ይሄ በማህደራችን የተመዘገበ የግላዊነት ፖሊሲያችን ስሪት ነው። ያሁኑን ስሪት ወይም ሁሉንም ያለፉት ስሪቶች እይ።

የGoogle የግላዊነት መመሪያ

አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ በመረጃዎ ረገድ እኛ ላይ እምነት እያሳደሩ ነው። ይህ ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን እንገነዘባለን፣ እና መረጃዎን ለመጠበቅ እና እርስዎን ተቆጣጣሪ ለማድረግ ተግተን እንሰራለን።

ይህ የግላዊነት መመሪያ ምን መረጃ እንደምንሰበስብ፣ ለምን እንደምንሰበስብ፣ እና እንዴት መረጃዎን ማዘመን፣ ማቀናበር፣ ወደ ውጭ መላክ እና መሰረዝ እንደሚችሉ እንዲረዱ ለማገዝ ያለመ ነው።

የግላዊነት ፍተሻ

የእርስዎን የግላዊነት ቅንብሮች ለመለወጥ እየፈለጉ ነው?

የግላዊነት ፍተሻውን ውሰድ

ውጤታማ 28 ኦገስት 2020 | የታቆሩ ስሪቶች | ፒዲኤፍ አውርድ

በየቀኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዓለምን አዲስ በሆኑ መንገዶች እንዲያስሱ እና ከእሱ ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ የሚያገዙ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንገነባለን። የእኛ አገልግሎቶች እነዚህን ያካትታሉ፦

  • እንደ ፍለጋ፣ YouTube እና Google Home ያሉ የGoogle መተግበሪያዎች፣ ጣቢያዎች እና መሣሪያዎች
  • እንደ የChrome አሳሽ እና የAndroid ስርዓተ ክወና ያሉ የመሣሪያ ስርዓቶች
  • እንደ ማስታወቂያዎች እና የተከተቱ የGoogle ካርታዎች ያሉ ከሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች የተዋሃዱ ምርቶች

ግላዊነትዎን ለማቀናበር አገልግሎታችንን በተለያዩ መንገዶች ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ለምሳሌ፣ እንደ ኢሜይሎች እና ፎቶዎች ያሉ ይዘቶችን መፍጠርና ማቀናበር ከፈለጉ፣ ወይም ይበልጥ ተዝማጅ የሆኑ የፍለጋ ውጤቶችን መመልከት ከፈለጉ ለGoogle መለያ መመዝገብ ይችላሉ። እና እንደ በGoogle ላይ መፈለግ ወይም የYouTube ቪዲዮዎችን መመልከት ያሉ ዘግተው ሲወጡ ወይም መለያ በጭራሽ ሳይፈጥሩ ብዙ የGoogle አገልግሎቶችን መጠቀም ይችላሉ። እንዲሁም Chromeን ማንነት በማያሳውቅ ሁነታ ላይ ተጠቅመው ድርን በግል ማሰስ ይችላሉ። እና እኛ ምን እንደምንሰበስብ እና መረጃዎ እንዴት ስራ ላይ እንደሚውል ለመቆጣጠር በመላ አገልግሎቶቻችን ላይ የግላዊነት ቅንብሮችዎን ማስተካከል ይችላሉ።

ነገሮችን በተቻል መጠን ግልጽ አድርጎ ለማብራራት ምሳሌዎችን፣ ማብራሪያ ቪዲዮዎችን እና የቁልፍ ቃላት ፍቺዎችን አክለናል። እና ስለዚህ ግላዊነት መመሪያ ማናቸውም ጥያቄዎች ካለዎት ሊያነጋግሩን ይችላሉ።

Google የሚሰበስበው መረጃ

አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ እኛ የምንሰበስበው የመረጃ አይነቶችን እንዲረዱ እንፈልጋለን

ለሁሉም ተጠቃሚዎቻችን የተሻሉ አገልግሎቶችን ለማቅረብ – እንደ እርስዎ የትኛውን ቋንቋ እንደሚናገሩ ካሉ መሠረታዊ ነገሮች ጀምሮ እስከ እንደ የትኛዎቹ ማስታወቂያዎች እርስዎ ጠቃሚ ሆነው እንደሚያገኟቸውበመስመር ላይ ከማንም በላይ ለእርስዎ ፋይዳ ያላቸው ሰዎች ወይም የትኞቹን የYouTube ቪዲዮዎች እርስዎ ሊወዷቸው እንደሚችሉ ያሉ ውስብስብ ነገሮች ማወቅ ድረስ – መረጃ እንሰበስባለን። Google የሚሰበስበው መረጃ እና ይህ መረጃ እንዴት ስራ ላይ እንደሚውል በአገልግሎታችን አጠቃቀምዎ እና እንዴት የግላዊነት መቆጣጠሪያዎችን እንደሚያቀናብሩ ላይ የሚወሰን ነው።

ወደ አንድ የGoogle መለያ ሲገቡ የምንሰበስበው መረጃ ከሚጠቀሙበት አሳሽ፣ መተግበሪያ ወይም መሣሪያ ጋር በተሳሰሩ ልዩ ለዪዎች እናከማቻለን። ይህ በተለያዩ የአሰሳ ክፍለ-ጊዜዎች ላይ እንደ የቋንቋ ምርጫዎችዎ ያሉ ነገሮችን ይዘት እንድናቆይ ያግዘናል።

በመለያ ሲገቡ እንዲሁም እንደ በGoogle መለያዎ ላይ የምናከማቸው የግል መረጃ የምንቆጥረውን መረጃ እንሰበስባለን።

እርስዎ የሚፈጥሯቸው ወይም ለእኛ የሚያጋሯቸው ነገሮች

የGoogle መለያ ሲፈጥሩ የእርስዎን ስም እና የይለፍ ቃል የሚያካትት የግል መረጃ ያቀርቡልናል። እንዲሁም በመለያዎ ላይ ስልክ ቁጥር ወይም የክፍያ መረጃ ለማከል መምረጥ ይችላሉ። ወደ የGoogle መለያ ባይገቡም እንኳ መረጃ ለእኛ ለመስጠት ሊመርጡ ይችላሉ — ለምሳሌ ስለአገልግሎታችን ዝማኔዎችን የሚቀበሉበት የኢሜይል አድራሻ።

እንዲሁም አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ የሚፈጥሩት፣ የሚሰቅሉት ወይም ከሌሎች የሚቀበሉት ይዘት እንሰበስባለን። ይህ እንደ የሚጽፉትና የሚቀበሉት ኢሜይል፣ የሚያስቀመጧቸው ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች፣ የሚፈጥሯቸው ሰነዶች እና ተመን ሉሆች እና በYouTube ቪዲዮዎች ላይ የሚሰጧቸው አስተያየቶች ያሉ ነገሮችን ያካትታል።

አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ እኛ የምንሰበስበው መረጃ

የእርስዎ መተግበሪያዎች፣ አሳሾች እና መሣሪያዎች

እርስዎ የGoogle አገልግሎቶችን ለመድረስ ስለሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች፣ አሳሾች እና መሣሪያዎች መረጃ እንሰበስባለን፣ ይህም እንደ ራስ-ሰር የምርት ዝማኔዎች እና የባትሪዎ ኃይል ዝቅተኛ ሲሆን ማያዎን ማደብዘዝ ያሉ ባህሪዎችን እንድናቀርብ ያግዘናል።

የምንሰበስበው መረጃ ልዩ ለዪዎች፣ የአሳሽ አይነት እና ቅንብሮች፣ የመሣሪያ አይነት እና ቅንብሮች፣ ስርዓተ ክወና፣ የአገልግሎት አቅራቢ ስም እና ስልክ ቁጥር ጨምሮ የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ መረጃ፣ እና የመተግበሪያ ስሪት ቁጥርን ያካትታል። እንዲሁም የአይፒ አድራሻ፣ የብልሽት ሪፖርቶች፣ የስርዓት እንቅስቃሴ እና የጥያቄዎ ቀን፣ ሰዓት እና የጠቃሽ ዩአርኤል ጨምሮ የእርስዎ መተግበሪያዎች፣ አሳሾች እና መሣሪያዎች ከአገልግሎቶቻችን ጋር ያላቸውን የመስተጋብር መረጃንም እንሰበስባለን።

ይህን መረጃ የምንሰበስበው በመሣሪያዎ ላይ ያለ አንድ የGoogle አገልግሎት አገልጋዮቻችን ሲያገኝ ነው — ለምሳሌ፣ ከPlay መደብር አንድ መተግበሪያ ሲጭኑ ወይም አንድ አገልግሎት ራስ-ሰር ዝማኔዎችን ሲፈትሽ። የGoogle መተግበሪያዎች ያለው የAndroid መሣሪያ እየተጠቀሙ ከሆኑ መሣሪያዎ በየጊዜው ስለመሣሪያዎ እና ከአገልግሎቶቻችን ጋር ስላለው ግንኙነት መረጃ ለማቅረብ በየጊዜው የGoogle አገልጋዮችን ያገኛል። ይህ መረጃ እንደ የእርስዎ የመሣሪያ አይነት፣ የአገልግሎት አቅራቢ፣ የብልሽት ሪፖርቶች እና የትኛዎቹን መተግበሪያዎች እንደጫኑ ያሉ ነገሮችን ያካትታል።

የእርስዎ እንቅስቃሴ

በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ስላለው እንቅስቃሴዎ መረጃ እንሰበስባለን፣ ይህም እንደ እርስዎ ሊወዱት የሚችሉት የYouTube ቪዲዮን መምከር ያሉ ነገሮችን እንድናደርግ ያስችለናል። ልንሰበስበው የምንችለው የእንቅስቃሴ መረጃ እነዚህን ያካትታል፦

ጥሪዎችን ለማድረግ እና ለመቀበል ወይም መልዕክቶችን ለመላክ እና ለመቀበል አገልግሎቶቻችንን የሚጠቀሙ ከሆኑ እንደ ስልክ ቁጥርዎ፣ የደዋዩ ስልክ ቁጥር፣ የተቀባይ ቁጥር፣ የማስተላለፊያ ቁጥሮች፣ የጥሪዎች እና መልዕክቶች ሰዓት እና ቀን፣ የጥሪው ቆይታ ጊዜ፣ የማዛወሪያ መረጃ እና የጥሪዎች አይነቶች ያሉ የስልክ ምዝግብ መረጃዎችን ልንሰበስብ እንችላለን።

በመለያዎ ውስጥ የተቀመጠውን የእንቅስቃሴ መረጃ ለማግኘትና ለማቀናበር የGoogle መለያዎን መጎብኘት ይችላሉ።

ወደ የGoogle መለያ ይሂዱ

የአካባቢዎ መረጃ

አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ ስለአካባቢዎ መረጃ እንሰበስባለን፣ ይህም እንደ ለሳምንት እረፍት ቀንዎ የሆነ የመኪና መንዳት አቅጣጫዎች ወይም ከእርስዎ አጠገብ የሚታዩ የፊልሞች መታያ ሰዓቶች ያሉ ባህሪያትን እንድናቀርብ ያግዘናል።

የእርስዎ አካባቢ በሚከተሉት አማካኝነት በተለያየ የትክክለኝነት ደረጃ ሊታወቅ ይችላል፦

የምንሰበስበው የአካባቢ ውሂብ አይነቶች በከፊል በእርስዎ የመሣሪያ እና የመለያ ቅንብሮች ላይ የሚወሰኑ ናቸው። ለምሳሌ፣ የመሣሪያዎን የቅንብሮች ውሂብ ተጠቅመው የAndroid መሣሪያን አካባቢ ጠቋሚ ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ። እንዲሁም በመለያ ከገቡባቸው መሣሪያዎችዎ የሚሄዱባቸውን ቦታዎች የግል ካርታ መፍጠር ከፈለጉ የአካባቢ ታሪክን ማብራት ይችላሉ።


በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ Google እንዲሁም ስለእርስዎ ያሉ መረጃዎች በይፋ ሊደረስባቸው ከሚችሉ ምንጮች ይሰበስባል። ለምሳሌ፣ የእርስዎ ስም በአካባቢያዊ ጋዜጣ ላይ ከታየ የGoogle ፍለጋ ፕሮግራም ያንን ዘገባ መረጃ ጠቋሚ ሊያሰናዳለትና ሌሎች ሰዎች ስምዎን ከፈለጉ እሱን ሊያሳያቸው ይችላል። እንዲሁም የንግድ አገልግሎቶቻችን ሊፈልጉ ስለሚችሉ ደንበኛዎች መረጃ የሚያቀርቡልን የገበያ ስራ አጋሮች እና በደልን ለመከላከል መረጃ የሚያቀርቡልን የደህንነት አጋሮች ጨምሮ ከታመኑ አጋሮች ስለእርስዎ ያለ መረጃ ሊሰበስብ ይችላል። እንዲሁም ማስታወቂያን እና እነሱን በመወከል የጥናት አገልግሎቶችን ለማቅረብ ከማስታወቂያ ሰሪዎች መረጃ ልንቀበልም እንችላለን።

