ይሄ በማህደራችን የተመዘገበ የግላዊነት ፖሊሲያችን ስሪት ነው። ያሁኑን ስሪት ወይም ሁሉንም ያለፉት ስሪቶች እይ።

የግላዊ ሁኔታ መመሪያ

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፦ 18 ዲሴምበር 2017 (የተመዘገቡ ስሪቶችን አሳይ)

መረጃን ለመፈለግ እና ለማጋራት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘት ወይም አዲስ ይዘት ለመፍጠር – አገልግሎቶቻችንን መጠቀም የምትችልበት የተለያዩ በርካታ መንገዶች አሉ። ከኛ ጋር መረጃ ስታጋራ፣ ለምሳሌ የGoogle መለያ በመፍጠር፣ የበለጠ ተዛማጅነት ያላቸውን የፍለጋ ውጤቶችን እና ማስታወቂያዎች ለማሳየት፣ ከሰዎች ጋር እንድትገናኝ ለማገዝ ወይም ለሌሎች ጋር ማጋራትን ይበልጥ ፈጣን እና ቀላል ለማድረግ– እነዚያን አገልግሎቶች የበለጠ የተሻሉ እንዲሆኑ እናደርጋለን። የኛን አገልግሎቶች እንደመጠቀምህ፣ እንዴት መረጃን እንደምንጠቀም እና ግላዊነትህን መጠበቅ የምትችልባቸው መንገዶችን በተመለከተ ግልጽ እንዲሆንልህ እንፈልጋለን።

የእኛ የግላዊነት መምሪያ የሚከተለውን ያስረዳል፦

  • ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ እና ለምን እንደምንሰበስብ።
  • መረጃውን እንዴት እንደምንጠቀምበት።
  • መረጃን መድረስ እና ማዘመን የሚቻልበትን መንገድ ጨምሮ የምናቀርባቸው አማራጮች።

ፖሊሲውን በተቻለ መጠን ቀላል እንዲሆን ለማድረግ ሞክረናል፣ ሆኖም ግን እንደ ኩኪስ /Cookies/፣ አይፒ አድራሻ /IP Address/፣ ፒክሴል መለያ /pixel tags/ እና አሳሾች0020/Browsers/ ለመሳሰሉት ቃላት አዲስ ከሆንክ፣ በመጀመሪያ ስለነዚህ ቁልፍ ቃላት ትርጉም አንብብ። አዲስ የጉግል ተጠቃሚም ሆንክ የጉግል የረዥም ጊዜ ደንበኛ፣ ያንተን የግላዊነት መብት ማስጠበቅ ለGoogle የሚያሳስበው ጉዳይ ነው፣ ስለሆነም እባክህ ጊዜ ወስደህ ስለኛ አሰራር ለማወቅ ሞክር – ጥያቄ ካለህም አግኘን

የምንሰበስበው መረጃ

ለእኛ ተጠቃሚዎች የተሻሉ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንዲቻል – የትኛውን ቋንቋ እርስዎ እንደሚናገሩ ማወቅ ከመሰሉ መሰረታዊ ነገሮች ጀምሮ እስከ እንደ የትኞቹ ማስታወቂያዎች እርስዎ ጠቃሚ ሆነው እንደሚያገኙዋቸውበመስመር ላይ ከማንም በላይ ለእርስዎ ፋይዳ ያላቸው ሰዎች፣ ወይም የትኞቹን የYouTube ቪዲዮዎች እርስዎ ሊወዱዋቸው እንደሚችሉ የመሳሰሉ ውስብስብ ነገሮች ድረስ ለማወቅ እንድንችል መረጃ እንሰበስባለን።

