ ከተፈቀደው ውጭ፣ መጠቀም አይችሉም። በሌሎች ሰዎች ወይም ድርጅቶች ይዘት ላይ ያሉ አመለካከቶች የራሳቸው ነው፣ የGoogle አመለካከት ያንጸባርቃሉ ማለት አይደለም።

በGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ሶፍትዌር

አንዳንድ አገልግሎቶቻችን ሊወርድ የሚችል ሶፍትዌርን ያካትታሉ። ይህን ሶፍትዌር እንደ የአገልግሎቶች አካል እንዲጠቀሙበት ፈቃድ ሰጥተነዎታል።

ይህ የምንሰጠዎ ፈቃድ እንደሚከተለው ነው፦

  • ዓለም አቀፍ፣ ይህም ማለት በየትኛውም ዓለም የሚሠራ ነው
  • ማንንም አያገልም፣ ይህም ማለት እኛ የዚኅን ሶፍትዌር ፈቃድ ለሌሎች አሳልፈን መስጠት እንችላለን
  • ከባለቤትነት ክፍያ ነፃ፣ ይህም ማለት ለዚህ ፈቃድ የሚከፈሉ ምንም ክፍያዎች የሉም
  • የግል፣ ይህም ማለት ወደሌላ ማንም አይተላለፍም
  • ሊመደብ የማይችል፣ ይህም ማለት ፈቃዱን ለሌላ ለማንም አሳልፈው መመደብ አይችሉም

ከእኛ አገልግሎቶች አንዳንዶቹ እኛ ለእርስዎ የሚገኝ የምናደርግልዎትን በክፍት ምንጭ ፈቃድ ውሎች ሥር የቀረበ ሶፍትዌርን ያካትታሉ። አንዳንድ ጊዜ በክፍት ምንጭ ፈቃድ ውስጥ የእነዚህን ውሎች ክፍሎች በግልጽ የሚሽሩ ድንጋጌዎች ስላሉ እባክዎ እነዚያን ፈቃዶች ማንበብዎትን እርግጠኛ ይሁኑ።

ማንኛውም የአገልግሎቶቻችን ወይም የሶፍትዌራችን ክፍል መቅዳት፣ መቀየር፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወይም ማከራየት አይችሉም። እንዲሁም ከእኛ የጽሑፍ ፈቃድ ካላገኙ ወይም የሚመለከተው ህግ የሚፈቅደልዎ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም የምንጭ ኮዳችን በኋሊዮሽ ምሕንድስና መፍታት ወይም ለማውጣት መሞከር አይችሉም።

አንድ አገልግሎትን ለመጠቀም የሚወርድ ሶፍትዌር የሚያስፈልግ ከሆነ ወይም ሶፍትዌሩ በአገልግሎቱ ውስጥ የተካተተ እንደሆነ፣ ያ ሶፍትዌር አዲስ ስሪት ወይም ባህሪ በሚገኝበት ጊዜ በእርስዎ መሣሪያ ላይ በራስ ሰር አንዳንድ ጊዜ ይዘምናል። አንዳንድ አገልግሎቶች የእርስዎን ራስሰር ዝማኔ ቅንብሮች እንዲያስተካክሉ ያስችልዎታል።

ችግሮች ወይም አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ

በሕግ እርስዎ (1) የተወሰነ ጥራት ያለው አገልግሎትን፣ እና (2) ነገሮች ከተሳሳቱ ችግሮችን ማስተካከል መብት ይኖርዎታል። እነዚህ ውሎች እነዚያን መብቶች አይገድቡም ወይም ማናቸውንም አይነጥቁም። ለምሳሌ፣ እርስዎ ደንበኛ ከሆኑ፣ በእርስዎ አገር ውስጥ ላሉ ደንበኞች የተሰጡትን ሁሉንም ሕጋዊ መብቶች በማግኘት መዝናናትዎን መቀጠል ይችላሉ።