ኩኪዎችየፒክስል መለያዎች፣ እንደ የአሳሽ ድር ማከማቻ ወይም የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫዎች ያለ አካባቢያዊ ማከማቻ፣ የውሂብ ጎታዎች እና የአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች ጨምሮ መረጃን ለመሰብሰብ እና ለማከማቸት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን።

Google ለምን ውሂብ እንደሚሰበስብ

የተሻሻሉ አገልግሎቶችን ለመገንባት ውሂብን እንጠቀማለን

ከሁሉም አገልግሎቶቻችን የምንሰበስበው መረጃ ለሚከተሉት ዓላማዎች እንጠቀምባቸዋለን፦

አገልግሎቶቻችንን ማቅረብ

መረጃዎን እንደ ውጤቶችን ለመመለስ የሚፈልጓቸውን ቃላት ማስሄድ ወይም ከእውቂያዎችዎ ተቀባዮችን በመጠቆም ይዘት እንዲያጋሩ ያሉ አገልግሎቶቻችንን ለማድረስ እንጠቀምበታለን።

አገልግሎቶቻችንን ማቆየት እና ማሻሻል

እንዲሁም መረጃዎን እንደ መብራት የጠፋባቸው አካባቢዎችን መከታተል ወይም ለእኛ ሪፖርት ለሚያደርጓቸው ችግሮች መላ መፈለግ ያሉ አገልግሎቶቻችን እንደታሰበው መስራቱን ለማረጋገጥ እንጠቀምበታለን። እና መረጃዎን በአገልግሎቶቻችን ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ እንጠቀምበታለን — ለምሳሌ፣ የተኛዎቹ የፍለጋ ቃላት በተደጋጋሚነት በተሳሳተ ፊደል እንደሚጻፉ መረዳት በመላ አገልግሎቶቻችን ላይ የፊደል ማረሚያ ባህሪያትን እንድናሻሽል ያግዘናል።

አዳዲስ አገልግሎቶችን መገንባት

በነባር አገልግሎቶቻችን ውስጥ የምንሰበስበው መረጃ አዳዲስ አገልግሎቶችን እንድንገነባ እንዲያግዘን እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ ሰዎች የመጀመሪያው የGoogle ፎቶዎች መተግበሪያ በሆነው Picasa ውስጥ ፎቶዎቻቸውን እንዴት እንዳደራጁ መረዳት Google ፎቶዎችን ለመንደፍ እና ለማስጀመር አግዞናል።

ይዘት እና ማስታወቂያዎችን ጨምሮ ግላዊነት የተላበሱ አገልግሎቶችን ማቅረብ

የምንሰበስበው መረጃ ምክሮችን፣ ግላዊነት የተላበሰ ይዘትን እና ብጁ የፍለጋ ውጤቶችን ጨምሮ አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ ለማበጀት እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ የደህንነት ፍተሻ የGoogle ምርቶችን ለሚጠቀሙበት አጠቃቀም የተበጀ ጠቃሚ የደህንነት ምክሮችን ማቅረብ። እና Google Play እርስዎ ሊወዷቸው የሚችሏቸው አዳዲስ መተግበሪያዎችን ለመጠቆም እንደ አስቀድመው የጫኗቸው መተግበሪያዎች እና በYouTube ላይ የተመለከቷቸው ቪዲዮዎች ያለ መረጃን ሊጠቀም ይችላል።

በቅንብሮችዎ የሚወሰን ሆኖ እንዲሁም በፍላጎቶችዎ ላይ በመመስረት ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ልናሳየዎት እንችላለን። ለምሳሌ፣ «የተራራ ቢስክሌት»ን ከፈለጉ በGoogle የሚቀርቡ ማስታወቂያዎችን የሚያሳዩ ጣቢያዎችን ሲያስሱ የስፖርት መገልገያዎች ማስታወቂያ ሊመለከቱ ይችላሉ። የማስታወቂያ ቅንብሮችዎን በመጎብኘት እኛ ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ምን መረጃ እንደምንጠቀም መቆጣጠር ይችላሉ።

  • እንደ ዘር፣ ኃይማኖት፣ ጾታዊ ዝንባሌ ወይም ጤና ባሉ ሚስጥራዊነት ባላቸው ምድቦች ላይ የተመሠረቱ ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን አናሳይዎትም።
  • ካልጠየቁን በስተቀር እንደ የእርስዎ ስም ወይም ኢሜይል ያለ እርስዎን በግል ለማስታወቂያ ሰሪዎች የሚያስለይ መረጃን አናጋርም። ለምሳሌ፣ በአቅራቢያ ያለ የአበባ መሸጫ ማስታወቂያ ከተመለከቱና የ«ለመደወል መታ አድርግ» አዝራሩን ከመረጡ ጥሪዎን እናገናኘውና ስልክ ቁጥርዎን ለአበባ መሸጫው ልናጋራው እንችላለን።

ወደ የማስታወቂያ ቅንብሮች ይሂዱ

አፈጻጸም መለካት

አገልግሎቶቻችን እንዴት ስራ ላይ እንደሚውሉ ለመረዳት ውሂብን ለትንታኔ እና ለመለካት እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ እንደ የምርት ንድፍን ማትባት ያሉ ነገሮች እንድናደርግ በጣቢያዎቻችን ላይ ስላደረጓቸው ጉብኝቶች ያለ ውሂብ እንተነትናለን። እንዲሁም ማስታወቂያ ሰሪዎች የማስታወቂያ ዘመቻዎቻቸው አፈጻጸም እንዲረዱ ለማገዝ መስተጋብር ስለሚፈጥሩባቸው ማስታወቂያ ውሂብም እንጠቀማለን። ይህን ለማድረግ Google ትንታኔዎችም ጨምሮ የተለያዩ መሣሪያዎችን እንጠቀማለን። Google ትንታኔዎችን የሚጠቀሙ ጣቢያዎችን ሲጎበኙ Google እና የGoogle ትንታኔዎች ደንበኛ ከዚያ ጣቢያ የመጣ የእንቅስቃሴ መረጃዎን የማስታወቂያ አገልግሎቶቻችንን ከሚጠቀሙ ሌሎች ጣቢያዎች የመጣ እንቅስቃሴን ሊያገናኝ ይችላል።

ከእርስዎ ጋር ግንኙነት መፍጠር

እንደ የኢሜይል አድራሻዎ ያለ የምንሰበስበው መረጃ በቀጥታ ከእርስዎ ጋር መስተጋብር ለመፍጠር እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ እንደ ካልተለመደ አካባቢ ሆኖ ወደ የGoogle መለያዎ የመግባት ሙከራ ያለ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ካገኘን ለእርስዎ ማሳወቂያ ለመላክ። ወይም ደግሞ በአገልግሎቶቻችን ላይ ስለሚመጡ ለውጦች ወይም ማሻሻያዎች ልናሳውቀዎት እንችላለን። እና Googleን ካነጋገሩ እያጋጠመዎት ያሉ ማናቸውም ችግሮችን እንዲፈቱ ለማገዝ የጥያቄዎን መዝገብ እናስቀምጣለን።

Googleን፣ ተጠቃሚዎቻችን እና ሕዝብን መጠበቅ

የአገልግሎቶቻችንን ደህንነት እና አስተማማኝነት ለማሻሻል መረጃን እንጠቀማለን። ይህ Googleን፣ ተጠቃሚዎቻችን ወይም ሕዝብን ሊጎዱ የሚችሉ ማጭበርበር፣ አላግባብ መጠቀም፣ የደህነንት ስጋቶች እና ቴክኒካዊ ችግሮችን ማግኘት፣ መከላከል እና ለእነሱ አጸፋ መስጠትን ያካትታል።


መረጃዎን ለእነዚህ ዓላማዎች ለማስሄድ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። እንደ ብጁ የፍለጋ ውጤቶች፣ ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎች ወይም ለአገልግሎቶቻችን አጠቃቀምዎ የተበጁ ሌሎች ባህሪያትን ያሉ ነገሮችን ለእርስዎ ለማቅረብ ይዘትዎን የሚተነትኑ ራስ-ሰር ስርዓቶችን እንጠቀማለን። እና እንደ አይፈለጌ መልዕክት፣ ተንኮል-አዘል ዌር እና ህገወጥ ይዘት ያለ አላግባብ መጠቀምን እንድናገኝ እንዲያግዘን ይዘትዎን እንተነትነዋለን። እንዲሁም በውሂብ ውስጥ ስርዓተ-ጥለቶችን ለማግኘት ስልተ-ቀመሮችን እንጠቀማለን። ለምሳሌ፣ Google ትርጉም እርስዎ እንዲተረጉምልዎ በሚጠይቋቸው ሐረጎች ውስጥ ያሉ የተለመዱ የቋንቋ ስርዓተ-ጥለቶችን በማግኘት ሰዎች በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲግባቡ ያግዛቸዋል።

ከላይ ለተጠቀሱት ዓላማዎች ሲባል ከእኛ አገልግሎቶች እና ከመላ መሣሪያዎችዎ የምንሰበስበውን መረጃ ልናጣምር እንችላለን። ለምሳሌ በYouTube ላይ የጊታር ተጫዋቾች ቪዲዮዎችን የሚመለከቱ ከሆኑ የማስታወቂያ ምርቶቻችንን በሚጠቀም አንድ ጣቢያ ላይ የጊታር ትምህርት ማስታወቂያን ሊመለከቱ ይችላሉ። በእርስዎ የመለያ ቅንብሮች የሚወሰን ሆኖ በሌሎች ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ ያለው እንቅስቃሴዎ የGoogle አገልግሎቶችን እና በGoogle የሚላኩ ማስታወቂያዎችን ለማሻሻል ከግል መረጃዎ ጋር ሊጎዳኝ ይችላል።

ሌሎች ተጠቃሚዎች አስቀድመው የእርስዎ ኢሜይል አድራሻ ወይም እርስዎን ለይቶ የሚያሳውቅ ሌላ መረጃ ካላቸው በይፋ የሚታዩትን እንደ ስምዎ እና ፎቶዎ ያሉ የእርስዎን የGoogle መለያ መረጃዎች ልናሳያቸው እንችላለን። ይህ ለምሳሌ ሰዎች ከእርስዎ የሚመጣ ኢሜይል ካለ እንዲለዩ ያግዛቸዋል።

መረጃዎን በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ ላልተሸፈነ ዓላማ ከመጠቀማችን በፊት የእርስዎን ፈቃድ እንጠይቃለን።

የእርስዎ የግላዊነት መቆጣጠሪያዎች

የምንሰበስበው መረጃና እንዴት እንደምንጠቀምበት በተመለከተ ምርጫዎች አለዎት

ይህ ክፍል በመላ አገልግሎቶቻችን ላይ ግላዊነትዎን የሚያቀናብሩባቸው ቁልፍ መቆጣጠሪያዎችን ይገልጻል። እንዲሁም አስፈላጊ የግላዊነት ቅንብሮችን የመገምገም እና የማስተካከል ዕድል የሚሰጠውን የግላዊነት ፍተሻን መጎብኘት ይችላሉ። ከእነዚህ መሣሪያዎች በተጨማሪም እንዲሁም በምርቶቻችን ውስጥ የተወሰኑ የግላዊነት ቅንብሮች እናቀርባለን — በእኛ የምርት ግላዊነት መመሪያ ውስጥ የበለጠ መረዳት ይችላሉ።

ወደ የግላዊነት ፍተሻ ይሂዱ

መረጃዎን ማቀናበር፣ መገምገም እና ማዘመን

በመለያ ሲገቡ የሚጠቀሙባቸውን አገልግሎቶች በመጎብኘት በማንኛውም ጊዜ መረጃን መገምገም እና ማዘመን ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ሁለቱም ፎቶዎች እና Drive በGoogle ላይ ያስቀመጧቸውን የተወሰኑ የይዘት አይነቶችን እንዲያቀናብሩ የተነደፉ ናቸው።

እንዲሁም እርስዎ በGoogle መለያዎ ውስጥ ያስቀመጡትን መረጃ የሚገመግሙበት እና የሚቆጣጠሩበት ቦታም ገንብተናል። የእርስዎ Google መለያ እነዚህን ያካትታል፦