መረጃ በሚከተሉት መንገድ ነው የምንሰበስበው፦

  • በሚሰጡን መረጃ። ለምሳሌ፣ አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን የGoogle አድራሻ አንዲኖርዎ የሚፈልጉ ናቸው። ሲመዘገቡ እንደ የእርስዎ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር ወይም ክሬዲት ካርድ ያሉ በመለያዎ ላይ (እንዲከማቹ)የሚከማቹ የግል መረጃ እንጠይቀዎታለን። በምንሰጣቸው የማጋራት ባህሪያት ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለጉ ስምዎን እና ፎቶዎን የሚያካትት በይፋ የሚታይ የGoogle መገለጫ እንዲፈጥሩ ልንጠይቅዎ እንችላለን።

  • አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ የምናገኘው መረጃ። እንደ YouTube ላይ አንድ ቪዲዮ መመልከት፣ የማስታወቂያ አገልግሎታችንን የሚጠቀም ድር ጣቢያን መጎብኘት ወይም ማስታወቂያዎቻችን እና ይዘቶችን ማየት እና ከእነሱ ጋር መስተጋብር መፍጠር ያሉ ስለሚጠቀሙባቸው አገልግሎቶች እና እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው ላይ መረጃ እንሰበስባለን። ይህ መረጃ የሚከተለውን ያካትታል፦

    • የምትጠቀምበትን ኮምፒዩተር ወይም ፕሮግራም የሚመለከት መረጃ

      መሣሪያ-ተኮር መረጃ (የእርስዎ ሃርድዌር ሞዴል፣ ኮምፒዩተርዎ የሚሰራበትን ስርዓተ ክወና ስሪት ዓይነት፣ መሣሪያ ለይቶ አዋቂዎች፣ እና የስልክ ቁጥርን ጨምሮ የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ መረጃዎችን የመሳሰሉ) እንሰበስባለን። Google የኮምፒውተር መሳሪያ መለያዎችዎን ወይም ስልክ ቁጥርዎን ከGoogle መለያዎ ጋር ሊያዛምድ ይችላል።

    • ምዝግብ ማስታወሻ

      የእኛን አገልግሎቶች ሲጠቀሙ ወይም በGoogle የቀረበ ይዘትን በሚመለከቱበት ጊዜ፣ በራስ-ሰር የተወሰነ መረጃ እንሰበስብ እና በአገልጋይ ምዝገባዎች ላይ እናከማቻለን። ይህ የሚከተሉትን ያካትታል፦

      • አገልግሎታችንን እንዴት እንደተጠቀሙ ለምሳሌ የፍለጋ ጥያቄዎችዎን ዝርዝሮች።
      • እንደ የስልክ ቁጥርዎ፣ የደወለልዎ አካል ስልክ ቁጥር፣ የማስተላለፊያ ቁጥሮች፣ የጥሪዎች ጊዜ እና ቀን፣ የጥሪው ቆይታ ጊዜ፣ ኤስኤምኤስ ማስተላለፊያ መረጃ እና የጥሪዎች አይነቶች ያሉ የስልክ ምዝግብ መረጃዎች።
      • የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አማራጮች
      • እንደ ብልሽቶች፣ የስርዓት እንቅስቃሴ፣ የሃርድዌር ቅንጅቶች፣ የአሳሽ ዓይነት፣ አሳሽ ቋንቋ፣ የጥያቄዎ ቀን እና ጊዜ እና ማጣቀሻ ዩአርኤል ያለ የመሳሪያ ሁኔታ መረጃ።
      • አሳሽዎን ወይም የGoogle መለያዎን በልዩ ሁኔታ ለይተው ሊያውቁ የሚችሉ ኩኪዎች።
    • የስፍራ መረጃ

      የGoogle አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ፣ ስለተጨባጩ ያሉበት ስፍራ መረጃዎችን ልንሰበስብ እና ልናስኬዳቸው እንችላለን። የአይፒ አድራሻ፣ ጂፒኤስ ጨምሮ፣ ለምሳሌ ለGoogle በአቅራቢያ ያሉ መሣሪያዎችን፣ Wi-Fi መዳረሻ ነጥቦችን እና የሞባይል ስልክ ማማዎችን በተመለከተ መረጃ የሚሰጡ ሌሎች አንፍናፊዎችን የመሳሰሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የመገኛ አካባቢን ለይቶ ለማወቅ እንጠቀማለን።

