ጉግል ኩኪዎችን እንዴት እንደሚጠቀም

ይህ ገጽ Google ኩኪዎችን እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀምባቸውን ዓላማዎች ይገልጻል። እንዲሁም Google እና የእኛ አጋሮች እንዴት ኩኪዎችን በማስታወቂያ ሥራ ላይ እንደሚጠቀሙባቸው ያብራራል።

ኩኪዎች እርስዎ በሚጎበኙት ድር ጣቢያ ወደ አሳሽዎ የተላኩ ትንሽ የጽሑፍ ክፍሎች ናቸው። እነሱ ድር ጣቢያውን ስለጉብኝትዎ ያለ መረጃን እንዲያስታውስ ያግዙታል፣ ይህም እርስዎ ጣቢያውን ዳግም ሲጎበኙት እንዲያቀልልዎት እና ለእርስዎ የበለጠ ጠቃሚ እንዲሆን ያደርጋል። መተግበሪያ ወይም መሣሪያ ለመለየት ጥቅም ላይ የዋሉ ልዩ ለዪዎች፣ የፒክስል መለያዎች እና አካባቢያዊ ማከማቻን ጨምሮ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ተመሳሳይ ተግባር ማከናወን ይችላሉ። በዚህ ገፅ ላይ የተገለጹት ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ከታች ለተገለጹት ዓላማዎች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

የእርስዎን ግላዊነት በእኛ የኩኪዎች እና ሌላ መረጃ አጠቃቀም እንዴት እንደምንጠብቅ ለመረዳት የግላዊነት መመሪያውን ይመልከቱ።

በGoogle ጥቅም ላይ የዋሉ የኩኪዎች ዓላማዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች

ከታች ለተገለጹት ዓላማዎች Google አንዳንድ ወይም ሁሉንም ኩኪዎችን ወይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን በአሳሽዎ፣ መተግበሪያዎ ወይም መሣሪያዎ ውስጥ ሊያከማች ወይም ሊጠቀም ይችላል። ኩኪዎችን እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ለማስተዳደር፣ ኩኪዎችን ለተወሰኑ ዓላማዎች መጠቀምን አለመቀበልን ጨምሮ፣ g.co/privacytoolsን መጎብኘት ይችላሉ። እንዲሁም በአሳሽዎ ውስጥ ኩኪዎችን ማስተዳደር ይችላሉ (ምንም እንኳ ለተንቀሳቃሽ መሣሪያዎች አሳሾች ይህንን ታይነት ላይሰጡ ባይችሉም)። ከእነዚህ ቴክኖሎጂዎች አንዳንዶቹ በመሣሪያ ቅንብሮችዎ ውስጥ ወይም በመተግበሪያ ቅንብሮች ውስጥ ሊተዳደሩ ይችላሉ።

ተግባራዊነት

ለተግባራዊነት ዓላማዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ለአገልግሎት መሠረታዊ የሆኑ ባህሪያትን እንዲደርሱባቸው ያስችሉዎታል። እነዚህ ኩኪዎች የGoogle አገልግሎቶችን ለማቅረብ እና ለማቆየት ያገለግላሉ። ለአገልግሎት መሠረታዊ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮች እንደ የእርስዎ የቋንቋ ምርጫ፤ ከክፍለ-ጊዜዎ ጋር ተዛማጅ የሆነ እንደ የሸመታ ተሳቢ ይዘት ያለ መረጃን ማከማቸት፤ ባህሪያትን ማንቃት ወይም በእርስዎ የተጠየቁ ተግባራትን ማከናወን እና አገልግሎቱን ለማስጠበቅ እና ለማሻሻል የሚረዱ የምርት ማመቻቸቶች ያሉ ምርጫዎች እና አማራጮች ማስታወስን ያካትታሉ።