የግላዊነት መቆጣጠሪያዎች

የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች

ምን አይነት እንቅስቃሴ በመለያዎ ላይ እንዲቀመጥ እንደሚፈልጉ ይወስኑ። ለምሳሌ፣ የዕለታዊ መጓጓዣዎ የትራፊክ ግምቶችን ከፈለጉ የአካባቢ ታሪክን ማብራት ይችላሉ፣ ወይም ደግሞ የተሻሉ የቪዲዮ አስተያየት ጥቆማዎችን ለማግኘት የYouTube እይታ ታሪክዎን ማስቀመጥ ይችላሉ።

ወደ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ይሂዱ

የማስታወቂያ ቅንብሮች

በGoogle እና ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከGoogle ጋር አጋር በሚሆኑ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ የሚታዩ የማስታወቂያዎች ምርጫዎችዎን ያቀናብሩ። የእርስዎን ፍላጎቶች መቀየር፣ ማስታወቂያዎን ለእርስዎ ተገቢነት ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ የእርስዎ መረጃ ጥቅም ላይ ይውል እንደሆነ መምረጥ እና የተወሰኑ የማስታወቂያ ስራ አገልግሎቶችን ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ።

ወደ የማስታወቂያ ቅንብሮች ይሂዱ

ስለእርስዎ

ሌሎች በመላይ የGoogle አገልግሎቶች ላይ ስለእርስዎ ምን እንደሚመለከቱ ይቆጣጠሩ።

ወደ ስለእርስዎ ይሂዱ

በጋራ ድጋፍ የተደረገበት

የእርስዎ ስም እና ፎቶ በማስታወቂያዎች ውስጥ በሚታዩ እንደ ግምገማዎች እና ምክሮች ካለ እንቅስቃሴዎ አጠገብ ይታዩ እንደሆነ ይምረጡ።

በጋራ ድጋፍ ወደተደረገበት ይሂዱ

የሚያጋሩት መረጃ

እርስዎ የG Suite ተጠቃሚ ከሆኑ በGoogle+ ላይ ባለው መለያዎ አማካኝነት ለማን መረጃ እንደሚያጋሩ ይቆጣጠሩ።

ወደ የሚያጋሩት መረጃ ይሂዱ

መረጃዎን የሚገመግሙባቸው እና የሚያዘምኑባቸው መንገዶች

የእኔ እንቅስቃሴ

የእኔ እንቅስቃሴ እርስዎ እንደ ያከናወኗቸው ፍለጋዎች ወይም Google Playን ሲጎበኙ ያሉ የGoogle አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ የሚፈጠር ውሂብን እንዲገመግሙና እንዲቆጣጠሩ ያስችልዎታል። በቀን እና ርዕስ ማሰስ፣ እና ከፊል ወይም ሙሉ እንቅስቃሴዎን መሰረዝ ይችላሉ።

ወደ የእኔ እንቅስቃሴ ሂድ

Google ዳሽቦርድ

Google ዳሽቦርድ ከተወሰኑ ምርቶች ጋር የተጎዳኘ መረጃን እንዲያቀናብሩ ያስችልዎታል።

ወደ ዳሽቦርድ ሂድ

የግል መረጃዎ

እንደ የእርስዎ ስም፣ ኢሜይል እና ስልክ ቁጥር ያለ የእውቂያ መረጃዎን ያቀናብሩ።

ወደ የግል መረጃ ሂድ

ዘግተው ሲወጡ የሚከተሉትን ጨምሮ ከእርስዎ አሳሽ ወይም መሣሪያ ጋር የተጎዳኘ መረጃን ማቀናበር ይችላሉ፦

  • ተዘግቶ የወጣ ፍለጋን ግላዊነት ማላበስ፦ የፍለጋ እንቅስቃሴዎን ይበልጥ ተገቢ የሆኑ ውጤቶችን ምክሮችን ለእርስዎ ለማቅረብ ስራ ላይ ይውል እንደሆነ ይምረጡ
  • የYouTube ቅንብሮች የእርስዎን የYouTube ፍለጋ ታሪክ እና የእርስዎን የYouTube እይታ ታሪክ ባለበት ያቁሙ እና ይሰርዙ።
  • የማስታወቂያ ቅንብሮች፦ በGoogle እና ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ከGoogle ጋር አጋር በሆኑ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ የሚታዩ የማስታወቂያ ምርጫዎችዎን ያቀናብሩ

መረጃዎን ወደ ውጭ መላክ፣ ማስወገድ እና መሰረዝ

ምትኬ ሊያስቀምጡለት ወይም ከGoogle ውጭ ከሆነ አገልግሎት ጋር ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ ከሆኑ በGoogle መለያዎ ውስጥ የይዘት ቅጂ ወደ ውጭ መላክ ይችላሉ።

ውሂብዎን ወደ ውጭ ይላኩ

እንዲሁም በሚመለከተው ህግ ላይ በመመስረት ከተወሰኑ የGoogle አገልግሎቶች ይዘት እንዲወገድ መጠየቅ ይችላሉ።

መረጃዎን ለመሰረዝ እነዚህን ማድረግ ይችላሉ፦

መረጃዎን ይሰርዙ

እና በመጨረሻም፣ የእንቅስቃሴ-አልባ መለያ አስተዳዳሪ እርስዎ ድንገት መለያዎን መጠቀም የማይችሉ ከሆኑ ለሌላ ሰው ከፊል የGoogle መለያዎን መዳረሻ እንዲሰጡ ያስችልዎታል።


የሚከተሉትንም ጨምሮ እርስዎ ወደ የGoogle መለያ ቢገቡም ባይገቡም Google የሚሰበስበውን መረጃ መቆጣጠር የሚቻልባቸው ሌሎች ብዙ መንገዶች አሉ።

  • የአሳሽ ቅንብሮች፦ ለምሳሌ፣ Google በአሳሽዎ ውስጥ ኩኪ አቀናብሮ ከሆነ እንዲያመለክት አሳሽዎን ማዋቀር ይችላሉ። እንዲሁም አሳሽዎ ከአንድ የተወሰነ ጎራ ወይም ከሁሉም ጎራዎች የሚመጡ ኩኪዎችን እንዲያግድ ማዋቀርም ይችላሉ። ነገር ግን አገልግሎቶቻችን እንደ የቋንቋ ምርጫዎችዎን ማስታወስ ላሉ ነገሮች በአግባቡ ለመስራት በኩኪዎች ላይ እንደሚተማመኑ ያስታውሱ።
  • የመሣሪያ-ደረጃ ቅንብሮች፦ የእርስዎ መሣሪያ ምን መረጃ እንደምንሰበስብ የሚወስኑ መቆጣጠሪያዎች ሊኖረው ይችላል። ለምሳሌ፣ በAndroid መሣሪያዎ ላይ የአካባቢ ቅንብሮችን መቀየር ይችላሉ።

መረጃዎን ማጋራት

መቼ መረጃዎን እንደሚያጋሩ

ብዙዎቹ አገልግሎቶቻችን መረጃ ለሌሎች ሰዎች እንዲያጋሩ፣ እና እንዴት እንደሚያጋሩ ላይ እንዲቆጣጠሩ ያስችሉዎታል። ለምሳሌ፣ ቪዲዮዎችን በYouTube ላይ በይፋ ማጋራት ወይም ቪዲዮዎችዎን የግል እንደሆኑ እንዲቀመጡ መወሰን ይችላሉ። ያስታውሱ፣ መረጃን በይፋ ሲያጋሩ የእርስዎ ይዘት በGoogle ፍለጋም ጨምሮ በፍለጋ ፕሮግራሞች በኩል ተደራሽ ሊሆን ይችላል።

በመለያ ሲገቡ እና እንደ በአንድ የYouTube ቪዲዮ ላይ አስተያየቶችን መተው ወይም በ Play ውስጥ አንድ መተግበሪያ መገምገም ያለ ከአንዳንድ የ Google አገልግሎቶች ጋር መስተጋብር ሲፈጥሩ የእርስዎ ስም እና ፎቶ ከእንቅስቃሴዎ አጠገብ ይታያል። እንዲሁም የጋራ ድጋፍ የሚታይባቸው ቅንብርዎ ላይ የሚወሰን ሆኖ ይህን መረጃ በማስታወቂያዎች ውስጥ ልናሳይ እንችላለን።

Google የእርስዎን መረጃ ሲያጋራ

ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ካልተከሰተ በቀር የግል መረጃዎን ከGoogle ውጪ ላሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች አናጋራም፦

በራስዎ ፈቃድ

የእርስዎ ፈቃድ ሲኖረን የግል መረጃዎትን ከGoogle ውጭ እናጋራለን። ለምሳሌ፣ በቦታ ማስያዣ አገልግሎት በኩል ቦታ ለማስያዝ Google Homeን የሚጠቀሙ ከሆነ የእርስዎን ስም ወይም ስልክ ቁጥር ለምግብ ቤቱ ከማጋራታችን በፊት ፈቃድዎን እንጠይቃለን። ማንኛውም ሚስጥራዊነት ያለው የግል መረጃ ለማጋራት የእርስዎን ግልጽ ፈቃድ እንጠይቃለን።

ከጎራ አስተዳዳሪዎች ጋር

እርስዎ ተማሪ ወይም የGoogle አገልግሎቶችን የሚጠቀም (እንደ G Suite ያለ) የሚጠቀም ድርጅት ሰራተኛ ከሆኑ የእርስዎ ጎራ አስተዳዳሪ እና መለያዎን የሚያስተዳድሩ ቸርቻሪዎች የGoogle መለያዎ መዳረሻ ይኖራቸዋል። እነዚህን ማድረግ ሊችሉ ይችላሉ፦

  • እንደ የእርስዎ ኢሜይል ያለ በመለያዎ ውስጥ የተከማቸ መረጃን መድረስ እና ማቆየት
  • እንደ ስንት መተግበሪያዎች እንደጫኑ ያለ መለያዎን በተመለከተ ስታቲስቲክስን መመልከት
  • የመለያዎን የይለፍ ቃል መለወጥ
  • የመለያዎን መዳረሻ ለጊዜው ማገድ ወይም ከነአካቴው ማቋረጥ
  • የሚመለከተውን ሕግ፣ ደንብ፣ ሕጋዊ ሂደት ወይም ተፈጻሚነት ያለው የመንግስት ጥያቄን ለማክበር የመለያዎን መረጃ መቀበል።
  • የእርስዎን መረጃ ወይም የግላዊነት ቅንብሮች የመሰረዝ ወይም የማርትዕ ችሎታዎን መገደብ።

መረጃዎችን ከGoogle ውጭ ለሆኑ አካላት መስጠት

በመመሪያዎቻችን መሰረት እና በግላዊነት መምሪያዎቻችን እና ሌሎች ተገቢነት ያላቸው የሚስጢራዊነት እና የደህንነት እርምጃዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ለተባባሪዎቻችን ወይም ሌሎች የታመኑ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን እኛ ለምንፈልገው ዓላማ እንዲያስሄዱት እንሰጣለን። ለምሳሌ፣ የአገልግሎት አቅራቢዎች በደንበኛ ድጋፍ ላይ እንዲያግዙን እንጠቀምባቸዋለን።

ለህጋዊ ምክንያቶች

መረጃውን መድረስ፣ መጠቀም፣ ማቆየት ወይም ይፋ ማድረግ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ለሚከተሉት አስፈላጊ ነው ብለን በቅን ልቦና ካመን የግል መረጃን ከGoogle ውጭ እናጋራለን፦

  • ማንኛውም የሚመለከተው ህግ፣ ደንብ፣ ህጋዊ ሂደት ወይም ተፈጻሚነት ያለው የመንግስት ጥያቄን ማሟላት። በየግልጽነት ሪፖርታችን ላይ ከመንግስቶች የምንቀበለው የጥያቄዎች ብዛት እና አይነት እናጋራለን።
  • ጥሰቶች ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን መመርመር ጨምሮ የሚመለከተውን የአገልግሎት ውል መፈጸም።
  • የማጭበርበር፣ የደህንነት ወይም ቴክኒካዊ ችግሮችን ማግኘት፣ መከላከል ወይም አጸፋ መስጠት።
  • ህግ በሚያዝዘው ወይም በሚፈቅደው መልኩ የGoogle፣ የእኛ ተጠቃሚዎች ወይም የሕዝቡ መብቶችን፣ ንብረቶችን ወይም ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ጉዳትን መከላከል።

በግል ተለይቶ ሊታወቅ የማይችል መረጃ በይፋ እና ለአጋሮቻችን ልናጋራ እንችላለን – እንደ አሳታሚዎች፣ ማስታወቂያ ሰሪዎች፣ ገንቢዎች ወይም ባለመብቶች ያሉ። ለምሳሌ፣ ስለአገልግሎቶቻችን አጠቃላይ አጠቃቀም ያሉ አዝማሚያዎችን ለማሳየት መረጃን በይፋ እናጋራለን። እንዲሁም ለማስታወቂያ እና መለኪያ ዓላማዎች የተወሰኑ አጋሮች የራሳቸውን ኩኪዎች ወይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው ከእርስዎ አሳሽ ወይም መሣሪያ መረጃ እንዲሰበስቡ እንፈቅዳለን።