    • ልዩ መተግበሪያ ቁጥሮች

      የተወሰኑ አገልግሎቶች ልዩ መተግበሪያ ቁጥር ያካትታሉ። ስለ አጫጫንዎ (ለምሳሌ፣ የክወና ስርዓት ዓይነት እና የመተግበሪያ ስሪት ቁጥር) ያንን አገልግሎትን ሲጭኑ ወይም ሲያራግፉ ወይም አገልግሎት ለምሳሌ ለራስ ሰር ዝማኔዎች በተወሰነ ጊዜ ወቅት ጠብቆ የእኛን አገልጋዮች ሲገናኝ ይህ ቁጥር እና መረጃ ወደ Google ሊላክ ይችላል።

    • አካባቢያዊ ማከማቻ

      መረጃ (የግል መረጃን ጨምሮ) ልንሰበስብ እና እንደ የአሳሽ ድር ክምችት (ኤችቲኤምኤል 5ን ጨምሮ) እና የመተግበሪያ ውሂብ መሸጎጫዎች ያሉ ስልቶችን በመጠቀም በመሣሪያዎ ላይ ልናከማች እንችላለን።

    • ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች

      አንድ የGoogle አገልግሎት ሲጎበኙ እኛ እና አጋሮቻችን መረጃን ለመሰብሰብ እና ለማከማቸት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን፣ እና ይሄ የእርስዎን አሳሽ ወይም መሣሪያ ለመለየት ኩኪዎችን ወይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ሊያካትት ይችላል። እንዲሁም እንደ የማስታወቂያ አገልግሎቶች ወይም በሌሎች ጣቢያዎች ላይ ብቅ የሚሉ የGoogle ባህሪያት ያሉ ለአጋሮቻችን ከምናቀርባቸው አገልግሎቶች ጋር መስተጋብር ሲፈጥሩ መረጃን ለመሰብሰብ እና ለማከማቸት እነዚህን ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። የእኛ የGoogle ትንታኔዎች ምርት ንግዶች እና የጣቢያዎች ባለቤቶች ወደ ድር ጣቢያዎቻቸው እና መተግበሪያዎቻቸው የሚሄድ ትራፊክ እንዲተነትኑ ያግዛቸዋል። እንደ የDoubleClick ኩኪን የሚጠቀሙ ካሉ የማስታወቂያ ሰሪዎቻችን ጋር አንድ ላይ ሲሰራበት የGoogle ትንታኔዎች መረጃ የGoogle ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደ በርካታ ጣቢያዎች በተደረጉ የጉብኝቶች መረጃ በGoogle ትንታኔዎችች ደንበኛ ወይም በGoogle ይገናኛል

ከአጋሮች ስለእርስዎ ያገኘነው መረጃ በተጨማሪ Google ውስጥ ገብተው ባሉበት ጊዜ የሰበሰብነው መረጃ ከእርስዎ Google መለያ ጋር ይጎዳኝ ይሆናል። መረጃ ከGoogle መለያዎ ጋር የተጎዳኘ ሲሆን እንደ የግል መረጃ አድርገን ነው የምንይዘው። እንዴት ከGoogle መለያዎ ጋር የተጎዳኘ መረጃን መድረስ፣ ማቀናበር ወይም መሰረዝ እንደሚችሉ መረጃ ለማግኘት የዚህ መመሪያ የግልጽነት እና ምርጫ ክፍሉን ይጎብኙ።

የምንሰበስበውን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም

ሁሉንም አገልግሎታችን ለማቅረብለመያዝለመጠበቅ እና እነሱን ለማሻሻል፣ አዲስ አገልግሎቶችን ለመገንባት እና Google እና ተጠቃሚዎቻችንን ለመጠበቅ ከእነሱ የምንሰበስበውን መረጃ እንጠቀማለን። እንዲሁም እንደ ይበልጥ ተገቢ የፍለጋ ውጤቶችን እና ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ መስጠት ያሉ ግላዊነት የተላበሰ ይዘት ለእርስዎ ለማቅረብ ይህን መረጃ እንጠቀማለን።