ዋስትና

ተቀባይነት ያለው ክኅሎት እና ጥንቃቄ በመጠቀም የእኛን አገልግሎቶች እናቀርባለን። በዚህ ዋስትና ውስጥ የተብራራውን የጥራት ደረጃ የማናሟላ ከሆነ፣ ለእኛ ይህንኑ ሊነግሩን ይስማማሉ እኛም ችግሩን መፍትሔ ለመስጠት ከእርስዎ ጋር አብረን ለመሥራት እንሞክራለን።

የኃላፊነት መግለጫ

ስለ የእኛ አገልግሎቶች እኛ የምንገባቸውን የውዴታ ግዴታዎች ብቻ (በአገልግሎቱ ውስጥ ስላለ ይዘት፣ የእኛ አገልግሎቶች የተወሰኑ ተግባራት፣ ወይም የእነርሱ አስተማማኝነት፣ ተገኝነት ወይም የእርስዎን ፍላጎቶች ለማሟላት ያለን አቅም ጨምሮ) (1) በ ዋስትና ክፍል ውስጥ እንድተብራራው፣ (2) በ አገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች፣ ወይም (3) ተገቢነት ባላቸው ሕጎች ሥር በቀረቡት መሠረት ተብራርተዋል። ስለ የእኛ አገልግሎቶች ሌሎች ማናቸውም ዓይነት የውዴታ ግዴታዎች ውስጥ አንገባም።

እና በህግ ካልተጠየቀ በስተቀር እንደ መሸጥ መቻል፣ ለአንድ ዓላማ ያለው ብቁነት እና ጥሰት-አልባ ያሉ በውስጥ ታዋቂ ዋስትናዎችን አናቀርብም።

ተጠያቂነቶች

ለሁሉም ተጠቃሚዎች

እነዚህ ውሎች አግባብነት ባለው ሕግ በሚፈቀደው መሠረት የእኛን ኃላፊነቶች ብቻ ይገድባሉ። በተለይ እነዚህ ውሎች ለሞት፣ ወይም በአካል ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣ መጭበርበር፣ ማታለል፣ ከፍተኛ ቸልተኝነት ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ መጥፎ ባሕሪን ማሳየት ድርጊት Google የሚኖርበትን ተጠያቂነት አይገድቡትም።

በዚህ ክፍል ላይ የተገለጹ ሌሎች መብቶች እና ግዴታዎች (ችግሮች ወይም አለመስማማቶች የተከሰቱ እንደሆነ) ውጭ Google ለማንኛውም ጥፋት ኃላፊነቱን አይወስድም፣ እኛ እነዚሂን ደንቦች ወይም አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦችን በመጣሳችን የተከሰቱ ካልሆኑ በስተቀር።

ለንግድ ተጠቃሚዎች እና ድርጅቶች ብቻ

እርስዎ የንግድ ተጠቃሚ ወይም ድርጅት ከሆኑ በሚመለከተው ህግ እስከሚፈቅደው ድረስ፦

  • እርስዎ ከአገልግሎቶቹ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወይም አላግባብ ባለመጠቀምዎ ወይም ደግሞ እነዚህን ደንቦች ወይም አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦችን በመጣስዎ Google እና የእሱ ዳይሬክተሮች፣ ሰራተኛዎች፣ ተቀጣሪዎች እና ተዋዋዮች ከማናቸውም የሶስተኛ ወገን ህጋዊ የክስ ሂደቶች (በመንግስት ባለስልጣናት የተወሰዱ እርምጃዎች ጨምሮ) ይክሳሉ። ይህ ካሳ ከይገባኛል ጥያቄዎች፣ ጥፋቶች፣ ጉዳቶች፣ ፍርዶች፣ ቅጣቶች፣ የሙግት ወጪዎች እና የህግ ስርዓት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ያሉ ማንኛውም ተጠያቂነትን ወይም ወጪን ይሸፍናል።
  • Google ለሚከተሉት ተጠያቂነቶች ኃላፊነቱን አይወስድም፦
    • የትርፍ፣ የገቢ፣ የንግድ ሼል ዕድል፣ መልካም ማንነት ወይም ተጠብቆ የነበረ ቁጠባ ገንዘብ ኪሣራ
    • ቀጥተኛ ያልሆኑ ወይም እንደ ውጤት የሚከሰት ጥፋት
    • የቅጣት ጉዳቶች
  • ከእነዚህ ውሎች በመነሣት የሚኖረው የGoogle ድምር ተጠያቂነት ደረጃ (1) US$500 ወይም የውል ጥሰቱ ከመፈጸሙ በፊት ባሉት 12 ወራት ውስጥ ተዛማጅነት ያላቸውን አገልግሎቶች ለመጠቀም እርስዎ ከከፈሉት ክፍያ (2) 125% ያክል ላይ የተገደበ ነው