Google ከሌላ ድርጅት ጋር ቢዋሃድ፣ ቢወረስ ወይም እሴቶች ቢሸጥ የግል መረጃዎን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅና መረጃ ከመተላለፉ ወይም ለተለየ ግላዊነት መመሪያ ተገዢ ከመሆኑ በፊት ተጽዕኖ ለሚደርስባቸው ተጠቃሚዎች ማሳወቂያ እንሰጣቸዋለን።

የመረጃዎን ደህንነት መጠበቅ

መረጃዎን ለመጠበቅ በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ደህንነት እንገነባለን

ሁሉም የGoogle ምርቶች መረጃዎን ቀጣይነት ባለው መልኩ በሚጠብቁ ጠንካራ የደህንነት ባህሪያት የተገነቡ ናቸው። አገልግሎቶቻችን ጠብቀን በማቆየት የምናገኛቸው ግንዛቤዎች የደህንነት አደጋዎች እርስዎ ጋር ሳይደርሱ እንድናገኛቸውና በራስ-ሰር እንድናግዳቸው ያግዙናል። እና እርስዎ ማወቅ አለብዎት ብለን የምናስበው የሆነ አስጊ ነገር ካገኘን እርስዎን እናሳውቀዎትና በተሻለ ሁኔታ እንዲጠበቁ የሚከተሏቸውን ደረጃዎች እናሳየዎታለን።

የሚከተሉትን ጨምሮ እርስዎን እና Google ካልተፈቀደ መዳረሻ፣ ለውጥ፣ ይፋ መደረግ ወይም የምንይዘው መረጃ መጥፋት ለመጠበቅ ተግተን እንሰራለን፦

  • ውሂብዎ እየተላለፈ ሳለ የግል እንደሆነ ለመጠበቅ ምስጠራን እንጠቀማለን
  • መለያዎን እንዲጠብቁ ለማገዝ እንደ የጥንቃቄ አሰሳ፣ የደህንነት ፍተሻ እና ባለ2-ደረጃ ማረጋገጫ ያሉ የተለያዩ ባህሪያትን እናቀርባለን
  • ያልተፈቀደ የስርዓቶቻችን መዳረሻን ለመከላከል የአካላዊ የደህንነት እርምጃዎችም ጨምሮ የመረጃ አሰባሰባችን፣ አከመቻቸታችን እና የማስሄጃ ልማዶቻችን እንገመግማለን
  • የግል መረጃ መዳረሻን ለማስሄድ መረጃው ለሚያስፈልጋቸው የGoogle ሰራተኛዎች፣ ተዋዋዮች እና ወኪሎች ብቻ ነው የምንገድበው። ይህ መዳረሻ ያለው ማንኛውም ሰው በጥብቅ የሚስጥራዊነት ግዴታዎች የሚገዛ ሲሆን እነዚህን ግዴታዎች መወጣት ካልቻሉ ቅጣት ሊጣልባቸው ወይም ሊቋረጡ ይችላሉ።

መረጃዎን ወደ ውጭ መላክ እና መሰረዝ

በማንኛውም ጊዜ የመረጃዎን ቅጂ ወደ ውጭ መላክ ወይም ከGoogle መለያዎ መሰረዝ ይችላሉ።

ምትኬ ሊያስቀምጡለት ወይም ከGoogle ውጭ ከሆነ አገልግሎት ጋር ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ ከሆኑ በGoogle መለያዎ ውስጥ የይዘት ቅጂ ወደ ውጭ መላክ ይችላሉ።

ውሂብዎን ወደ ውጭ ይላኩ

መረጃዎን ለመሰረዝ እነዚህን ማድረግ ይችላሉ፦

መረጃዎን ይሰርዙ

መረጃዎን ማቆየት

የምንሰበስበው ውሂብ ምን እንደሆነ፣ እንዴት እንደምንጠቀምበት እና እርስው ቅንብሮችዎን ባዋቀሩበት መንገድ ላይ ተመስርተን ለተለያየ ያህል ጊዜ እናቆያለን፦

  • እንደ እርስዎ የፈጠሩት ወይም የሰቀሉት ያለ አንዳንድ ውሂብ እርስዎ በፈለጉበት ጊዜ መሰረዝ ይችላሉ። እንዲሁም በመለያዎ ላይ የተቀመጠ የእንቅስቃሴ መረጃን መሰረዝ ወይም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በራስ-ሰር እንዲሰረዝ ማድረግ ይችላሉ። በራስ-ሰር እንዲሰረዝ ማድረግ ይችላሉ።
  • እንደ የማስታወቂያ ውሂብ ያለ በአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች ውስጥ ያለ ሌላ ውሂብ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በራስ-ሰር ይሰረዛል ወይም ስም-አልባ ይደረጋል።
  • እንደ አገልግሎቶቻችንን ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠቀሙ የሚገልጽ መረጃ ያለ አንዳንድ ውሂብ የGoogle መለያዎ እስኪሰርዙት ድረስ እናቆያቸዋለን።
  • እና አንዳንድ ውሂብ እንደ ደህንነት፣ ማጭበርበር ወይም አላግባብ መጠቀም መከላከል፣ ወይም የፋይናንስ መዝገብ አያያዝ ላሉ ህጋዊ ጉዳዮች ወይም ዓላማዎች ረዘም ላሉ ጊዜዎች እናቆያለን።

ውሂብ ሲሰርዙ ውሂብዎ ከአገልጋዮቻችን መወገዱን በጥንቃቄ እና ሙሉ ለሙሉ መወገዱን ወይም ስም-አልባ በሆነ መልኩ መያዙን ለማረጋገጥ የስረዛ ሂደት እንከተላለን። አገልግሎቶቻችን ከድንገተኛ ወይም ተንኮል-አዘል ስረዛ የሚጠብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን። በዚህ ምክንያት እርስዎ የሆነ ነገር ሲሰርዙና እና ቅጂዎች ከገቢር እና የምትኬ ስርዓቶቻችን እስኪሰረዙ ድረስ የሆነ መዘግየት ሊኖር ይችላል።

መረጃዎን ለመሰረዝ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድብን ጨምሮ ስለ የGoogle ውሂብ ማቆያ ጊዜዎች ተጨማሪ ማንበብ ይችላሉ።

ደንቦችን ማክበር እና ከደንብ አስከባሪዎች ጋር መተባበር

ይህን የግላዊነት መመሪያ በመደበኝነት የምገመግመው ሲሆን እሱን በሚያከብር መልኩ መረጃዎን የምናስሄድ መሆኑን እናረጋግጣለን።

የውሂብ ዝውውሮች

በመላው ዓለም ላይ አገልጋዮች አለን፣ እና መረጃዎ እርስዎ ከሚኖሩበት አገር ውጭ ባሉ አገልጋዮች ላይ ሊካሄድ ይችላል። አንዳንዶች ይበልጥ ከሌሎቹ ይልቅ ጥበቃ በሚሰጡበት ሁኔታ በተለያዩ አገሮች ውስጥ ያለው የውሂብ ጥበቃ ሕጎች ሊለያዩ ይችላሉ። የእርስዎ መረጃ የትም ቢስተናገድ በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ የተብራሩትን ተመሳሳይ ጥበቃዎች ተፈጻሚ እናደርጋለን። እንዲሁም እንደ የአህ-አሜሪካ እና የስዊስ-አሜሪካ የግላዊነት ጥበቃ መዋቅሮች ያሉ ከውሂብ ዝውውር ጋር የሚዛመዱ የተወሰኑ ህጋዊ መዋቅሮችን እናከብራለን።

መደበኛ የጽሑፍ ቅሬታዎች ሲደርሱን ቅሬታውን ያስገባውን ሰው በማነጋገር ምላሽ እንሰጣለን። በቀጥታ ከእርስዎ ጋር ሆነን ለመፍታት ያልቻልነውን ውሂብዎን ማስተላለፍ የሚመለከቱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካባቢያዊ የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣናትን ጨምሮ አግባብነት ካላቸው የክትትል ባለስልጣናት ጋር አብረን እንሰራለን።

የካሊፎርኒያ መስፈርቶች

የካሊፎርኒያ የሸማች የግላዊነት ሕግ (ሲሲፒኤ) ለካሊፎርኒያ ነዋሪዎች የተወሰኑ መረጃዎችን ይፋ ማውጣትን ያስገድዳል።

ይህ የግላዊነት መመሪያ እንዴት Google የእርስዎን መረጃ እንደሚይዝ እርስዎ እንዲረዱ ተብሎ የተዘጋጀ ነው፦

ሲሲፒኤ በተጨማሪ እንዴት Google የእርስዎን የግል መረጃ እንደሚሰበስብ፣ እንደሚጠቀምበት እና አሳልፎ ይፋ እንደሚያወጣ መረጃን የመጠየቅ መብትን ይሰጣል። እና የእርስዎን መረጃ እንዲደርሱበት እንዲሁም Google ያንን መረጃ እንዲሰርዝ የሚችሉበትን መብት ይሰጣል። በመጨረሻም፣ ሲሲፒኤ የእርስዎን የግላዊነት መብቶች ስላስከበሩ ምንም ዓይነት መድልዎ እንዳይፈጸምብዎት የሚያስችልዎትን መብት ይሰጥዎታል።

የእርስዎን ግላዊነት እና ውሂብ በመላው የGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ለማቀናበር ያለዎትን ምርጫዎች በየእርስዎ የግላዊነት መቆጣጠሪያዎች ውስጥ አብራርተናል። የእርስዎን መረጃ እንዲደርሱበት፣ እንዲገመግሙት፣ እንዲያዘምኑት እና እንዲሰርዙት እንዲሁም ቅጂውን ወደ ውጭ እንዲልኩ እና እንዲያወርዱት የሚያስችሉዎ እነዚህን መቆጣጠሪያዎች በመጠቀም የእርስዎን መብቶች ማስከበር ይችላሉ። ሲጠቀሙባቸው ወደ የእርስዎ Google መለያ እንደገቡ በማረጋገጥ የእርስዎን ጥያቄ ትክክለኛነት እናረጋግጣለን። ጥያቄዎች ካለዎት ወይም ከእርስዎ በሲሲፒኤ ሥር ያሉ መብቶች ዙሪያ ጥያቄዎች ካለዎት እርስዎ (ወይም የእርስዎ ሥልጣን ያለው ተወካይ) እንዲሁም Googleን ማነጋገር ትችላላችሁ።

ሲሲፒኤ የተወሰኑ ምድቦችን በመጠቀም የውሂብ አያያዝ ልማዶችን ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ያስገድዳል። ይህ ሰንጠረዥ በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ መረጃን ለማደራጀት እነዚህን ምድቦች ይጠቀማል።

እኛ የምንሰበስበው የግል መረጃ ምድቦች

እንደ የእርስዎ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና አድራሻ ያሉ ለዪዎች፣ እንዲሁም እርስዎ ከሚጠቀሙበት አሳሽ፣ መተግበሪያ ወይም መሣሪያ ጋር የተሳሰሩ ልዩ ለዪዎች

እንደ የእርስዎ ዕድሜጾታ እና ቋንቋ የመሳሰለ ሥነ ሕዝባዊ መረጃ

እንደ የእርስዎ የክፍያ መረጃ እና እርስዎ በGoogle አገልግሎቶች ላይ የሚፈጽሟቸው የግዢዎች ታሪክ ያለ የንግድ መረጃ

ባዮሜትሪክ መረጃ እንደ በGoogle ምርት ግንባታ ጥናቶች ውስጥ እንደ የጣት አሻራዎች ያለለመስጠት ከመረጡ።

እንደ የእርስዎ የፍለጋ ቃላት፤ እይታዎች ከይዘት እና ማስታወቂያዎች ጋር እርስዎ ያለዎት መስተጋብሮች፤ እርስዎ ከGoogle መለያ ጋር ያሰመሩት የChrome አሰሳ ታሪክ፤ የእርስዎ መተግበሪያዎች፣ አሳሾች እና መሣሪያዎች ከእኛ አገልግሎቶች (እንደ የአይፒ አድራሻ፣ የስንክል ሪፖርቶች እና የሥርዓት እንቅስቃሴ ያሉ) ጋር ያላቸው መስተጋብር፤ እና አገልግሎቶቻችንን በሚጠቀሙ የሦስተኛ ወገን ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ ያለ እንቅስቃሴ ያለ የበይነመረብ፣ የአውታረ መረብ እና የሌላ እንቅስቃሴ መረጃ። በእርስዎ Google መለያ ውስጥ የተከማቸውን ውሂብ በየእኔ እንቅስቃሴ ውስጥ መገምገም እና መቆጣጠር ይችላሉ።