አንዳንድ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ምርጫዎችዎን ለማስጠበቅ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለምሳሌ፣ የGoogle አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ አብዛኛዎቹ ሰዎች በኩኪ ምርጫቸው ላይ በመመሥረት በአሳሻቸው ውስጥ «NID» ወይም «_Secure-ENID» የሚባል ኩኪ አላቸው። እነዚህ ኩኪዎች እንደ የእርስዎ ተመራጭ ቋንቋ፣ በአንድ የፍለጋ ውጤቶች ገጽ ላይ ምን ያህል ውጤቶች እንዲታዩ እንደሚፈልጉ (ለምሳሌ፣ 10 ወይም 20) እና የGoogle SafeSearch ማጣሪያ እንዲበራልዎ ይፈልጉ ወይም አይፈልጉ እንደሆነ ያሉ የእርስዎን ምርጫዎች እና ሌላ መረጃ ለማስታወስ ጥቅም ላይ ይውላሉ። እያንዳንዱ የ«NID» ኩኪ አንድ ተጠቃሚ መጨረሻ ላይ ከተጠቀሙበት ጊዜ ጀምሮ ከ6 ወራት በኋላ የአገልግሎት ጊዜው የሚያበቃ ሲሆን የ«_Secure-ENID» ኩኪው ለ13 ወራት ይቆያል። «VISITOR_INFO1_LIVE» እና «__Secure-YEC» የሚባሉ ኩኪዎች ለYouTube ተመሳሳይ ዓላማ አላቸው እና እንዲሁም በአገልግሎቱ ላይ ችግሮችን ለማወቅ እና ለመፍታት ጥቅም ላይ ይውላሉ። እነዚህ ኩኪዎች በቅደም ተከተል ለ6 ወራት እና ለ13 ወራት ይቆያሉ።

ሌሎች ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች በአንድ የተወሰነ ክፍለ-ጊዜ ውስጥ የእርስዎን ተሞክሮ ለማስጠበቅ እና ለማሻሻል ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለምሳሌ፣ YouTube እንደ የእርስዎ ተመራጭ የገፅ ውቅረት እና እንደ ግልጽ የራስ-ሰር ማጫወት ምርጫዎች፣ የይዘት መበወዝ እና የተጫዋች መጠን የመሳሰሉ የመልሶ ማጫወት ምርጫዎች ያሉ መረጃዎችን ለማከማቸት የ«PREF» ኪኩን ይጠቀማል። ለYouTube Music፣ እነዚህ አማራጮች የድምጽ መጠንን፣ የድግግሞሽ ሁነታን እና በራስ-ሰር አጫውትን ያካትታሉ። ይህ ኩኪ ተጠቃሚው ለመጨረሻ ጊዜ ከተጠቀሙበት ጊዜ ጀምሮ ከ8 ወራት በኋላ የአገልግሎት ጊዜው ያበቃል። እንዲሁም የ«pm_sess» ኩኪው የአሳሽዎን ክፍለ-ጊዜ ለማስጠበቅ ያግዛል እና ለ30 ደቂቃዎች ይቆያል።

እንዲሁም ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች የGoogle አገልግሎቶች አፈጻጸምን ለማሻሻል ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የ«CGIC» ኩኪው በተጠቃሚው የመጀመሪያ ግቤት ላይ በመመስረት የፍለጋ ጥያቄዎችን በራስ-ሰር በማጠናቀቅ የፍለጋ ውጤቶች ማድረስን ያሻሽላል። ይህ ኩኪ ለ6 ወራት ይቆያል።

Google የተጠቃሚውን የኩኪ ምርጫ በተመለከተ የተጠቃሚውን ሁኔታ ለማከማቸት ለ13 ወራት የሚቆይ የ'SOCS' ኩኪን ይጠቀማል።

ደህንነት

ተጠቃሚዎችን በማረጋገጥ፣ ከአይፈለጌ መልዕክት፣ ማጭበርበር እና አላግባብ መጠቀምን በመጠበቅ እና የማቋረጥ አገልግሎትን በመከታተል እርስዎን ለመጠበቅ Google ኩኪዎችን እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን ለደኅንነት ዓላማ ይጠቀማል።