ለሁሉም የGoogle መለያ የሚጠይቁ አገልግሎቶች በሙሉ ለGoogle መገለጫ የሰጡትን ስም ልንጠቀምበት እንችላለን። በተጨማሪ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻችን ዙሪያ በወጥነት እንዲወከሉ ከGoogle መለያዎ ጋር የተቆራኙ ሌሎች የዱሮ ስሞችዎን ልንተካቸው እንችል ይሆናል። ሌሎች ተጠቃሚዎች አስቀድመው የእርስዎ ኢሜይል ወይም እርስዎን ለይቶ የሚያሳውቅ ሌላ መረጃ ካላቸው በይፋ የሚታዩትን እንደ ስምዎ እና ፎቶዎ ያሉ የእርስዎን የGoogle መገለጫ መረጃዎች ልናሳያቸው እንችላለን።

የGoogle መለያ ካልዎት የእርስዎን የመገለጫ ስም፣ የመገለጫ ፎቶ እና በGoogle ወይም ከእርስዎ የGoogle መለያ ጋር በተገናኙ የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ላይ የሚወስዷቸውን እንቅስቃሴዎች (እንደ +1 ዎች፣ የጻፏቸው ግምገማዎች እና የለጠፏቸው አስተያየቶችን) ማስታወቂያዎች እና በሌሎች ንግድ ነክ አገባቦችን ጨምሮ በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ልናሳያቸው እንችላለን። እርስዎ በእርስዎ የGoogle ላይ ማጋራትን ወይም የታይነት ቅንብሮችን ለመገደብ ያደርጉዋቸውን ምርጫዎች እናከብርልዎታለን።

Googleን በሚያነጋግሩበት ጊዜ፣ ሊያጋጥምዎት የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት ለማገዝ እንዲቻል ከእርስዎ ጋር የሚደረገውን የመልዕክት ልውውጥ ሪኮርድ እንይዛለን። የኢሜይል አድራሻዎን ስለአገልግሎቶቻችን መረጃ ለመስጠት ማለትም በቅርቡ እንደሚደረጉ ለውጦች ወይም መሻሻሎች ያሉ መረጃዎችን ለእርስዎ ለመስጠት ልንጠቀምበት እንችላለን።

የተጠቃሚ ተሞክሮዎን እና የአገልግሎቶቻችን አጠቃላይ ጥራት ለማሻሻል እንደ የፒክስል መለያዎች ያሉ ኩኪዎች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን እንጠቀምበታለን። በእኛ አገልግሎቶች ላይ ይህን ለማድረግ ከምንጠቀምባቸው ምርቶች መካከል አንዱ Google ትንታኔዎች ነው። ለምሳሌ፣ የቋንቋ ምርጫዎችዎን በማስቀመጥ በሚመርጡት ቋንቋ አገልግሎቶቻችን እንዲታዩዎ ለማድረግ እንችላለን። ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ስናሳየዎት ከኩኪዎች ወይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች የመጣ ለዪ እንደ በዘር፣ ኃይማኖት፣ ጾታዊ ዝንባሌ ወይም ጤና በተመሠረቱ ያሉ ሚስጥራዊነት ካላቸው ምድቦች ጋር አናጎዳኝም።

በራስ-ሰር የሚሰሩ ስርዓቶቻችን እንደ ብጁ የፍለጋ ውጤቶች፣ የተበጁ ማስታወቂያዎች እና የአይፈለጌ መልዕክት እና የተንኮል-አዘል ዌር ማወቅ ያሉ በግል ለእርስዎ ተገቢ የሆኑ ባህሪያትን ለማቅረብ ይዘትዎን (ኢሜይሎችም ጭምሮ) ይተነትናሉ።

