ትርጓሜዎች

መካስ ወይም ካሳ

የአንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ ክሶች ባሉ የህግ ስርዓቶች ምክንያት ከሚከሰቱ ጥፋቶች መከላከል ያለባቸው የውል ግዴታ።

ሸማች

የGoogle አገልግሎቶችን ከንግዳቸው፣ ጥበባቸው ወይም ሙያቸው ውጭ ለግልና ለንግድ ላልሆኑ ዓላማዎች የሚጠቀም ግለሰብ። (የንግድ ሥራ ተጠቃሚ የሚለውን ይመልከቱ)

ተጠያቂነት

አቤቱታው በውል ላይ በመመርኮዝ፣ በጥፋት (ቸልተኝነትን ጨምሮ)፣ ወይም ሌላ ምክንያት የሚነሣ የሕጋዊ ይገባኛል ጥያቄ ማናቸውም ዓይነት የተነሣ የሚፈጠሩ ኪሳራዎች እና እነዚህ ኪሳራዎች በአግባቡ አስቀድሞ ሊታሰብባቸው ወይም ሊገመቱ ይችሉ የነበሩ ይሁኑ ወይም አይሁኑ።

አገልግሎቶች

የGoogle አገልግሎቶች https://policies.google.com/terms/service-specific ላይ የተዘረዘሩ ምርቶች እና አገልግሎቶች ናቸው፣ እነዚህንም ጨምሮ፦

 • Google መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች (እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች ያሉ)
 • መድረኮቸ (እንደ Google Play)
 • የተዋሃዱ አገልግሎቶች (እንደ በሌሎች ኩባንያዎች መተግበሪያዎች ወይም ጣቢያዎች ላይ የተከተተ ካርታዎች ያሉ)
 • መሣሪያዎች (እንደ Google Home ያለ)

አጋር

የGoogle የኩባንያዎች ቡድን አባል የሆነ ተቋም ማለትም Google LLC እና የበታች መሥሪያ ቤቶቹ፣ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የደንበኛ አገልግሎት የሚያቀርቡ የሚከተሉትን ኩባንያዎች ጨምሮ፦ Google Ireland Limited፣ Google Commerce Ltd፣ እና Google Dialer Inc.።

ዋስትና

አንድ ምርት ወይም አገልግሎት በተወሰነ ደረጃ መሠረት እንደሚሠራ የሚሰጥ ዋስትና።

የቅጂ መብት

ኦርጂናሉ ሥራ (ለምሳሌ የጦማር ልጥፍ፣ ፎቶ ወይም ቪዲዮ) በሌሎች እንዴት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በኦርጂናል ሥራ ፈጣሪው እንዲወስን የሚያስችለው ሕጋዊ መብት።

የኃላፊነት መግለጫ

የአንድን ሰው ሕጋዊ ግዴታዎች የሚገድብ ዐርፍተ ነገር።

የንግድ ምልክት

የአንድ ግግለሰብ ወይም ድርጅት ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ከሌላኛው መለየት የሚችሉ በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች።

የንግድ ተጠቃሚ

ሸማች (ሸማች ይመልከቱ) ያልሆነ ግለሰብ ወይም ህጋዊ አካል።

የአህ መድረክ ለንግድ ቁጥር

ለመስመር ላይ የመሃል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለሆኑ የንግድ ተጠቃሚዎች ፍትሐዊነትን እና ግልጽነትን ማስተዋወቅ ላይ ያለው ደንብ (አህ) 2019/1150።

የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች (IP መብቶች)

እንደ የመፈልሰፍ ፈጠራዎች (የፓተንት መብቶች)፤ የስነ ጽሑፋዊ እና ኪነ ጥበባዊ ስራዎች (ቅጂ መብት)፤ ንድፎች (የንድፍ መብቶች)፤ እና በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች (የንግድ ምልክቶች) ባሉ የአንድ ሰው አዕምሯዊ ፈጠራዎች ላይ ያሉ መብቶች። የአዕምሯዊ መብቶች የእርስዎ፣ የሌላ ግለሰብ ወይም የአንድ ድርጅት ሊሆኑ ይችላሉ።

የእርስዎ ይዘት

እርስዎ የሚጽፏቸውን፣ የሚሰቅሏቸውን፣ የሚያስገቧቸውን፣ የሚያከማቿቸውን፣ የሚልኳቸውን፣ የሚቀበሏቸውን ወይም የእኛን አገልግሎቶች በመጠቀም ከGoogle ጋር የሚያጋሯቸውን እንደ የሚከተሉት ያሉት ነገሮች፦

 • እርስዎ የሚፈጥሯቸው ሰነዶች፣ ሉሆች እና ስላይዶች
 • በጦማሪ በኩል የሚሰቅሏቸው የጦማር ልጥፎች
 • በካርታዎች ላይ የሚያስገቧቸው ግምገማዎች
 • በDrive ላይ የሚያከማቿቸው ቪዲዮዎች
 • በGmail በኩል እርስዎ የሚልኳቸው እና የሚቀበሏቸው ኢሜይሎች
 • በፎቶዎች በኩል ለጓደኛዎች የሚያጋሯቸው ስዕሎች
 • ለGoogle የሚያጋሯቸው የጉዞ ዕቅዶች

ድርጅት

ሕጋዊ ተቋም (እንደ ማህበር፣ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት ወይም ትምህርት ቤት) እና ግለሰብ ያልሆነ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