ተጠቃሚዎችን ለማረጋገጥ ስራ ላይ የሚውሉ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ይህን መለያ መድረስ የሚችለው የመለያው ትክክለኛ ባለቤት ብቻ መሆኑን ለማረጋገጥ ይረዳሉ። ለምሳሌ፣ በዲጂታል የተፈረመባቸው እና የተመሠጠሩ የተጠቃሚው የGoogle መለያ መታወቂያ እና የቅርብ ጊዜው መግቢያ ሰዓት መዝገቦችን የያዙ «SID» እና «HSID» የተባሉ ኩኪዎች። የእነዚህ ኩኪዎች ጥምረት እንደ በGoogle አገልግሎቶች ውስጥ የገቡ የቅጾች ይዘትን የመስረቅ ሙከራዎች ያሉ ብዙ የጥቃት ዓይነቶችን Google እንዲያግድ ያስችሉታል። እነዚህ ኩኪዎች ለ2 ዓመታት ይቆያሉ።

አንዳንድ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አይፈለጌ መልዕክት፣ ማጭበርበር እና አላግባብ መጠቀምን ለማወቅ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለምሳሌ የ«pm_sess» እና «YSC» ኩኪዎች በአንድ የአሰሳ ክፍለ-ጊዜ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎች በተጠቃሚው የቀረቡ መሆናቸውን እና በሌሎች ጣቢያዎች የቀረቡ አለመሆናቸውን ያረጋግጣሉ። እነዚህ ኩኪዎች ተንኮል-አዘል ጣቢያዎች ተጠቃሚው ሳያውቅ ተጠቃሚውን በመወከል እንዳይንቀሳቀሱ ይከለክላሉ። የ«pm_sess» ኩኪው ለ30 ደቂቃዎች የሚቆይ ሲሆን የ«YSC» ኩኪው ለተጠቃሚው የአሰሳ ክፍለ ጊዜ የቆይታ ጊዜ ይቆያል። የ«__Secure-YEC» እና «AEC» ኩኪዎች አስተዋዋቂዎች ለአጭበርባሪ ወይም ልክ ላልሆኑ ዕይታዎች ወይም ከማስታወቂያዎች ጋር ለተደረጉ መስተጋብሮች በተሳሳተ መንገድ እንዳይከፍሉ እና በYouTube አጋር ፕሮግራም ውስጥ ያሉ የYouTube ፈጣሪዎች ፍትሃዊ ክፍያ እንዲከፈላቸው ለማረጋገጥ አይፈለጌ መልዕክት፣ ማጭበርበር እና አላግባብ መጠቀምን ለማወቅ ጥቅም ላይ ይውላሉ። የ«AEC» ኩኪው ለ6 ወራት ይቆያል እና የ«__Secure-YEC» ኩኪው ለ13 ወራት ይቆያል።

ትንታኔ

ከአንድ አገልግሎት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ለመረዳት Google ኩኪዎችን እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን ለትንታኔ ዓላማ ይጠቀማል። እነዚህ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች የተመልካቾችን ተሳትፎ እና የጣቢያ ስታቲስቲክስን ለመለካት የሚያስችለንን ውሂብ ለመሰብሰብ ይረዳሉ። ይህ አገልግሎቶች እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ለመረዳት እና ይዘታቸውን፣ ጥራታቸውን እና ባህሪያቸውን ለማሻሻል ይረዳናል፣ እንዲሁም አዳዲስ አገልግሎቶችን እንድናዳብር እና እንድናሻሽል ያስችለናል።

አንዳንድ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ጎብኚዎቻቸው እንዴት ከአገልግሎቶቻቸው ጋር እንደሚሳተፉ እንዲረዱ ያግዟቸዋል። ለምሳሌ፣ Google ትንታኔ የGoggle ትንታኔ አገልግሎትን የሚጠቀሙ ንግዶችን ወክሎ መረጃ ለመሰብሰብ እና የግለሰብ ጎብኚዎችን ማንነትን በማያሳውቅ መልኩ የጣቢያ የአጠቃቀም ስታትስቲክስን ለእነሱ ሪፖርት ለማድረግ የኩኪዎች ስብስብን ይጠቀማል። በGoogle ትንታኔ ጥቅም ላይ የሚውለው ዋናው ኩኪ «_ga» አገልግሎቱ አንድ ጎብኚን ከሌላኛው እንዲለይ ያስችለዋል እና ለ2 ዓመታት ይቆያል። የGoogle አገልግሎቶችን ጨምሮ Google ትንታኔን የሚጠቀም ማንኛውም ጣቢያ የ«_ga» ኩኪን ይጠቀማል። እያንዳንዱ የ«_ga» ኩኪ ለተወሰነ ንብረት ልዩ ነው፣ ስለዚህ አንድ የተወሰነ ተጠቃሚ ለመከታተል ወይም በመላው የማይዛመዱ ድር ጣቢያዎች ላይ ለማሰስ ጥቅም ላይ ሊውል አይችልም።