በእርስዎ መሣሪያ እና በመለያ ቅንብሮች ላይ የሚወሰን ሆኖ በጂፒኤስ፣ የአይፒ አድራሻ እና በመሣሪያዎ ላይ ወይም በእሱ ዙሪያ ካሉ ዳሳሾች የተገኘ ሌላ ውሂብ ያለ የጂዮ አካባቢ ውሂብ። ስለየGoogle አካባቢ መረጃን አጠቃቀም የበለጠ ይረዱ።

የኦዲዮ፣ ኤሌክትሮኒክ፣ ምስላዊ እና ተመሳሳይ መረጃ፣ እንደ እርስዎ ኦዲዮ ባህሪያትን ሲጠቀሙ ያለ የድምጽ እና የኦዲዮ መረጃ

ሞያዊ፣ የሥራ ቅጥር እና የትምህርት መረጃ፣ እንደ እርስዎ የሚሰጡትመረጃ የመሳሰለ ወይም እርስዎ በሚማሩበት ወይም ሥራ በሚሠሩበት ተቋም አማካይነት በG Suite መለያ የተያዘ።

እርስዎ የሚፈጥሩት ወይም የሚያቀርቡት ሌላ መረጃ፣ እንደ እርስዎ የሚፈጥሩት፣ የሚሰቅሉት ወይም የሚቀበሉት (ለምሳሌ ፎቶዎች ኣና ቪዲዮዎች ወይም ኢሜይሎች፣ ሰነዶች እና የተመን ሉሆች) ይዘት ያለ። Google ዳሽቦርድ ከተወሰኑ ምርቶች ጋር የተጎዳኘ መረጃን እንዲያቀናብሩ ያስችልዎታል።

እንደ የእርስዎ ማስታወቂያዎች ፍላጎት ምድቦች ያሉ ከላይ የተወሰዱ ማጣቀሻዎች

መረጃ ጥቅም ላይ ሊውል ወይም ይፋ ሊወጣ የሚችልባቸው የንግድ ሥራ ዓላማዎች

ከደህንነት ስጋቶች፣ በደል እና ሕገወጥ እንቅስቃሴን መከላከል፦ Google የደህንነት ችግሮችን ፈልጎ ለማግኘት፣ ለመከላከል እና አጸፋ ለመስጠት እንዲሁም ሌሎች ተንኮል-አዘል፣ አጭበርባሪ፣ አታላይ ወይም ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ጥበቃ ለማድረግ ሲባል መረጃን ሊጠቀም እና አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል። ለምሳሌ፣ የእኛን አገልግሎቶች ለመጠበቅ ሲባል Google ተንኮል-አዘል አካላትን የነጠቁትን የአይፒ አድራሻ በተመለከተ መረጃ ሊቀበል ወይም አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል።

ኦዲት ማድረግ እና ልኬት፦ Google የእኛ አገልግሎቶች እንዴት ስራ ላይ እንደሚውሉ ለመረዳትና እንዲሁም እንደ አታሚዎች፣ ማስታወቂያ ሰሪዎች፣ ገንቢዎች ወይም የመብት ባለቤቶች ያሉ ለእኛ አጋሮች ያሉብን ኃላፊነቶች ለመወጣት መረጃን ለትንታኔ ሥራ እና ለልኬት ይጠቀማል። ማንነትን በግል ለይቶ የማያሳውቅ መረጃ በይፋ ከእነዚህ አጋሮች ጋር ለኦዲት ሥራ ጭምር አሳልፈን ልንሰጥ እንችላለን።

የእኛን አገልግሎቶች መጠገን፦ Google እንደ የኃይል መቋረጦችን መከታተል ወይም ለሳንካዎች እና እርስዎ ለእኛ ሪፖርት ለሚያደርጓቸው ሌሎች ችግሮች መላ ለመፈለግ ያሉ የእኛ አገልግሎቶች እንደታሰበው እየሠሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መረጃን ይጠቀማል።

ምርምር እና ግንባታ፦ Google የእኛን አገልግሎቶች ለማሻሻል እና ለእኛ ተጠቃሚዎች እና ለሕዝብ የሚጠቅሙ አዲስ ምርቶችን፣ ባህሪያትን እና ቴክኖሎጂዎችን ለመገንባት መረጃን ይጠቀማል። ለምሳሌ፣ እንደ Google ትርጉም ያሉ ባህሪያትን ለመገንባት እና የGoogle ቋንቋ ሞዴሎችን ለማለማመድ እንዲያግዝ በይፋ የሚገኝ መረጃን እንጠቀማለን።

አገልግሎት አቅራቢዎችን አጠቃቀም፦ Google በእኛ ምትክ አገልግሎት አቅራቢዎች አገልግሎቶችን ማከናወን እንዲችሉ የእኛን የግላዊነት መመሪያ እና ሌላ አግባብ የሆኑ የሚስጥር እና የደህንነት ጥበቃ እርምጃዎች እንደተጠበቁ መረጃን ለአገልግሎት አቅራቢዎች ያጋራል። ለምሳሌ፣ የደንበኛ እገዛ አገልግሎትን ማቅረብ እንዲቻል ለማገዝ በአገልግሎት አቅራቢዎች ላይ ልንመሠረት እንችላለን።

የማስታወቂያ ስራ፦ Google ማስታወቂያን ለማቅረብ የመስመር ላይ ለይቶ ማወቂያዎችን እና እርስዎ ከማስታወቂያዎች ጋር ስላለዎት መስተጋብሮች መረጃ ጨምሮ መረጃን በሥራ ሂደት ውስጥ ያስገባል። ይህ የGoogle አገልግሎቶችን እና እርስዎ ያለምንም ክፍያ የሚጠቀሙባቸውን በርካታ የድር ጣቢያዎች እና አገልግሎቶችን ያቆያል። የእርስዎን የማስታወቂያ ቅንብሮች በመጎብኘት እኛ ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ምን መረጃ እንደምንጠቀም መቆጣጠር ይችላሉ።

ሕጋዊ ምክንያቶች፦ Google እንዲሁም የሚመለከታቸው ሕጎችን ወይም ደንቦችን ለማክበር፣ እና የሕግ ማስፈጸምን ጨምሮ በሕጋዊ ሂደት ወይም ተፈጻሚነት በሚኖራቸው የመንግሥት ጥያቄዎች ላይ መረጃን አሳልፎ ለመስጠት መረጃን ይጠቀማል። በእኛ የግልጽነት ሪፖርት ላይ ከመንግሥታት የምንቀበላቸውን የጥያቄዎች ብዛት እና ዓይነት በተመለከተ መረጃ እንሰጣለን።

መረጃ ሊጋራላቸው የሚችሉ ወገኖች

እንደ ሰነዶች ወይም ፎቶዎች፣ እና በYouTube ላይ ያሉ ቪዲዮዎች ወይም አስተያየቶች ያሉ የእርስዎን መረጃ ለማጋራት የመረጧቸው ሌሎች ሰዎች

እንደ የGoogle አገልግሎቶችን የሚያካትቱ አገልግሎቶችን ያሉ እርስዎ መረጃዎ እንዲያጋራላቸው የፈቀዱላቸው ሦስተኛ ወገኖች። በእርስዎ የGoogle መለያ ውስጥ የውሂብ መዳረሻ ያላቸው የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎችንና ጣቢያዎችን መገምገም እና ማቀናበር ይችላሉ።

አገልግሎት አቅራቢዎች፣ በእኛ መመሪያዎች እና የግላዊነት መመሪያችንና ሌሎች ማናቸውም አግባብ የሆኑ የሚስጥራዊነትና የደህንነት እርምጃዎች በመከተል Googleን ወክለው መረጃን የሚያሰናዱ የታመኑ ንግዶች ወይም ግለሰቦች።

የጎራ አስተዳዳሪዎች፣ እንደ G Suite ያሉ የGoogle አገልግሎቶችን በሚጠቀም ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ወይም የሚማሩ ከሆነ።

ሕግ አስከባሪ ወይም ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች፣ በየእርስዎን መረጃ ማጋራት ውስጥ ለተብራሩ ሕጋዊ ምክንያቶች።

ስለዚህ መመሪያ

ይህ መመሪያ ሲተገበር

ይህ የግላዊነት መመሪያ YouTube፣ Android እና እንደ የማስታወቂያ አገልግሎቶች ያሉ በሶስተኛ ወገን ጣቢያዎች የሚቀርቡ አገልግሎቶችም ጨምሮ በGoogle LLC እና በአጋሮቹ በሚቀርቡ ሁሉም አገልግሎቶች ላይ ተፈጻሚ ነው። ይህን የግላዊነት መመሪያ በማያካትቱ የተለያዩ የግላዊነት መመሪያዎች ያላቸው አገልግሎቶች ላይ ይህ የግላዊነት መመሪያ አይተገበርም።

ይህ የግላዊነት መመሪያ በእነዚህ ላይ አይተገበርም፦

  • የአገልግሎቶቻችንን ማስታወቂያ የሚያሳዩ የሌሎች ኩባንያዎች እና ድርጅቶች የመረጃ ልምዶች
  • የGoogle አገልግሎቶችን ሊያካትቱ የሚችሉ ምርቶች ወይም ጣቢያዎችም ጨምሮ በሌሎች ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች የሚቀርቡ በፍለጋ ውጤቶች ውስጥ የሚታዩ ወይም ከአገልግሎቶቻችን የሚገናኙ አገልግሎቶች

በዚህ መመሪያ ላይ የተደረጉ ለውጦች

ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህን የግላዊነት መመሪያ እንቀይረዋለን። በግልጽ የተሰጠ ፈቃድዎን ሳናገኝ በዚህ ግላዊነት መምሪያ ላይ ያሉዎት መብቶችን አንቀንስም። ሁልጊዜ የመጨረሻዎቹ ለውጦች የታተሙበትን ቀን እናመለክታለን፣ እና በማህደር የተቀመጡ ስሪቶች መዳረሻን ለግምገማዎ እናቀርባለን። ለውጦቹ ጉልህ ከሆኑ ይበልጥ ጎላ ያለ ማስታወቂያ እናቀርባለን (ለተወሰኑ አገልግሎቶች የግላዊነት መመሪያ ለውጦች ኢሜይል ማሳወቂያ ጨምሮ)።

ተዛማጅ የግላዊነት ልምዶች

የተወሰኑ የGoogle አገልግሎቶች

የሚከተሉት የግላዊነት ማስታወቂያዎች ስለአንዳንድ የGoogle አገልግሎቶች ተጨማሪ መረጃ ያቀርባሉ፦

ሌሎች ጠቃሚ መርጃዎች

የሚከተሉት አገናኞች እርስዎ ስለልማዶቻችን እና የግላዊነት ቅንብሮች ተጨማሪ እንዲያውቁ የሚያስችልዎ ጠቃሚ መርጃዎችን ያደምቃሉ።

የቃላት ፍቺ

ልዩ ለዪዎች

ልዩ ለዪ አሳሽን፣ መተግበሪያን ወይም መሣሪያን ለይቶ ለማወቅ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል የቁምፊዎች ኅብረቁምፊ ነው። የተለያዩ ለዪዎች በዘላቂነታቸው፣ በተጠቃሚዎች ዳግም ሊጀመሩ መቻላቸው፣ እና እንዴት ሊደረስባቸው እንደሚቻል ላይ ይለያያሉ።

ልዩ ለዪዎች ለደህንነት እና ማጭበርበርን ለመያዝ፣ እንደ የእርስዎ የኢሜይል ገቢ መልዕክት ሳጥን ያሉ አገልግሎቶችን ለማሳመር፣ የእርስዎ ምርጫዎችን ለማስታወስ እና ተገቢ ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ ጨምሮ ለተለያዩ ዓላማዎች ሥራ ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ በኩኪዎች ውስጥ የተቀመጡ ልዩ ለዪዎች ጣቢያዎች በእርስዎ አሳሽ ውስጥ በተመራጭ ቋንቋዎ እንዲያሳዩ ያግዛቸዋል። አሳሽዎ ሁሉንም ኩኪዎች እንዳይቀበል ወይም አንድ ኩኪ እየተላከ ሳለ እንዲያመለክት ማዋቀር ይችላሉ። እንዴት Google ኩኪዎችን እንደሚጠቀም የበለጠ ይረዱ።