ካሳ መክፈልን ጨምሮ ከተወሰኑ ኃላፊነቶች በሕግ የሚታለፉ ከሆኑ እነዚያ ኃላፊነቶች በእነዚህ ውሎች መሠረት በእርስዎ ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም። ለምሳሌ፣ የተባበሩት መንግሥታት ከተወሰኑ ግዴታዎች የተወሰኑ ያለመከሰስ መብቶች ያሉት ሲሆን እነዚህ ውሎች እነዚያን ያለመከሰስ መብቶች አይሽሯቸውም።

ችግሮች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እርምጃ መውሰድ

ከዚህ በታች በተብራራው መሠረት እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት፣ አቅም በፈቀደ መጠን ለእርስዎ ቅድሚያ ማስታወቂያ እንሰጥዎታለን፣ የምንወስደውን እርምጃ ምክንያት እናብራራለን እና ችግሩን መፍትሔ መስጠት እንዲችሉ ዕድል እንሰጣለን፤ ይህን ሳናደርግ ብንቀር ምክንያቱ ይህ ነው ሊሆን የሚችለው፦

  • ጉዳት እንዲደርስ ወይም ተጠቃሚ፣ ሦስተኛ ወገን፣ ወይም Google ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ
  • ሕጉን ወይም የሕግ አስከባሪውን ባለሥልጣን ትዕዛዝ ይጥሳል
  • አንድ ምርመራን ማሰናከል
  • የእኛን አገልግሎቶች ሥርዓተ ክውና፣ ተዓማኒነት፣ ወይም ደህንነት ያሳጣል

ይዘትዎን ማስወገድ

በምክንያታዊነት ማንኛውም የእርስዎ ይዘት (1) እነዚህን ደንቦች፣ አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች ወይም መመሪያዎች እንደሚጥስ፣ (2) የሚመለከተውን ህግ እንደሚጥስ፣ ወይም (3) የእኛን ተጠቃሚዎቻች፣ ሶስተኛ ወገኖች ወይም Google ሊጎዳ እንደሚችል ካመነን በሚመለከተው ህግ መሠረት አንዳንድ ወይም ሁሉም ይዘትዎ የማውረድ መብታችን የተጠበቀ ነው። ምሳሌዎቹ የሕፃናት ወሲብ ቀስቃሽ ነገሮች፣ የሕገወጥ የሰው ልጅ ዝውውርን ወይም ውርደትን የሚያቀላጥፍ ይዘት፣ እና የሆነ ሌላ አካልን አእምሯዊ ንብረት መብቶች የሚጥስ ይዘትን ያካትታሉ።

ወደ Google አገልግሎቶች የእርስዎን መዳረሻ ማገድ ወይም ማቋረጥ

ከሚከተሉት ውስጥ ማናቸምው ቢከሰቱ Google የአገልግሎቶቹ መዳረሻዎን የማገድ ወይም የማቋረጥ ወይም ደግሞ የGoogle መለያዎን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፦

