የAI አመንጪ የተከለከለ አጠቃቀም መመሪያ
ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፦ 14 ማርች 2023
የAI አመንጪ ሞዴሎች አዲስ ርዕሶችን ለማሰስ፣ የእርስዎን ፈጠራ ለማነቃቃት እና አዲስ ነገሮችን ለመማር ሊያግዙዎት ይችላሉ። ቢሆንም ኃላፊነት በተላበሰ፣ ሕጋዊ መንገድ እንዲጠቀሙባቸው እና አንዲሳተፉባቸው እንጠብቃለን። በዚህ ረገድ እርስዎ የሚከተሉትን ለማድረግ ይህን መመሪያ ዋቢ የሚያደርጉ የGoogle አገልግሎቶችን መጠቀም የለብዎትም፦
- የሚከተሉትን ጨምሮ አደገኛ፣ ሕገ-ወጥ ወይም ተንኮል-አዘል እንቅስቃሴዎችን መፈጸም ወይም ማመቻቸት
- ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ወይም የሕግ ጥሰቶችን ማመቻቸት ወይም ማስተዋወቅ፣ ለምሳሌ
- ከልጅ ወሲባዊ ጥቃት ወይም ብዝበዛ ጋር ተዛማጅ የሆነ ይዘትን ማስተዋወቅ ወይም ማመንጨት
- የሕገ-ወጥ ንጥረ ነገሮች፣ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶችን ሽያጭ ማስተዋወቅ ወይም ማመቻቸት ወይም እነዚህን ለማቀናጀት ወይም ለመድረስ መመሪያዎችን ማቅረብ
- ተጠቃሚዎች ማናቸውንም ዓይነት ወንጀሎች እንዲፈጽሙ ማመቻቸት ወይም ማበረታታት
- አመጻዊ ጽንፈኝነትን ወይም የአሸባሪ ይዘትን ማስተዋወቅ ወይም ማመንጨት
- የአገልግሎቶች አላግባብ መጠቀም፣ ጉዳት፣ ጣልቃ ገብነት ወይም መስተጓጎል (ወይም ሌሎችም ይህንኑ እንዲያደርጉ ማስቻል) ለምሳሌ፣
- የአይፈለጌ መልዕክትን መመንጨት ወይም መሰራጨት ማስተዋወቅ ወይም ማመቻቸት
- ለአታላይ ወይም ለአጭበርባሪ እንቅስቃሴዎች፣ ለማጭበርበሮች፣ ለማስገር ወይም ለተንኮል አዘል ዌር ይዘትን ማመንጨት።
- የደህንነት ማጣሪያዎችን ለመሻር ወይም ለመተላለፍ ወይም ሆነ ተብሎ ሞዴሉን ከመመሪያዎቻችን ጋር በሚቃረን መንገድ ለመንዳት የሚደረጉ ሙከራዎች
- ግለሰቦችን ወይም አንድን ቡድን የሚጎዳ ወይም የእነሱን ጉዳት የሚያበረታታ ይዘት ማመንጨት፣ ለምሳሌ
- ጥላቻን የሚደግፍ ወይም የሚያበረታታ ይዘትን ማመንጨት
- የትንኮሳ ወይም ሌሎችን ለማስፈራራት የማጥቃት፣ አላግባብ የመጠቀም ወይም የመሳደብ ዘዴዎችን ማመቻቸት
- ጥቃትን የሚያመቻች፣ የሚያስተዋውቅ ወይም የሚያነሳሳ ይዘትን ማመንጨት
- ራስን መጉዳት የሚያመቻች፣ የሚያስተዋውቅ ወይም የሚያበረታታ ይዘትን ማመንጨት
- በግል የሚያስለይ መረጃን ለማከፋፈል ወይም ሌሎች ጉዳቶች ማመንጨት
- ሰዎችን ያለፈቃደኝነታቸው መከታተል ወይም ክትትል ማድረግ
- በሰዎች ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖዎች በተለይ አደገኛ ከሆኑ ወይም ጥበቃ ከተደረገላቸው ባህሪያት ጋር የተያያዙ ተጽዕኖዎች ሊኖረው የሚችል ይዘትን ማመንጨት
- ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ወይም የሕግ ጥሰቶችን ማመቻቸት ወይም ማስተዋወቅ፣ ለምሳሌ
- የሚከተሉትን ጨምሮ የተሳሳተ መረጃ ለመስጠት፣ ሐሳዊ ውክልና ለመስጠት ወይም ለማሳሳት የታሰበ ይዘትን መፍጠር እና ማሰራጨት
- ይዘቱ የተፈጠረው በሰው ነው በማለት የመነጨው ይዘትን ምንጭ ሐሳዊ ውክልና መስጠት ወይም ለማታለል የመነጨውን ይዘት እንደ ኦሪጂናል ሥራዎች አድርጎ መወከል
- ያለ ልቅ ይፋ ማውጣት ግለሰብን (በሕይወት ያለ ወይም የሞተ) የሚያስመስል ይዘትን ማመንጨት
- አሳሳች የክህሎት ወይም የችሎታ የይገባኛል ጥያቄዎች በተለይ ጥንቃቄ በሚሹ አካባቢዎች ውስጥ (ለምሳሌ ጤና፣ ፋይናንስ፣ የመንግሥት አገልግሎቶች ወይም ሕጋዊ)
- የቁሳቁስ ወይም የግለሰብ መብቶች ወይም ደህንነት ላይ ተጸዕኖ በሚያደርጉ ጎራዎች ውስጥ ራስ-ሰር ውሳኔዎችን ማድረግ (ለምሳሌ፦ ፋይናንስ፣ ሕጋዊ፣ የሥራ ቅጥር፣ የጤና እንክብካቤ፣ የቤት አቅርቦት፣ መድህን እና ማህበራዊ ደህንነት)
- ለወሲብ ቪድዮ ወይም ለወሲባዊ እርካታ ዓላማዎች የተፈጠረ ይዘትን (ለምሳሌ ወሲባዊ ቻትቦቶች) ጨምሮ ወሲባዊ ልቅነትን የያዘ ይዘት ማመንጨት። ይህ ለሳይንሳዊ፣ ትምህርታዊ፣ ዘጋቢ ወይም ጥበባዊ ዓላማዎች የተፈጠረ ይዘትን እንደማያካትት ልብ ይበሉ።