በሌሎች የመሣሪያ ስርዓቶች ላይ ከአሳሾች በተጨማሪ የተወሰነ መሣሪያ ወይም በዚያ መሣሪያ ላይ ያለን መተግበሪያን ለይቶ ለማወቅ ልዩ ለዪዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለምሳሌ፣ እንደ የማስታወቂያ መታወቂያ ያለ ልዩ ለዪ በAndroid መሣሪያዎች ላይ ተዛማጅ ማስታወቂያን ለማቅረብ በእርስዎ የመሣሪያ ቅንብሮች ውስጥ ሊቀናበር ይችላል። እንዲሁም ልዩ ለዪዎች በአምራቹ ለምሳሌ እንደ የተንቀሳቃሽ ስልክ ኢኤምኢአይ ቁጥር ያለ (አንዳንድ ጊዜ ሁለንተናዊ ልዩ መታወቂያ ወይም ዩዩአይዲ በመባል የሚታወቅ) ለአንድ መሣሪያ በውስጡ ሊካተት ይችላል። ለምሳሌ፣ የአንድ መሣሪያ ልዩ ለዪ አገልግሎታችን ለመሣሪያዎ ለማበጀት ወይም ከአገልግሎቶቻችን ጋር የተገናኙ የመሣሪያ ችግሮችን ለመተንተን ልዩ ለዪዎች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

መሣሪያ

መሣሪያ ማለት የGoogle አገልግሎቶችን ለመድረስ ሥራ ላይ ሊውል የሚችል ኮምፒውተር ነው። ለምሳሌ፣ የዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ጡባዊዎች፣ ዘመናዊ ድምጽ ማጉያዎች እና ዘመናዊ ስልኮች በሙሉ እንደ መሣሪያዎች ይቆጠራሉ።

ምስጢራዊ የግል መረጃ

ይሄ ከምሥጢራዊ የሕክምና እውነታዎች፣ የዘር ወይም የጎሣ ምንጮች፣ ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ እምነቶች ወይም ጾታዊ ተፈጥሮዎች ጋር የሚያያዝ ለየት ያለ የግል መረጃ ምድብ ነው።

ስልተ-ቀመር

ችግር-ፈቺ ክወናዎችን ማከናውን ላይ አንድ ኮምፒውተር የሚከተላቸው ሂደት ወይም የደንቦች ስብስብ።

በግል የማይለይ መረጃ

ይህ መረጃ ስለተጠቃሚዎች የተመዘገበ መረጃ ነው፣ እናም ካሁን በኋላ በግል የሚለይ ተጠቃሚ አያንጸባርቅም ወይም አይጠቅስም።

አይ. ፒ. አድራሻ

ከበይነመረቡ ጋር የተገናኘ እያንዳንዱ መሣሪያ የበይነመረብ ፕሮቶኮል (አይፒ) አድራሻ ተብሎ የሚታወቅ ቁጥር ይመደብለታል። እነዚህ ቁጥሮች አብዛኛው ጊዜ በጂዮግራፊያዊ ስብስቦች ነው የሚመደቡት። አብዛኛው ጊዜ አንድ መሣሪያ ከየት ሆኖ ከበይነመረብ ጋር እንደተገናኘ ለማወቅ የአይፒ አድራሻን መጠቀም ይቻላል።

ኩኪዎች

ኩኪ ማለት አንድ ድር ጣቢያ ሲጎበኙ ወደ ኮምፒውተርዎ የሚላክ የቁምፊዎች መደዳ የያዘ ትንሽ ፋይል ነው። ጣቢያውን እንደገና ሲጎበኙት ኩኪው ያንን ጣቢያ አሳሽዎ እንዲያውቀው ያስችለዋል። ኩኪዎች የተጠቃሚ ምርጫዎችና ሌላ መረጃ ሊያከማቹ ይችላሉ። አሳሽዎ ሁሉንም ኩኪዎች እንዳይቀበል ወይም አንድ ኩኪ እየተላከ ሳለ እንዲያመለክት ማዋቀር ይችላሉ። ይሁንና አንዳንድ የድር ጣቢያ ባህርያት ያለ ኩኪዎች በአግባቡ ላይሠሩ ይችላሉ። እርስዎ የአጋሮቻችን ጣቢያዎች ወይም መተግበሪያዎች በሚጠቀሙበት ጊዜ እንዴት ኩኪዎችን እንደሚጠቀም እና Google ኩኪዎችን ጨምሮ ውሂብን እንዴት እንደሚጠቀም ተጨማሪ ይረዱ።

የላኪ ዩአርኤል

የጠቃሽ ዩአርኤል (ዩኒፎርም ሪሶርስ ሎኬተር) በአንድ ድር አሳሽ ወደ መድረሻ ድረ-ገጽ የሚተላለፍ መረጃ ነው፣ በተለይ ወደዚያ ገጽ የሚወስድ አገናኝ ጠቅ ሲያደርጉ። የጠቃሹ ዩአርኤል አሳሹ የጎበኘው የመጨረሻው ድረ-ገጽ ዩአርኤል ይዟል።

የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫ

የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫ በአንድ መሣሪያ ላይ ያለ የውሂብ ክምችት ነው። ለምሳሌ፣ አንድ የድር መተግበሪያ የበይነመረብ ግንኙነት ሳይኖር ማሄድ እና ፈጣን የይዘት መጫንን በማንቃት የመተግበሪያውን አፈጻጸም ማሻሽል ይችላል።

የሽያጭ ተባባሪ አካላት

አጋር ማለት በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ የሸማች አገልግሎቶች የሚሰጡትን Google Ireland Limited፣ Google Commerce Ltd፣ Google Payment Corp እና Google Dialer Inc ኩባንያዎችን ጨምሮ የGoogle የኩባንያዎች ቡድን አካል የሆነ ሕጋዊ አካል ነው.። በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ የንግድ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ኩባንያዎችን በተመለከተ የበለጠ ይረዱ።

የአሳሽ ድር ማከማቻ

የአሳሽ ድር ማከማቻ ድር ጣቢያዎች ውሂብ በአንድ መሣሪያ ላይ ባለ አሳሽ ላይ እንዲያከማቹ ያግዛል። በ«አካባቢያዊ ማከማቻ» ሁነታ ላይ ሥራ ላይ ሲውል ውሂብ በተለያዩ ክፍለ-ጊዜዎች ላይ እንዲከማች ያስችላል። ይህ አሳሽ ተዘግቶ ዳግም ከተከፈተ በኋላ እንኳ ውሂብን ሰርስሮ ማውጣት የሚቻል ያደርገዋል። ኤችቲኤምኤል 5 አንድ የድር ማከማቸትን የሚያመቻች ቴክኖሎጂ ነው።

የአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች

አገልጋዮቻችን ልክ እንደአብዛኛዎቹ ድር ጣቢያዎች ጣቢያዎቻችን ሲጎበኙ ያደረጓቸው የጠየቅዋቸው ገጾች በራስ-ሰር ይዘግባሉ። እነዚህ «የአገልጋይ ምዝግብ ማስታወሻዎች» በተለይ የጠየቅዋቸው ድሮች፣ የአይ.ፒ. አድራሻ፣ የአሳሽ አይነት፣ የአሳሽ ቋንቋ፣ የጥያቄህ ቀንና ጊዜ እና አሳሽዎን በተለየ ሁኔታ ሊለይ የሚችል አንድ ወይም ተጨማሪ ኩኪስ ያካትታሉ።

«መኪናዎች» ለሚል የተለመደ የምዝግብ ግቤት ይህን ይመስላል፦

123.45.67.89 - 25/Mar/2003 10:15:32 -
http://www.google.com/search?q=cars -
Firefox 1.0.7; Windows NT 5.1 -
740674ce2123e969
  • 123.45.67.89 ተጠቃሚው በበይነመርብ አገልግሎት አቅራቢው የተመደበለት የአይፒ አድራሻ ነው፤ በተጠቃሚው አገልግሎት የሚወሰን ሆኖ ተጠቃሚው ከበይነመረቡ ጋር በተገናኘ ቁጥር በአገልግሎት አቅራቢው የተለየ አድራሻ ሊሰጠው ይችላል።
  • 25/Mar/2003 10:15:32 የመጠይቁ ቀን እና ሰዓት ነው።
  • http://www.google.com/search?q=cars የፍለጋ መጠይቁን ጨምሮ የተጠየቀው ዩአርኤል ነው።
  • Firefox 1.0.7; Windows NT 5.1 ሥራ ላይ የዋሉት አሳሽና ሥርዓተ ክወና ነው።
  • 740674ce2123a969 ለዚሁ ኮምፒውተር በGoogle ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኝ የተመደበለት ልዩ የኩኪ መታወቂያ ነው። (ኩኪዎች በተጠቃሚዎች ሊሰረዙ ይችላሉ። ተጠቃሚው Googleን ከጎበኘበት የመጨረሻ ጊዜ ኩኪውን ከኮምፒውተሩ ከሰረዙት ተጠቃሚው በሚቀጥለው ጊዜ Googleን ከዚያው ኮምፒውተር ሲጎበኙ ለተጠቃሚው የሚመደብ ልዩ የኩኪ መታወቂያ ይሆናል)።

የግል መረጃ

ይህ እርስዎን በግል የሚለይ እንደ የእርስዎ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ ወይም የክፍያ መረጃ፣ ወይም ሌላ እንደ ከGoogle መለያዎ ጋር የምናጎዳኘው መረጃ ያሉ Google በምክንያታዊነት እንደዚህ ካለ መረጃ ጋር ሊያገናኝ የሚችል ውሂብ ያለ ለእኛ የሚያቀርቡት መረጃ ነው።

የፒክሰል መለያ

የፒክሴል መለያ እንደ የድር ጣቢያዎች ዕይታ ወይም ኢሜይል ሲከፈት ያለ የተወሰነ እንቅስቃሴን ለመከታተል ዓላማ በድር ጣቢያ ወይም በኢሜይል አካል ውስጥ የሚቀመጥ የቴክኖሎጂ ዓይነት ነው። የፒክሴል መለያዎች አብዛኛውን ጊዜ ከኩኪዎች ጋር በጣምራነት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

የGoogle መለያ

Google መለያ በመመዝገብና አንዳንድ የግል መረጃ (በተለይ የእርስዎ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ እና አንድ የይለፍ ቃል) ለእኛ በመስጠት አንዳንድ አገልግሎቶቻችንን ሊደርሱባቸው ይችላሉ። ይሄ የመለያ መረጃ የGoogle አገልግሎቶች ሲደርሱባቸው እርስዎን ለማረጋገጥና መለያዎን በሌሎች ከሚደረጉ ያልተፈቀደ መድረስ ለመጠበቅ ስራ ላይ ይውላል። በማንኛውም ጊዜ በእርስዎ የGoogle መለያ ቅንብሮች በኩል የእርስዎን መለያ ማርትዕ ወይም መሰረዝ ይችላሉ።

ተጨማሪ አውድ

ልክ እንደ ሌሎች የቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ኩባንያዎች ሁሉ Google የተጠቃሚ ውሂብ አሳልፎ እንዲሰጥ በመላው ዓለም ካሉ መንግስታት እና ፍርድ ቤቶች በየጊዜው ጥያቄዎች ይድርሱታል። Google ላይ የሚያከማቹት የውሂብ ግላዊነት እና ደህንነት ማክበር እነዚህ ህጋዊ ጥያቄዎችን የምናከብርበት መንገድ መርህ ነው። ምንም አይነት ጥያቄዎች ይሁኑ የእኛ የህግ ቡድን እያንዳንዱን ጥያቄ ይገመግማል፣ እና ጥያቄዎቹ በጣም ሰፊ ወይም ትክክለኛውን ሂደት ያልተከተሉ ሆነው ከታዩ በተደጋጋሚነት ይመልሳል። በእኛ የግልጽነት ሪፖርት ውስጥ የበለጠ ይረዱ።

መሣሪያዎች

ለምሳሌ፣ አንድ መተግበሪያ ለመጫን ወይም ከGoogle Play የገዙትን ፊልም ለመመልከት የትኛውን መሣሪያ እንደሚጠቀሙ እንዲወስኑ ለማገዝ ይህን መረጃ ልንጠቀምበት እንችላለን። እንዲሁም መለያዎን ለመጠበቅ ይህን መረጃ እንጠቀማለን።