ከአንድ አገልግሎት የመጣን መረጃ የግል መረጃን ጨምሮ ከሌሎች Google አገልግሎቶች ከሚገኝ መረጃ ጋር ልናጣምር እንችላለን – ለምሳሌ፣ ነገሮችን ለሚያውቋቸው ሰዎች ማጋራት ይበልጥ ቀላል ለማድረግ። በእርስዎ የመለያ ቅንብሮች የሚወሰን ሆኖ በሌሎች ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ ያለው እንቅስቃሴዎን የGoogle አገልግሎቶችን እና በGoogle የሚላኩ ማስታወቂያዎችን ለማሻሻል ከግል መረጃዎ ጋር ሊጎዳኝ ይችላል።

በዚህ የግላዊነት መምሪያ ከተቀመጡት ምክንያቶች እና ሁኔታዎች ውጪ መረጃዎን መጠቀም ቢያስፈልገን በቅድሚያ ፈቃደኛ መሆንዎን እንጠይቅዎታለን።

Google የግል መረጃዎችን በመላ ዓለም በሚገኙ በርካታ ሃገሮች በእኛ አገልጋዮች አማካኝነት ያስኬዳል። የግል መረጃዎን ከሚኖሩበት ሃገር ውጪ ባለ አገልጋይ ላይ ልናስኬደው እንችል ይሆናል።

የአሰራር ግልጽነት እና ምርጫዎች

ሰዎች የተለያዩ ስለግላዊነት መብት የሚያሳስቡዋቸው ነገሮች አሉ። መረጃው እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል አውቀው ትርጉም ያለው ምርጫ እንዲያደርጉ፣ ዓላማችን ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ ግልጽ ሆኖ መገኘት ነው። ለምሳሌ፣ የሚከተለውን ማድረግ ይችላሉ፦

  • የGoogle አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ እንደ በYouTube ላይ የተመለከቷቸው ቪዲዮዎች ወይም ያለፉ ፍለጋዎችዎ ያሉ ምን አይነት ውሂብ በመለያዎ ላይ እንደሚቀመጥ ለመወሰን የGoogle እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎችዎን ይከልሱና ያዘምኑ። እንዲሁም ከመለያዎ ወጥተው ሳለ አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ የተወሰነ እንቅስቃሴ በመሣሪያዎ ላይ በኩኪ ወይም በተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ይከማች እንደሆነ ለማቀናበር እነዚህን መቆጣጠሪያዎችም መጠቀም ይችላሉ።
  • Google Dashboard በመጠቀም ከእርስዎ የGoogle መለያ ጋር የተሳሰሩ የተወሰኑ አይነት መረጃዎችን ይገምግሙ እና ይቆጣጠሩ።
  • የማስታወቂያ ቅንብሮችን በመጠቀም እንደ የትኛዎቹ ምድቦች እርስዎን ሊያስደስቱ ይችላሉ ያሉ በGoogle እና በመላው ድር ላይ ለእርስዎ ስለሚታዩ የGoogle ማስታወቂያዎች ምርጫዎችዎን ይመልከቱ እና ያርትዑ። እንዲሁም ከተወሰኑ የGoogle ማስታወቂያ አገልግሎቶች መርጠው ለመውጣት ያንን ገጽ መጎብኘትም ይችላሉ።
  • ከእርስዎ የGoogle መለያ ጋር የተጎዳኘው መገለጫ እንዴት ለሌሎች እንደሚታይ ያስተካክሉ
  • በእርስዎ የGoogle መለያ አማካኝነት መረጃ ለማን እንደሚያጋሩ ይቆጣጠሩ
  • ከእርስዎ የGoogle መለያ ጋር ከተጎዳኘ መረጃ ከብዙዎቹ አገልግሎታችን ይውሰዱ
  • በማስታወቂያዎች ላይ ብቅ በሚሉ በተጋሩ ፈቃድ መስጫዎች ውስጥ የእርስዎ መገለጫ ስም እና የእርስዎ መገለጫ ፎቶ ስለመታየታቸው ወይም አለመታየታቸው ይምረጡ

