ጉግል ድምጽ እንዴት እንደሚሰራ

Google ድምጽ አገልግሎቱን ለእርስዎ ለማቅረብ የጥሪ ታሪክዎን (የጠሪ አካል ስልክ ቁጥር፣ የተጠሪ አካል ስልክ ቁጥር፣ ቀን፣ ሰዓት እና የጥሪ ርዝመት ጨምሮ)፣ የድምጽ መልዕክት ሰላምታዎ(ችዎ)ን፣ የድምጽ መልዕክቶችዎን፣ የአጭር መልዕክት አገልግሎት (ኤስ ኤም ኤስ) መልዕክቶችዎን፣ የተቀዱ ውይይቶችዎን፣ እና ሌላ ከመለያዎ ጋር የሚገናኝ ውሂብ ያከማቻል፣ ያስሄዳል እና ያቆያል።

ምንም እንኳ ለሚከፈልባቸው ጥሪዎች የእርስዎ የጥሪ ታሪክ በእርስዎ መለያ ላይ እየታየ መቀጠሉ እንዳለ ቢሆንም የጥሪ ታሪክዎን፣ የድምፅ መልእክት ሰላምታዎ(ችዎ)ን፣ የድምፅ መልእክት መልእክቶችዎን (ሁለቱም ኦዲዮ እና/ወይም የድምፅ በጽሑፍ ግልባጮች)፣ የአጭር መልእክት አገልግሎት (ኤስ ኤም ኤስ) መልእክቶችዎን፣ እና የተቀዱ ውይይቶችዎን በእርስዎ የGoogle ድምፅ መለያ ሊሰርዟቸው ይችላሉ። ለክፍያ መጠየቂያ ወይም ሌላ ንግድ ነክ ዓላማዎች አንዳንድ መረጃዎች በእኛ ንቁ አገልጋዮች ላይ በጊዜያዊነት ሊቀሩ እና ቀሪ ቅጂዎች በምትኬ ሥርዓቶቻችን ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ። ምንም በግል ሊለዩ የሚያስችሉ መረጃ የሌላቸው ስም-አልባ የተደረጉ የጥሪ መዝገብ መረጃዎች ቅጂዎች የሪፖርት ማድረግ እና የኦዲቲንግ መስፈርቶቻችንን ለማሟላት በሥርዓቶቻችን ውስጥ ይቀራሉ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