Google ትንታኔዎች በአንደኛ ወገን ኩኪዎች ላይ የሚተማመን ነው፣ ይህ ማለት ኩኪዎች በGoogle ትንታኔዎች ደንበኛ የተቀናበሩ ናቸው ማለት ነው። ስርዓቶቻችንን በመጠቀም በGoogle ትንታኔዎች በኩል የመነጨ ውሂብ በGoogle ትንታኔዎች ደንበኛውና በGoogle ወደ ሌሎች ድር ጣቢያዎች ከተደረጉ ጉብኝቶች ጋር ከሚዛመዱ የሶስተኛ ወገን ኩኪዎች ጋር እንዲገናኙ ሊያደርጉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ አንድ ማስታወቂያ ሰሪ ይበልጥ ተገቢ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለመፍጠር ወይም ትራፊኩን በይበልጥ ለመተንተን የGoogle ትንታኔዎች ውሂቡን መጠቀም ሊፈልግ ይችላል። የበለጠ ለመረዳት

መስመር ላይ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ሰዎች

ለምሳሌ፣ በሚጽፉት የኢሜይል «ለ»፣ «ካርቦን ቅጂ» ወይም «ስውር ካርቦን ቅጂ» መስክ ላይ አድራሻ ሲተይቡ Gmail እርስዎ በተደጋጋሚነት በሚያገኟቸው እውቂያዎች ላይ ተመስርቶ አድራሻዎችን ይጠቁማል።

ሚስጥራዊነት ያላቸው ምድቦች

ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ስናሳይ በእንቅስቃሴዎ ላይ ተመስርተን እርስዎን ሊስቡ ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ርዕሶችን እንጠቀማለን። ለምሳሌ፣ እንደ «የምግብ አዘገጃጀቶች» ወይም «የአየር ጉዞ» ያሉ ነገሮች ማስታወቂያዎች ሊያዩ ይችላሉ። እንደ ዘር፣ ኃይማኖት፣ ጾታዊ ዝንባሌ ወይም ጤና ባሉ ሚስጥራዎነት ያላቸው ምድቦች ላይ ተመስርተን ርዕሶችን ወይም ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን አንጠቀምም። እና አገልግሎቶቻችን ከሚጠቀሙ ማስታወቂያ ሰሪዎች ተመሳሳዩን እንፈልጋለን

ማረጋገጥ እና ማሻሻል

ለምሳሌ፣ የማስታወቂያዎቻችን አፈጻጸም ለማሻሻል ሰዎች እንዴት ከማስታወቂያ ጋር መስተጋብር እንደሚፈጥሩ እንተነትናለን።

ማሻሻያዎችን ማድረግ

ለምሳሌ፣ ሰዎች እንዴት ከአገልግሎቶቻችን ጋር መስተጋብር እንደሚፈጥሩ ለመተንተን ኩኪዎችን እንጠቀማለን። እና ይህ ትንታኔ የተሻሉ ምርቶችን እንድንገነባ ያግዘናል። ለምሳሌ፣ ሰዎች አንድን ተግባር ለማጠናቀቅ በጣም ረጅም ጊዜ እየወሰደባቸው ወይም ጭራሽ ደረጃዎችን መጨረስ ላይ ችግሮች እያጋጠማቸው እንደሆነ እንድናውቅ ሊያግዘን ይችላል። ከዚያ ባህሪውን ዳግም መንደፍና ምርቱን ለሁሉም ማሻሻል እንችላለን።

ስልክ ቁጥር

በመለያዎ ላይ ስልክ ቁጥር ካከሉ በቅንብሮችዎ የሚወሰን ሆኖ በመላ የGoogle አገልግሎቶች ላይ ለተለያዩ ዓላማዎች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ለምሳሌ፣ የይለፍ ቃልዎን ከረሱ ስልክ ቁጥርዎ መለያዎን እንዲደርሱ፣ ሰዎች እርስዎን አግኝተው እንዲገናኙ፣ እና የሚመለከቷቸውን ማስታወቂያዎች ለእርስዎ ይበልጥ ተገቢነት ያላቸው እንዲሆኑ ለማገዝ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። የበለጠ ለመረዳት

ሶስተኛ ወገኖች

ለምሳሌ፣ የባለመብቶች ይዘት በአገልግሎቶቻችን ውስጥ እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋለ ላይ የአጠቃቀም ስታቲስቲክስ ለእነሱ ሪፖርት ለማድረግ መረጃዎን እናስሄደዋለን። እንዲሁም ሰዎች የእርስዎን ስም ከፈለጉ መረጃዎን ልናስሄደው እንችላለን፣ እና ስለእርስዎ ያለ በይፋ የሚገኝ መረጃ ያላቸው የጣቢያዎች ፍለጋ ውጤቶችን እናሳያለን።

በሌሎች ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ ያለው እንቅስቃሴዎ

ይህ እንቅስቃሴ እንደ መለያዎን ከChrome ጋር ማሳመር ወይም ከGoogle ጋር አጋር በሆኑ ጣቢያዎችና መተግበሪያዎች ላይ ያደረጓቸው ጉብኝቶች ካሉ የGoogle አገልግሎቶች አጠቃቀምዎ ሊመጣ ይችላል። ብዙ ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ይዘታቸውን እና አገልግሎታቸውን ለማሻሻል ከGoogle ጋር አጋርነት ይፈጥራሉ። ለምሳሌ፣ አንድ ድር ጣቢያ የእኛን የማስታወቂያ አገልግሎቶች (እንደ AdSense ያሉ) ወይም የትንታኔዎች መሣሪያዎች (እንደ Google ትንታኔዎች ያሉ) ሊጠቀም ይችላል፣ ወይም ደግሞ በሌሎች ይዘቶች (እንደ የYouTube ቪዲዮዎች ያሉ) ላይ ሊከትት ይችላል። እነዚህ ምርቶች ስለእንቅስቃሴዎ መረጃን ለGoogle ሊያጋሩ የሚችሉ ሲሆን በየመለያ ቅንብሮችዎ እና ስራ ላይ በዋሉት ምርቶች ላይ በመመስረት (ለምሳሌ፣ አንድ አጋር Google ትንታኔዎችን ከማስታወቂያ አገልግሎቶቻችን ጋር በጥምረት ሲጠቀም) ይህ ውሂብ ከግል መረጃዎ ጋር ሊጎዳኝ ይችላል።

እርስዎ የአጋሮቻችን ጣቢያዎች እና ጣቢያዎች ሲጠቀሙ Google እንዴት ውሂብ እንደሚጠቀምበት የበለጠ ይወቁ

በመላው ዓለም ያሉ አገልጋዮች

ለምሳሌ፣ ምርቶቻችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለተጠቃሚዎች የሚገኙ እንዲሆኑ ለማገዝ በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ የውሂብ ማዕከሎችን እንከውናለን።

በአግባቡ ለመስራት በኩኪዎች ላይ መተማመን

ለምሳሌ፣ እርስዎ በአንድ አሳሽ ውስጥ ብዙ Google ሰነዶችን መክፈት እንዲችሉ «lbcs» የሚባል ኩኪ እንጠቀማለን። ይህን ኩኪ ማገድ Google ሰነዶች እንደተጠበቀው እንዳይሰራ ይከለክለዋል። የበለጠ ለመረዳት

በይፋዎ ተደራሽ የሆኑ ምንጮች

ለምሳሌ፣ የGoogle ቋንቋ ሞዴሎችን ለማሰልጠንና እንደ Google ትርጉም ያሉ ባህሪያትን ለመገንባት ለማገዝ በይፋ መስመር ላይ የሚገኝ ወይም ከሌሎች ይፋዊ ምንጮች የሚገኝ መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን።

በጣም ጠቃሚ ሆነው የሚያገኟቸው ማስታወቂያዎች

ለምሳሌ፣ YouTube ላይ ስለመጋገር ያሉ ቪድዮዎችን የሚመለከቱ ከሆኑ ድሩን ሲያስሱ መጋገርን የሚመለከቱ ተጨማሪ ማስታወቂያዎችን ሊመለከቱ ይችላሉ። እንዲሁም ግምታዊ አካባቢዎን ለመወሰን የአሁኑ የአይፒ አድራሻዎን ልንጠቀም እንችላለን፣ በዚህም «ፒዛ» ብለው ከፈለጉ አቅራቢያ ስላለ የፒዛ መላኪያ አገልግሎት ማስታወቂያዎችን ልናቀርብልዎ እንችላለን። ስለGoogle ማስታወቂያዎች እና ለምን የተወሰኑ ማስታወቂያዎችን ሊመለከቱ እንደሚችሉ ተጨማሪ ይወቁ።

ለምሳሌ፣ ወደ የGoogle መለያዎ ሲገቡ እና የድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴ ቁጥጥር ሲያነቁ በቀዳሚ ፍለጋዎችዎ እና በሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ላይ ባለዎት እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረቱ ይበልጥ ተገቢ የሆኑ የፍለጋ ውጤቶችን ማግኘት ይችላሉ። እዚህ የበለጠ መረዳት ይችላሉ። እንዲሁም ዘግተው ሲወጡም እንኳ ብጁ የፍለጋ ውጤቶችን ማግኘት ይችላሉ። በዚህ ደረጃ የተበጀ ፍለጋ ካልፈለጉ በግል መፈለግ እና ማሰስ ወይም ተዘግቶ የተወጣ የፍለጋ ግላዊነት ማላበስን ማጥፋት ይችላሉ።

አላግባብ መጠቀምን ማግኘት

መመሪያዎቻችንን በመጣስ አይፈለጌ መልዕክት፣ ተንኮል-አዘል ዌር፣ ህገወጥ ይዘት እና ሌሎች የአላግባብ መጠቀም አይነቶችን በስርዓቶቻችን ላይ ስናገኝ መለያዎን ልናሰናክል ወይም ሌላ አግባብ የሆነ እርምጃ ልንወስድ እንችላለን። በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ ጥሰቱን አግባብ ለሆኑ ባለስልጣናትም ሪፖርት ልናደርግ እንችላለን።

ብዙ ሰዎች የሆነ ነገር መፈለግ ሲጀምሩ ይሄ በዚያ ጊዜ ላይ ስላሉ ለየት ያሉ አዝማሚያዎች ጠቃሚ የሆነ መረጃ ሊያቀርብ ይችላል። Google አዝማሚያዎች ፍለጋዎች በተወሰነ ጊዜ ላይ ያላቸው ታዋቂነትን ለመገመትና እነዚያ ውጤቶች በይፋ በተዋሃደ መልኩ ለማጋራት የGoogle ድር ፍለጋዎች ናሙናን ይወስዳል። የበለጠ ለመረዳት

አገልግሎቶቻችን እንደታሰቡት መስራታቸውን ማረጋገጥ

ለምሳሌ፣ ችግሮች ካሉ ለማግኘት ስርዓቶቻችንን በቋሚነት እንከታተላለን። እና በአንድ የተወሰነ ባህሪ ላይ ችግር ካገኘን ከችግሩ በፊት የነበረ የእንቅስቃሴ መረጃን መገምገም ነገሮችን በበለጠ ፍጥነት እንድናስተካክላቸው ያስችለናል።

አገልግሎቶቻችንን ማድረስ

አገልግሎቶቻችንን ለማድረስ መረጃዎን የምንጠቀምባቸው መንገዶች ምሳሌዎች፦

  • እንደ አንድ የYouTube ቪዲዮ መጫን ያለ እርስዎ የጠየቁትን ውሂብ ለመላክ ለመሣሪያዎ የተመደበውን የአይፒ አድራሻ እንጠቀማለን
  • የGoogle መለያዎ መዳረሻ ሊኖረው የሚገባ ሰው እርስዎ መሆንዎን ለማረጋገጥ በመሣሪያዎ ላይ ባሉ ኩኪዎች ውስጥ የተከማቹ ልዩ ለዪዎችን እንጠቀማለን
  • ወደ Google ፎቶዎች የሚሰቅሏቸው ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች እርስዎ ሊያጋሯቸው የሚችሏቸው አልበሞችን፣ እነማዎችን እና ሌሎች ፈጠራዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ ጥቅም ላይ ይውላሉ። የበለጠ ለመረዳት
  • የሚቀበሉት የበረራ ማረጋገጫ ኢሜይል በእርስዎ Gmail ውስጥ የሚታይ የ«ተመዝግቦ-መግቢያ» አዝራር ለመፍጠር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል
  • ከእኛ የአገልግሎቶች ወይም የዕቃዎች ግዢ ሲፈጽሙ የመላኪያ አድራሻዎን ወይም የመላኪያ መመሪያዎችን የመሳሰሉ መረጃዎች ሊሰጡን ይችላሉ። ይህን መረጃ ትዕዛዝዎን ማካሄድ፣ መፈጸም እና ማድረስ ለመሳሰሉ ጉዳዮች እና ከሚገዙት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር በተያያዘ ድጋፍ ለማቅረብ እንጠቀምበታለን።