ከኛ አገልግሎቶች ጋር የተጣመሩ ኩኪዎችን ጨምሮ፣ ሁሉንም ኩኪዎች ለማገድ ወይም ኩኪ በኛ ሲቀናበር እንዲጠቁምህ አሳሽህን ማቀናበር ጭምር ትችላለህ። ሆኖም ግን፣ ኩኪዎችህ እንዲቦዝኑ ከተደረጉ በርካታዎቹ የኛ አገልግሎቶች በሚገባ ሊሰሩ የማይችሉበት ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፣ የቋንቋ ምርጫህን ላናስታውስ እንችላለን።

የሚያጋሩት መረጃ

በርካታዎቹ የኛ አገልግሎቶች መረጃ ከሌሎች ጋር እንድትጋራ ያስችሉሃል። በይፋ መረጃ ስታጋራ፣ በፍለጋ ፕሮግራሞች፣ Googleን ጨምሮ ዋቢ ሊደረግ እንደሚችል አስታውስ። አገልግሎታችን በማጋራት እና በይዘትህን በማስወገድ ረገድ በርካታ አማራጮችን ይሰጡሃል።

የግል መረጃዎን መድረስ እና ማዘመን

አገልግሎቶቻችን በማናቸውም ጊዜ ሲጠቀሙ፣ ወደ ግል መዳረሻ እንዲችሉ ማድረግ ዓላማችን ነው። መረጃው የተሳሳተ ከሆነ፣ መረጃውን ለህጋዊ የንግድ ስራ ምክንያት ወይም ለሕግ ጉዳይ ከእኛ ጋር ማስቀረት ካልተገደድን በቀር – መረጃውን በፍጥነት ሊያዘምኑ የሚችሉበትን ወይም ሊሰርዙ የሚችሉበትን አማራጭ መንገዶች ለማቅረብ ተግተን እንሰራለን።

አገልግሎቶቻችንን ከድንገተኛ እና ከጎጂ ጥፋቶች ለመጠበቅ ዓላማችን ነው። በዚህ ምክንያት፣ ከአገልግሎቶቻችን መረጃ ከሰረዙ በኋላ፣ ትራፊ ቅጂዎችን ከንቁ አገልጋዮች ወዲያውኑ ላንሰርዝ እና ከምትኬ ስርዓቶቻችን ላናስወግድ እንችላለን።

የምናጋራው መረጃ

ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ካልተከሰተ በስተቀር የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ላሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አናጋራም፦

  • በራስዎ ፈቃድ

    የእርስዎን ፈቃድ ካገኘን የግል መረጃን ከGoogle ውጪ ካሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር እናጋራለን። ማናቸውንም ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው የግል መረጃዎችን ለማጋራት ተመርጦ የሚገባበት ፈቃድ መስጫን እንጠይቃለን።

  • ከጎራ አስተዳዳሪዎች ጋር

    የእርስዎ የGoogle መለያ በጎራ አስተዳዳሪ የሚተዳደርልዎ ከሆነ (ለምሳሌ፣ ለG Suite ተጠቃሚዎች) የጎራ አስተዳዳሪዎ እና ለድርጅትዎ የተጠቃሚ ድጋፍ የሚሰጡት መልሶ ሻጮች ለGoogle መለያ መረጃዎ (ኢሜይልዎን እና ሌሎች ውሂቦችን ጨምሮ) መዳረሻ ይኖራቸዋል። የጎራ አስተዳዳሪዎ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፦

    • የድረገጽ አድራሻዎን አጠቃቀም የሚመለከት (ለምሳሌ አዳዲስ ፕሮግራሞች ጭነው አንደሆነ) ስታስቲክስን ማየት።
    • የመለያዎን የይለፍ ቃል መለወጥ።
    • የመለያዎን መዳረሻ ለጊዜው ማገድ ወይም ከናካቴው ማቋረጥ።
    • በመለያዎ እንደ አንድ አካል ሆኖ የተቀመጠን መረጃ መድረስ ወይም መያዝ።
    • ተገቢነት ያለውን ሕግ፣ ደንብ፣ ለማስከበር፣ ሕጋዊ ሂደት ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የመለያህን መረጃ መቀበል።
    • መረጃ ወይም የግላዊነት ቅንብሮችዎን የመሰረዝ ወይም አርትዖት የማድረግ ችሎታዎን መገደብ።