  • እነዚህን ውሎች፣ አገልግሎት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች፣ ወይም መመሪያዎች በተጨባጭ ወይም በተደጋጋሚ ጥሰዋል
  • የህግ መስፈርት ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝን ለማክበር ይህን ማድረግ ይፈለግብናል
  • የእርስዎ ምግባር በአንድ ተጠቃሚ፣ የሶስተኛ ወገን ወይም Google — ላይ ጉዳት ወይም ተጠያቂነት እንደሚያደርስ በምክንያታዊነት ካመንን — ለምሳሌ፣ ሌሎችን ሰርጎ በመግባት፣ በማስገር፣ በመተናኮስ፣ አይፈለጌ በመላክ፣ በማሳሳት ወይም የእርስዎ ያልሆነ ይዘትን በመቅዳት።

የእርስዎ የGoogle መለያ የታገደ ወይም በስህተት እንዲቋረጥ የተደረገ መስሎ ከተሰማዎት፣ ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ።

በእርግጥ በማንኛውም ጊዜ አገልግሎቶቻችንን ማቆም ይችላሉ። አንድ አገልግሎት መጠቀም ካቆሙ አገልግሎቶቻችንን ማሻሻል መቀጠል እንድንችል ለምን እንደሆነ ብናውቅ ደስ ይለናል።

አለመግባባቶችን መፍታት፣ ገዢ ሕግ እና ፍርድ ቤቶች

Googleን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል መረጃ ለማግኘት፣ እባክህ የኛን የመገኛ ገጽ ጎብኝ።

ከእነዚህ ውሎች፣ ምርት ላይ የተወሰኑ ተጨማሪ ውሎች ወይም ማናቸውም ተዛማጅ አገልግሎቶች ጋር በተገናኘ ወይም ከእነዚህ በተነሣ የሚነሣ ማናቸውንም አለመግባባት፣ የግል ዓለም አቀፍ ሕግ ከግምት ሳይገባ የካሊፎርኒያ ሕግ የሚዳኛቸው ይሆናል። እነዚህ ክሶችና አቤቱታዎች በካሊፎርኒያ የሚገኘው የሳንታ ክላራ ካውንቲ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤቶች ብቻ የሚታይ ሲሆን በዚህ ጉዳይ እነዚህ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ሥልጣን ለመቀበል እርስዎ እና Google እንደተስማማችሁ ታረጋግጣላችሁ።

የሚመለከተው አካባቢያዊ ሕግ እነዚህ ግጭቶች በካሊፎርኒያ ፍርድ ቤት እንዳይፈቱ የሚከለክል ከሆነ እነዚህን ግጭቶች በአካባቢያዊ ፍርድ ቤቶችዎ ላይ ማስገባት ይችላሉ። በተመሳሳይ መልኩም የሚመለከተው ህግ አካባቢያዊ ፍርድ ቤትዎ እነዚህን ግጭቶች ለመፍታት የካሊፎርኒያ ህግን እንዲተገብሩ የሚከለክልዎ ከሆነ እነዚህ ግጭቶች ለሚመለከታቸው የአገርዎ፣ የግዛትዎ ወይም የሌላ ቦታዎ አካባቢያዊ ህጎች ተገዢ ናቸው።

ስለ እነዚህ ውሎች

በህግ መሠረት እንደ ይህ የአገልግሎት ውል ያለ በውል ሊገደቡ የማይችሉ የተወሰኑ መብቶች አለዎት። እነዚህ ደንቦች በምንም አይነት መልኩ እነዚህን መብቶች ለመገደብ የታሰቡ አይደሉም።

እነዚህ ደንቦች በእርስዎ እና በGoogle መካከል ያለውን ግንኙነት ይገልጻሉ። ለሌሎች ሰዎች ወይም ለድርጅቶች ምንም ህጋዊ መብቶች አይፈጥሩም፣ ሌሎች በእነዚህ ደንቦች ስር ከዚያ ግንኙነት የሚጠቀሙ ቢሆኑ እንኳ።

የእኛ ውሎች ለመረዳት ቀላል እንዲሆኑ ለማድረግ እንፈልጋለን በመሆኑም ከእኛ አገልግሎቶች ምሳሌዎችን ተጠቅመናል። ሆኖም የተጠቀሱት አገልግሎቶች በእርስዎ አገር ውስጥ ላይገኝ ይችሉ ይሆናል።