እነሱን በመወከል ማስታወቂያ እና የጥናትና ምርምር አገልግሎቶች

ለምሳሌ፣ ማስታወቂያ ሰሪዎች የማስታወቂያ ዘመቻዎቻቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ውሂብ ከታማኝነት-ካርድ ፕሮግራሞቻቸው ሊሰቅሉ ይችላሉ። የተዋሃዱ ሪፖርቶች የግለሰቦች መረጃን አሳልፈው ለማይሰጡ ማስታወቂያ ሰሪዎች ብቻ ነው የምናቀርበው።

እይታዎች እና ከይዘትና ማስታወቂያዎች ጋር ያሉ መስተጋብሮች

ለምሳሌ፣ እንደ ማስታወቂያ በአንድ ገጽ ላይ ከቀረበ እና በአንድ ተመልካች ታይቶ ከሆነ ያሉ የተዋሃዱ ሪፖርቶች ለማስታወቂያ ሰሪዎች ለማቅረብ በማስታወቂያዎች ላይ ስላሉ እይታዎች እና መስተጋብሮች መረጃ እንሰበስባለን። እንዲሁም እንደ መዳፊትዎን በአንድ ማስታወቂያ ላይ ወስደው ከሆነ ወይም ማስታወቂያው ከቀረበበት ገጽ ጋር መስተጋብር ፈጥሮ ከሆነ ያሉ ሌሎች መስተጋብሮችን ልንለካ እንችላለን።

ከመሣሪያዎ አጠገብ ስላሉ ነገሮች መረጃ

በAndroid ላይ የGoogle አካባቢ አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ከሆኑ እንደ Google ካርታዎች ያሉ በአካባቢዎ ላይ የሚተማመኑ የመተግበሪያዎች አፈጻጸምን ማሻሻል እንችላለን። የGoogle አካባቢ አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ከሆኑ መሣሪያዎ ስለአካባቢው፣ መዳሰሻዎች (እንደ የፍጥነት መለኪያ ያሉ) እና በአቅራቢያ ያሉ የሕዋስ ማማዎች እና የWi-Fi መዳረሻ ነጥቦች (እንደ የማክ አድራሻ እና የምልክት ጥንካሬ) ያለ መረጃ ለGoogle ይልካል። አካባቢዎን ለማወቅ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ያስፈልጋሉ። የGoogle አካባቢ አገልግሎቶችን ለማንቃት የመሣሪያዎን ቅንብሮች መጠቀም ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት

ከአላግባብ መጠቀም ለመከላከል

ለምሳሌ፣ የደህንነት ስጋቶች መረጃ መለያዎ ተጠልፏል ብለን ካሰብን እንድናሳውቅዎ ያግዘናል (በዚህ ጊዜ መለያዎን ለመጠበቅ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች እንዲወስዱ ማገዝ እንችላለን)።

ከGoogle መለያዎ ጋር የተጎዳኘ

የእርስዎ Chrome አሰሳ ታሪክ በመለያው ላይ የሚቀመጠው ከGoogle መለያዎ ጋር የChrome ስምረትን ካነቁ ብቻ ነው። የበለጠ ለመረዳት

ከGoogle ጋር አጋር መሆን

ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከGoogle ጋር አጋር የሆኑ ከ2 ሚሊዮን በላይ የGoogle ያልሆኑ ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች አሉ። የበለጠ ለመረዳት

የመሣሪያዎ የመዳሰሻ ውሂብ

መሣሪያዎ የእርስዎን አካባቢ እና እንቅስቃሴ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ መዳሰሻዎች ሊኖራቸው ይችላል። ለምሳሌ፣ የፍጥነት መለኪያ መሣሪያ የእርስዎን ፍጥነትን ለማወቅ እና ጋይሮስኮፕ የጉዞዎን አቅጣጫ ለማወቅ ጥቅም ላይ መዋል ይችላሉ።

የምንሰበስበውን መረጃ ማጣመር

የምንሰበሰበውን መረጃ የምናጣምርባቸው አንዳንድ ምሳሌዎች እነዚህን ያካትታሉ፦

  • ወደ Google መለያዎ ሲገቡ እና በGoogle ላይ ፍለጋ ሲያደርጉ ይፋዊ የድር ፍለጋ ውጠቶችን እንደ Gmail ወይም Google ቀን መቁጠሪያ ባሉ ሌሎች የGoogle ምርቶች ውስጥ ካለዎት ይዘት ጋር አብረው ይመለከታሉ። ይህ እንደ የእርስዎ መጪ በረራዎች፣ ምግብ ቤት፣ የተያዙ የሆቴል ክፍሎች ወይም ፎቶዎች ያሉ ነገሮችን ሊያካትት ይችላል። የበለጠ ለመረዳት
  • ከሆነ ሰው ጋር በGmail በኩል ከተገናኙና እሱን ወደ አንድ የGoogle ሰነድ ወይም በGoogle ቀን መቁጠሪያ ውስጥ ባለ አንድ ክስተት ላይ ማከል ከፈለጉ ስሙን መተየብ ሲጀምሩ Google በራስ-በማጠናቀቅ ቀላል ያደርገዋል። ይህ ባህሪ ነገሮችን ለሚያውቋቸው ሰዎች ማጋራት ቀላል ያደርገዋል። የበለጠ ለመረዳት
  • በቅንብሮችዎ የሚወሰን ሆኖ የGoogle መተግበሪያው በሌሎች የGoogle ምርቶች ውስጥ ያለዎትን ውሂብ ተጠቅሞ ግላዊነት የተላበሰ ይዘትን ሊያሳየዎት ይችላል። ለምሳሌ፣ ፍለጋዎችን በእርስዎ የድር እና መተግበሪያ እንቅስቃሴ ላይ የሚያከማቹ ከሆኑ የGoogle መተግበሪያው እንደ የስፖርት ውጤቶች ያሉ በእንቅስቃሴዎ ላይ የተመሠረቱ የፍላጎቶችዎ ዜና ዘገባዎችን እና ሌሎች መረጃዎችን ሊያሳየዎት ይችላል። የበለጠ ለመረዳት
  • የGoogle መለያዎን ከእርስዎ Google Home ጋር ካገናኙት በGoogle ረዳት በኩል መረጃዎን ማቀናበር እና ነገሮችን ማከናወን ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ክስተቶችን በእርስዎ Google ቀን መቁጠሪያ ላይ ማከል ወይም የዕለቱ መርሐግብርዎን ማግኘት፣ በመጪ በረራዎ ላይ የሁኔታ ዝማኔዎችን መጠየቅ ወይም እንደ የመኪና አቅጣጫዎች ያለ መረጃ ወደ ስልክዎ መላክ ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት

የተወሰኑ አጋሮች

ለምሳሌ፣ የYouTube ፈጣሪዎች እና ማስታወቂያ ሰሪዎች ኩኪዎችን ወይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ስለYouTube ቪዲዮዎቻቸው ወይም ማስታወቂያዎቻቸው ታዳሚዎች እንዲያውቁ ከልኬት ኩባንያዎች ጋር እንዲሰሩ እንፈቅዳለን። ሌላ ምሳሌ ደግሞ በእኛ የገበያ ገጾች ላይ ምን ያህል የተለያዩ ሰዎች የምርት ዝርዝሮቻቸውን እንደሚመለከቱ ለመረዳት ኩኪዎችን የሚጠቀሙ ነጋዴዎች ናቸው። ስለእነዚህ አጋሮች እና መረጃዎን እንዴት እንደሚጠቀሙ የበለጠ ይረዱ

የተወሰኑ የGoogle አገልግሎቶች

ለምሳሌ፣ የእርስዎን ጦማር ከጦማሪ ወይም እርስዎ ባለቤት የሆኑበት የGoogle ጣቢያ ከGoogle ጣቢያዎች መሰረዝ ይችላሉ። እንዲሁም እርስዎ ለመተግበሪያዎች፣ ጨዋታዎች ወይም በPlay መደብር ላይ ላሉ ሌሎች ይዘቶች የሰጧቸውን ግምገማዎችም መሰረዝ ይችላሉ።

የክፍያ መረጃ

ለምሳሌ፣ በGoogle መለያዎ ላይ ክሬዲት ካርድ ወይም ሌላ የመክፈያ ዘዴ ካከሉ በመላ አገልግሎቶቻችን ላይ እንደ በPlay መደብር ውስጥ ያሉ መተግበሪያዎች ያሉ ነገሮችን ለመግዛት ሊጠቀሙበት ይችላሉ። እንዲሁም ክፍያዎን መስራት እንዲያግዝ እንደ የንግድ ግብር መታወቂያ ያለ ሌላ መረጃ ልንጠይቅ እንችላለን። በአንዳንድ አጋጣሚዎች እንዲሁም ማንነትዎን ማረጋገጥ እና ይህን ለማድረግ መረጃ ልንጠይቀዎት እንችላለን።

እንዲሁም ለምሳሌ የGoogle መለያ ለመጠቀም ዕድሜዎ በቂ እንዳልሆነ የሚያመለክት ትክክል ያልሆነ የልደት ቀን አስገብተው ከሆነ እርስዎ የዕድሜ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆንዎን ለማረጋገጥ የክፍያ መረጃን ልንጠቀም እንችላለን። የበለጠ ለመረዳት

የGoogle መተግበሪያዎች ያለው የAndroid መሣሪያ

የGoogle መተግበሪያዎች ያላቸው የAndroid መሣሪያዎች በGoogle ወይም በአንዱ አጋራችን የሚሸጡ መሣሪያዎች እና ስልኮችን፣ ካሜራዎችን፣ ተሽከርካሪዎችን፣ ተለባሾችን እና ቴሊቪዥኖችን ያካትታሉ። እነዚህ መሣሪያዎች የGoogle Play አገልግሎቶችን እና እንደ Gmail፣ ካርታዎች፣ የስልክዎ ካሜራ እና የስልክ መደወያ፣ የንግግር-ወደ-ጽሑፍ ልወጣ፣ የቁልፍ ግቤት እና የደህንነት ባህሪያት ያሉ አገልግሎቶችን የሚያካትቱ ሌሎች ቅድሚያ የተጫኑ መተግበሪያዎችን ይጠቀማሉ።

ደህንነት እና አስተማማኝነት

የአገልግሎቶቻችን ደህንነት እንዲጠበቅ አስተማማኝ እንዲደረግ ለማገዝ መረጃዎን የምንጠቀምባቸው አንዳንድ ምሳሌዎች እነዚህን ያካትታሉ፦

  • ከራስ-ሰር አላግባብ መጠቀም ለመጠበቅ የአይፒ አድራሻዎችን እና የኩኪ ውሂብን መሰብሰብና መተንተን። ይህ አላግባብ መጠቀም እንደ አይፈለጌ መልዕክት ወደ Gmail ተጠቃሚዎች መላክ፣ በተጭበረበረ ሁኔታ ማስታወቂያዎች ላይ ጠቅ በማድረግ ከማስታወቂያ ሰሪዎች መስረቅ ወይም የተሰራጨ የአገልግሎት ክልከላ (ዲዶስ/DDoS) ጥቃትን በማስጀመር ይዘትን ሳንሱር ማድረግ ያሉ ብዙ መልክ ሊይዝ ይችላል።
  • በGmail ውስጥ ያለው «የመጨረሻ መለያ እንቅስቃሴ» ባህሪ የሆነ ሰው እርስዎ ሳያውቁ ኢሜይልዎን ደርሶ ከሆነ እንዲያውቁ ያግዘዎታል። ይህ ባህሪ እንደ መልዕክትዎን የደረሱ የአይፒ አድራሻዎች፣ ተጓዳኙ አካባቢ እና የተደረሰበት ቀን እና ሰዓት ያሉ በGmail ውስጥ ስለነበረ የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴ መረጃ ያሳየዎታል። የበለጠ ለመረዳት

ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎች

እንዲሁም ከማስታወቂያ ሰሪው በመጣ መረጃ ላይ የተመሠረቱ ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችም ሊያዩ ይችላሉ። ለምሳሌ አንድ ማስታወቂያ ሰሪ ጋር ሸምተው ከሆነ ያንን መረጃ ተጠቅመው ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን ሊያሳዩ ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት

ጥሪዎች የሚደረጉባቸው እና የሚቀበሉባቸው ወይም መልዕክቶችን የሚልኩባቸው እና የሚቀበሉባቸው አገልግሎቶች

የእነዚህ አገልግሎቶች ምሳሌዎች እነዚህን ያካትታሉ፦

  • Google Hangouts፣ አገር-ውስጥ እና አለምአቀፍ ጥሪዎችን ለማድረግ
  • Google ድምጽ፣ ጥሪዎችን ለማድረግ፣ የጽሑፍ መልዕክቶችን ለመላክ እና የድምጽ መልዕክትን ለማቀናበር
  • Google Fi፣ ለስልክ ዕቅድ
Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