እንዲሁም የGoogle አገልግሎቶች ለትንታኔ በGoogle ፍለጋ ላይ የ«NID» እና «_Secure-ENID» ኩኪዎችን፣ እና በYouTube ላይ የ«VISITOR_INFO1_LIVE» እና «__Secure-YEC» ኩኪዎችን ይጠቀማሉ። እንዲሁም የGoogle የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያዎች ለትንታኔ እንደ «የGoogle አጠቃቀም መታወቂያ» ያሉ ልዩ ለዪዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ።

ማስታወቂያዎች

Google ኩኪዎችን ለማስታወቂያ ዓላማዎች ይጠቀማል፣ ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት፣ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት እና ለማቅረብ እና ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ለማላበስ ጨምሮ (በእርስዎ ቅንብሮች myadcenter.google.com እና adssettings.google.com/partnerads ላይ በመመሥረት)። እነዚህ ኩኪዎች ጥቅም ላይ የሚውሉት ማስታወቂያ ለተጠቃሚው የሚታይበትን ብዛት በመገደብ፣ ማየት ለማቆም የመረጧቸውን ማስታወቂያዎች ድምጸ-ከል በማድረግ እና የማስታወቂያዎችን ማድረስ እና ውጤታማነትን በመለካት ነው።

የ«NID» ኩኪ የGoogle ማስታወቂያዎችን በGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ዘግተው ለወጡ ተጠቃሚዎች ለማሳየት የሚያገለግል ሲሆን የ«IDE» እና «id» ኩኪዎች የGoogle ባልሆኑ ጣቢያዎች ላይ የGoogle ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ሥራ ላይ ይውላሉ። እንደ የAndroid የማስታወቂያ መታወቂያ (AdID) ያሉ የሞባይል ማስታወቂያ መታወቂያዎች በእርስዎ የመሣሪያ ቅንብሮች ላይ በመመሥረት በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ላይ ለተመሳሳይ ዓላማ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ካነቁ የ«IDE» ኩኪ የሚመለከቱዋቸውን ማስታወቂያዎች ግላዊነት ለማላበስ ጥቅም ላይ ይውላል። ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ካጠፉ እርስዎ ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን እንዳይመለከቱ ይህን አማራጭ ለማስታወስ የ«id» ኩኪ ጥቅም ላይ ይውላል። የ«NID» ኩኪ ተጠቃሚው ለመጨረሻ ጊዜ ከተጠቀመበት ከ6 ወራት በኋላ ጊዜው ያበቃል። የ«IDE» እና «id» ኩኪዎች በአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ (አኢአ)፣ በሲውዘርላንድ እና በዩናይትድ ኪንግደም (UK) ለ13 ወራት እና በየትኛውም ቦታ ለ24 ወራት ይቆያሉ።

በእርስዎ የማስታወቂያ ቅንብሮች ላይ በመመስረት እንደ YouTube ያሉ ሌሎች የGoogle አገልግሎቶች እነዚህን እና እንደ የ«VISITOR_INFO1_LIVE» ያለ ኩኪ ሌሎች ኩኪዎችንና ቴክኖሎጂዎችን ለማስታወቂያ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

ለማስታወቂያ ጥቅም ላይ የዋሉ አንዳንድ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች የGoogle አገልግሎቶችን ለመጠቀም በመለያ ለሚገቡ ተጠቃሚዎች ናቸው። ለምሳሌ፣ የተጠቃሚው ማስታወቂያዎች ግላዊነት የማላበስ ቅንብር በቅደም ተከተል እንዲከበር የ«DSID» ኩኪ የGoogle ባልሆኑ ጣቢያዎች ላይ በመለያ የገባ ተጠቃሚን ለመለየት ጥቅም ላይ ይውላል። የ«DSID» ኩኪ ለ2 ሳምንታት ይቆያል።