እነዚህ ደንቦች ከአገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች ጋር የሚጋጩ ከሆኑ ተጨማሪ ደንቦቹ ለዚያ አገልግሎት ይገዛሉ።

ከውል ድንጋጌዎቹ መካከል አንዱ የማይሠራ ቢሆን ወይም ተፈጻሚ መሆን ባይችል ይህ በሌሎቹ የውል ድንጋጌዎቹ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖም አይኖርም።

እነዚህን ደንቦች ወይም አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦችን የማይከተሉ ከሆኑ፣ እና እኛ ወዲያውኑ እርምጃ ካልወሰድን፣ ይህ ማለት እንደ ለወደፊቱ እርምጃ መውሰድ ያሉ ሊኖሩን የሚችሉ ማናቸውም መብቶች እየተወን ነው ማለት አይደለም።

እነዚህን ደንቦች እና አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች (1) በአገልግሎቶቻችን ወይም እንዴት ንግድ እንደምንሰራ ላይ ያሉ ለውጦችን ለማንጸባረቅ — ለምሳሌ፣ አዲስ አገልግሎቶችን፣ ባህሪያትን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ ዋጋዎችን ወይም ጥቅማጥቅሞችን ስናክል (ወይም የድሮዎቹን ስናስወግድ)፣ (2) ለህጋዊ፣ ደንባዊ ወይም የደህንነት ምክንያቶች፣ ወይም (3) አላግባብ መጠቀምን ወይም ጉዳትን ለመከላከል ስንል ልናዘምናቸው እንችላለን።

እነዚህን ደንቦች ወይም አገልግሎት-ተኮር ተጨማሪ ደንቦች በጉልህ ከቀየርን ከሚከተሉት ሁኔታዎች በስተቀር ምክንያታዊ የሆነ ቅድመ-ማሳወቂያ እና ለውጦቹን የመገምገም ዕድል እናቀርብልዎታለን፤ (1) አዲስ አገልግሎት ወይም ባህሪ ስንለቅቅ ወይም (2) በአስቸኳይ ሁኔታዎች ላይ እንደ በመካሄድ ያለ አላግባብ መጠቀም ወይም ለህጋዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት በስተቀር።በእነዚህ አዳዲስ ውሎች የማይስማሙ ከሆነ፣ የእርስዎን ይዘት ማስወገድ እና እነዚህን አገልግሎቶች መጠቀም ማቆም አለብዎት። እንዲሁም የGoogle መለያዎን በማንኛውም ጊዜ በመዝጋት ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ማቆም ይችላሉ።

ትርጓሜዎች

መካስ ወይም ካሳ

የአንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ ክሶች ባሉ የህግ ስርዓቶች ምክንያት ከሚከሰቱ ጥፋቶች መከላከል ያለባቸው የውል ግዴታ።

ሸማች

የGoogle አገልግሎቶችን ከንግዳቸው፣ ጥበባቸው ወይም ሙያቸው ውጭ ለግልና ለንግድ ላልሆኑ ዓላማዎች የሚጠቀም ግለሰብ። (የንግድ ሥራ ተጠቃሚ የሚለውን ይመልከቱ)

ተጠያቂነት

አቤቱታው በውል ላይ በመመርኮዝ፣ በጥፋት (ቸልተኝነትን ጨምሮ)፣ ወይም ሌላ ምክንያት የሚነሣ የሕጋዊ ይገባኛል ጥያቄ ማናቸውም ዓይነት የተነሣ የሚፈጠሩ ኪሳራዎች እና እነዚህ ኪሳራዎች በአግባቡ አስቀድሞ ሊታሰብባቸው ወይም ሊገመቱ ይችሉ የነበሩ ይሁኑ ወይም አይሁኑ።

አገልግሎቶች

የGoogle አገልግሎቶች https://policies.google.com/terms/service-specific ላይ የተዘረዘሩ ምርቶች እና አገልግሎቶች ናቸው፣ እነዚህንም ጨምሮ፦