    ለበለጠ መረጃ የጎራዎን አስተዳዳሪ የግላዊነት መረጃ እባክዎ ይመልከቱ።

  • መረጃዎችን ከGoogle ውጭ ለሆኑ አካላት መስጠት

    በመመሪያዎቻችን መሰረት እና በግላዊነት ፖሊሲዎቻችን እና ሌሎች ተገቢነት ያላቸው የሚስጢራዊነት እና የደህንነት እርምጃዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ለተባባሪዎቻችን ወይም ሌሎች የታመኑ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን እኛ ለምንፈልገው ዓላማ እንዲያጠናክሩት እንሰጣለን።

  • ለህጋዊ ምክንያቶች

    ከGoogle ውጪ ላሉ ወደ ግል መረጃ በመድረስ፣ በመጠቀም፣ በማስቀመጥ ወይም ለሌሎች በመግለጽ ላይ ጥሩ እምነት ለምንጥልባቸው ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የግል መረጃን በሚከተሉት ሁኔታዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እናጋራለን፦

    • ማንኛውም የሚመለከተው ህግ፣ ደንብ፣ ህጋዊ ሂደት ወይም ተፈጻሚነት ያለው የመንግስት ጥያቄን ያሟሉ።
    • ተገቢነት ያላቸውን የአገልግሎት ውሎች ሊፈጸም የሚችል የሕግ ጥሰትን ጨምሮ ለማስፈጸም፤
    • ለወንጀል ምርመራ፣ ለመከላከል ወይም በሌላ መልኩ የማጭበርበር ስራን ለማጋለጥ፣ ለደህንነት ወይም ቴክኒካዊ ጉዳዮች፤
    • ህግ በሚፈቅደውና በሚጠይቀው መልኩ በGoogle፣ የእኛ ተጠቃሚዎች ወይም የሕዝቡን መብቶች፣ ንብረቶች ወይም ደህንነቶች ላይ ሊደረስ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል።

በግል ሊለይዩ የማይችል መረጃ እንደ አታሚዎች፣ አሰተዋዋቂዎች ወይም የተገናኙ ጣቢያዎች ላሉ አጋሮቻችን በይፋ ልናጋራ እንችላለን። ለምሳሌ፣ ስለአገልግሎቶቻችን አጠቃላይ አጠቃቀም በተመለከተ ያሉትን አዝማሚያዎች ለማሳየት መረጃን በይፋ ልናጋራ እንችላለን።

Google ከሌላ ድርጅት ጋር ቢዋሃድ፣ ቢወረስ ወይም ንብረቱ ቢሸጥ፣ ማናቸውንም የግል መረጃ ምስጢራዊነት ጠብቀን እንቀጥላለን እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተጠቃሚዎችን የግል መረጃቸው ለሌላ ከመተላለፉ በፊት ወይም የሌላ የተለየ ግላዊነት መምሪያ ተገዢ ከመሆኑ በፊት ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው እናደርጋለን።

የመረጃ ደህንነት ጥበቃ

Google እና የእኛን ተጠቃሚዎች ያልተፈቀደለት ሰው አንዳያገኘው ወይም አንዳይለውጠው ይፋ ማድረግ ወይም የያዝነው መረጃ ከመበላሸት ለመጠበቅ ጠንክረን እንሰራለን። በተለይ፦