በGoogle የማስታወቂያ መሰረተ ስርዓት አማካኝነት ንግዶች በGoogle አገልግሎቶችና እንዲሁም የGoogle ባልሆኑ ጣቢያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሳየት ይችላሉ። አንዳንድ ኩኪዎች Googleን በሶስተኛ ወገን ጣቢያዎች ላይ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ይደግፋሉ እና እርስዎ በሚጎበኙት ድር ጣቢያ ጎራ ውስጥ ይቀናበራሉ። ለምሳሌ፣ የ«_gads» ኩኪ ጣቢያዎች የGoogle ማስታወቂያዎችን እንዲያሳዩ ያስችላቸዋል። በ«_gac_» የሚጀምሩ ኩኪዎች ከGoogle ትንታኔ የመጡ ሲሆኑ ማስታወቂያ ሰሪዎች የተጠቃሚ እንቅስቃሴን እና የማስታወቂያ ዘመቻዎቻቸውን አፈጻጸም ለመለካት ይጠቀሙባቸዋል። የ«_gads» ኩኪዎች ለ13 ወራት የሚቆይ ሲሆን የ«_gac_» ኩኪዎች ደግሞ ለ90 ቀናት ይቆያሉ።

አንዳንድ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች እርስዎ በሚጎበኙት ጣቢያ ላይ የGoogle ማስታወቂያዎችን የማስታወቂያ እና የዘመቻ አፈጻጸም እና የልወጣ ብዛቶችን ለመለካት ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለምሳሌ፣ በ«_gcl_» የሚጀምሩ ኩኪዎች በዋነኝነት ጥቅም ላይ የዋሉት በማስታወቂያዎቻቸው ላይ ጠቅ የሚያደርጉ ተጠቃሚዎች ስንት ጊዜ በጣቢያቸው ላይ እንደ ግዢ መፈጸም ያለ እርምጃ እንደወሰዱ እንዲወስኑ ማስታወቂያ ሰሪዎችን ለማገዝ ነው። የልወጣ ብዛቶችን ለመለካት ጥቅም ላይ የዋሉ ኩኪዎች ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ለማላበስ ጥቅም ላይ አይውሉም። የ«_gcl_» ኩኪዎች ለ90 ቀናት ይቆያሉ። እንዲሁም በAndroid መሣሪያዎች ላይ ያለ የማስታወቂያ መታወቂያ ያሉ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች የማስታወቂያ እና የዘመቻ አፈጻጸምን ለመለካት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። በAndroid መሣሪያዎ ላይየማስታወቂያ መታወቂያ ቅንብሮችዎን ማስተዳደር ይችላሉ።

ለማስታወቂያ ስራ ላይ ስለሚውሉ ኩኪዎች ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይመልከቱ።

ግላዊነት ማላበስ

ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ግላዊነት የተላበሰ ይዘትን ለማሳየት ጥቅም ላይ ይውላሉ። እነዚህ ኩኪዎች በg.co/privacytools ላይ ባሉ ቅንብሮች ወይም በእርስዎ መተግበሪያ እና መሣሪያ ቅንብሮች ላይ በመመሥረት ግላዊነት የተላበሰ ይዘትን እና ባህሪያትን በማቅረብ የእርስዎን ተሞክሮ ለማሻሻል ይረዳሉ።

ግላዊነት የተላበሰ ይዘት እና ባህሪዎች እንደ ይበልጥ አግባብነት ያላቸው ውጤቶች እና ምክሮች፣ ብጁ የYouTube መነሻ ገፅ እና ለእርስዎ ፍላጎቶች የተበጁ ማስታወቂያዎች ያሉ ነገሮችን ያካትታሉ። ለምሳሌ፣ የ«VISITOR_INFO1_LIVE» ኩኪ ባለፉ ዕይታዎች እና ፍለጋዎች ላይ በመመስረት በYouTube ላይ ግላዊነት የተላበሱ ምክሮችን ሊያነቃ ይችላል። እና እርስዎ የፍለጋ ቃላትን በሚተይቡበት ጊዜ የ«NID» ኩኪ በፍለጋ ውስጥ ግላዊነት የተላበሱ የራስ-ሰር አጠናቅቅ ባህሪያትን ያነቃል። እነዚህ ኩኪዎች ተጠቃሚው ለመጨረሻ ጊዜ ከተጠቀሙበት ጊዜ ጀምሮ ከ6 ወራት በኋላ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃል።