  • Google መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች (እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች ያሉ)
  • መድረኮቸ (እንደ Google Play)
  • የተዋሃዱ አገልግሎቶች (እንደ በሌሎች ኩባንያዎች መተግበሪያዎች ወይም ጣቢያዎች ላይ የተከተተ ካርታዎች ያሉ)
  • መሣሪያዎች (እንደ Google Home ያለ)

አጋር

የGoogle የኩባንያዎች ቡድን አባል የሆነ ተቋም ማለትም Google LLC እና የበታች መሥሪያ ቤቶቹ፣ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የደንበኛ አገልግሎት የሚያቀርቡ የሚከተሉትን ኩባንያዎች ጨምሮ፦ Google Ireland Limited፣ Google Commerce Ltd፣ እና Google Dialer Inc.።

ዋስትና

አንድ ምርት ወይም አገልግሎት በተወሰነ ደረጃ መሠረት እንደሚሠራ የሚሰጥ ዋስትና።

ኦርጂናሉ ሥራ (ለምሳሌ የጦማር ልጥፍ፣ ፎቶ ወይም ቪዲዮ) በሌሎች እንዴት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በኦርጂናል ሥራ ፈጣሪው እንዲወስን የሚያስችለው ሕጋዊ መብት።

የኃላፊነት መግለጫ

የአንድን ሰው ሕጋዊ ግዴታዎች የሚገድብ ዐርፍተ ነገር።

የንግድ ምልክት

የአንድ ግግለሰብ ወይም ድርጅት ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ከሌላኛው መለየት የሚችሉ በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች።

የንግድ ተጠቃሚ

ሸማች (ሸማች ይመልከቱ) ያልሆነ ግለሰብ ወይም ህጋዊ አካል።

የአህ መድረክ ለንግድ ቁጥር

ለመስመር ላይ የመሃል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለሆኑ የንግድ ተጠቃሚዎች ፍትሐዊነትን እና ግልጽነትን ማስተዋወቅ ላይ ያለው ደንብ (አህ) 2019/1150።

የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች (IP መብቶች)

እንደ የመፈልሰፍ ፈጠራዎች (የፓተንት መብቶች)፤ የስነ ጽሑፋዊ እና ኪነ ጥበባዊ ስራዎች (ቅጂ መብት)፤ ንድፎች (የንድፍ መብቶች)፤ እና በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች (የንግድ ምልክቶች) ባሉ የአንድ ሰው አዕምሯዊ ፈጠራዎች ላይ ያሉ መብቶች። የአዕምሯዊ መብቶች የእርስዎ፣ የሌላ ግለሰብ ወይም የአንድ ድርጅት ሊሆኑ ይችላሉ።

የእርስዎ ይዘት

እርስዎ የሚጽፏቸውን፣ የሚሰቅሏቸውን፣ የሚያስገቧቸውን፣ የሚያከማቿቸውን፣ የሚልኳቸውን፣ የሚቀበሏቸውን ወይም የእኛን አገልግሎቶች በመጠቀም ከGoogle ጋር የሚያጋሯቸውን እንደ የሚከተሉት ያሉት ነገሮች፦

  • እርስዎ የሚፈጥሯቸው ሰነዶች፣ ሉሆች እና ስላይዶች
  • በጦማሪ በኩል የሚሰቅሏቸው የጦማር ልጥፎች
  • በካርታዎች ላይ የሚያስገቧቸው ግምገማዎች
  • በDrive ላይ የሚያከማቿቸው ቪዲዮዎች
  • በGmail በኩል እርስዎ የሚልኳቸው እና የሚቀበሏቸው ኢሜይሎች
  • በፎቶዎች በኩል ለጓደኛዎች የሚያጋሯቸው ስዕሎች
  • ለGoogle የሚያጋሯቸው የጉዞ ዕቅዶች

ድርጅት

ሕጋዊ ተቋም (እንደ ማህበር፣ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት ወይም ትምህርት ቤት) እና ግለሰብ ያልሆነ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