Google ለአካባቢዎ አግባብነት ያላቸውን ውጤቶች ለእርስዎ ማሳየት እንዲችል ሌላ ኩኪ የሆነው «UULE» ትክክለኛ የአካባቢ መረጃን ከአሳሽዎ ወደ የGoogle አገልጋዮች ይልካል። የዚህ ኩኪ አጠቃቀም በአሳሽዎ ቅንብሮች እና ለአሳሽዎ አካባቢ እንዲበራ መምረጥዎ ወይም አለመምረጥዎ ላይ የተመሰረተ ነው። የ«UULE» ኩኪ እስከ 6 ሰዓታት ድረስ ይቆያል።

ምንም እንኳን ግላዊነት ለማላበስ ጥቅም ላይ የዋሉ ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሊጂዎችን ውድቅ ቢያደርጉም እርስዎ የሚያዩት ግላዊነት ያልተላበሰ ይዘት እና ባህሪያት እንደ የእርስዎ አካባቢ፣ ቋንቋ፣ የመሣሪያ ዓይነት ወይም አሁን እያዩት ያሉት ይዘት ባሉ ዓውዳዊ ምክንያቶች ተጽዕኖ ሊደስርባቸው ይችላል።

በአሳሽዎ ውስጥ ኩኪዎችን ማቀናበር

አብዛኛዎቹ አሳሾች እርስዎ ሲያስሱ ኩኪዎች እንዴት እንደሚቀናበሩ እና ጥቅም ላይ እንደሚውሉ እንዲያስተዳድሩ እና ኩኪዎችን እና የአሰሳ ውሂብን እንዲያጸዱ ያስችሉዎታል። እንዲሁም የእርስዎ አሳሽ ኩኪዎችን እንደ ጣቢያ በጣቢያ እያዩ እንዲያስተዳድሩ የሚያስችልዎ ቅንብሮች ሊኖሩት ይችላል። ለምሳሌ፣ chrome://settings/cookies ላይ የGoogle Chrome ቅንብሮች ነባር ኩኪዎችን እንዲሰርዙ፣ ሁሉንም ኩኪዎች እንዲፈቅዱ ወይም እንዲያግዱ እና ለድር ጣቢያዎች የኩኪ አማራጮችን እንዲያቀናብሩ ያስችልዎታል። እንዲሁም Google Chrome ማንነት የማያሳውቅ ሁነታን ያቀርባል፣ ይህም ማንነት የማያሳውቅ ሁነታ መስኮቶችዎን ከዘጉ በኋላ በመሣሪያዎ ላይ የአሰሳ ታሪክዎን ይሰርዛል እና ኩኪዎችን ያጸዳል።

በእርስዎ መተግበሪያዎች እና መሣሪያዎች ውስጥ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዳደር

አብዛኛዎቹ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎች እና መተግበሪያዎች እንደ መተግበሪያ ወይም መሣሪያ ለመለየት ጥቅም ላይ የዋሉ ልዩ ለዪዎች ያሉ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች እንዴት እንደሚቀናበሩ እና ጥቅም ላይ እንደሚውሉ እንዲያስተዳድሩ ያስችልዎታል። ለምሳሌ፣ በAndroid መሣሪያዎች ላይ ያሉ የማስታወቂያ መታወቂያው ወይም የApple የማስታወቂያ ለዪ በመሣሪያዎ ቅንብሮች ውስጥ ሊተዳደሩ የሚችሉ ሲሆን መተግበሪያ-ተኮር ለዪዎች በተለምዶ በመተግበሪያው ቅንብሮች ውስጥ ሊተዳደሩ ይችላሉ።

ዋናው ምናሌ
Google መተግበሪያዎች