  • አብዛኛዎቹን አገልግሎቶቻችንን SSL በመጠቀም እንመሰጥራለን።
  • የእርስዎን የGoogle መለያ ሲደርሱበት Google Chrome ውስጥ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ እና አስተማማኝ የአሰሳ ባህሪይ እናቀርብልዎታለን።
  • የእኛን የመረጃ አሰባሰብ፣ አከመቻቸት እና ሂደት አካሄድ ልማዶች፣ አካላዊ የደህንነት እርምጃዎችን ጨምሮ ፈቃድ ካልተሰጠው ወደ ስርዓቶች መድረስን ለመከላከል ስንል እንገመግማለን።
  • የግል መረጃን ለእኛ ሂደት ለማስኬድ ሲሉ የግል መረጃን የሚፈልጉ የGoogle ሰራተኞች፣ ስራ ተቋራጮች እና ወኪሎች እንዲሁም በውል ሚስጢር እንዲጠብቁ ግዴታ ያለባቸውን ወደ ግል መረጃ መዳረሻ እንዳያገኙ እንገድባቸዋለን፣ እናም እነዚህን ግዴታዎችን ሳይወጡ ቢቀሩ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰደባቸው ወይም ስራቸው እንዲቋረጥ ሊደረግ ይችላል።

ይህ የግላዊነት መመሪያ ሲተገበር

የግላዊነት መመሪያችን በGoogle LLC እና YouTube ጨምሮ አጋሮቹ በሚያቀርቡት አገልግሎቶች፣ Google በAndroid መሳሪያዎች ላይ የሚያቀርባቸው አገልግሎቶች፣ እና በሌሎች ጣቢያዎች ላይ የሚቀርቡ አገልግሎቶች (እንደ የማስታወቂያ አገልግሎታችን ያሉ) ላይ በሙሉ ተግባራዊ ይሆናል፣ ነገር ግን ይህን የግላዊነት መመሪያ የማያካትት የራሳቸው የግላዊነት መመሪያ ያላቸውን አገልግሎቶች አይጨምርም።

የእኛ የግላዊነት መምሪያ በሌሎች ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች እንዲሁም በፍለጋ ውጤቶችዎ ላይ ሊታዩ የሚችሉ ምርቶችን ወይም ጣቢያዎችን፣ የGoogle አገልግሎቶችን የሚያካትቱ፣ ወይም ሌሎች ከእኛ አገልግሎቶች ጋር የተገናኙ ጣቢያዎችን ጨምሮ ተፈጻሚ አይሆንም። የግላዊነት መምሪያችን የእኛን አገልግሎቶች የሚያስተዋውቁ እና ኩኪዎች፣ ፒክስል ስያሜዎችን እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ተዛማጅነት ያላቸውን ለማስተናገድ እና ለማቅረብ የሚጠቀሙ ሌሎች ኩባንያዎች እና ድርጅቶች የመረጃ ልማዶችን አያካትትም።

ከአስተዳዳሪ ባለስልጣናት ጋር ማክበር እና መተባበር

የግላዊነት መመሪያችንን ምን ያህል እንዳከበርን በየጊዜው ግምገማ እናደርጋለን። እንዲሁም የEU-US እና Swiss-US Privacy Shield Frameworks ጨምሮ የተለያዩ የራስ መከታተያ መዋቅሮችንም እናከብራለን። መደበኛ የጽሑፍ ቅሬታዎች ስንቀበል ክትትል ለማድረግ ቅሬታውን ያቀረበውን ሰው እናነጋግራለን። በቀጥታ ከተጠቃሚዎቻችን ጋር ሆነን ለመፍታት ያልቻልናቸውን ማንኛቸውም የግል ውሂብን ማስተላለፍ የሚመለከቱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካባቢያዊ የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣናትን ጨምሮ አግባብነት ካላቸው የክትትል ባለስልጣናት ጋር አብረን እንሰራለን።

ለውጦች

የግላዊነት መምሪያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለወጥ ይችላል። በግልጽ የተቀመጠ ፈቃድዎን ሳናገኝ በዚህ ግላዊነት መምሪያ ላይ ያሉዎን መብቶች አንቀንስም። ማናቸውንም የግላዊነት መምሪያ ለውጦች በዚህ ገጽ ላይ የምንለጥፍ ሲሆን የተደረጉት ለውጦች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ዓይነት ከሆኑ፣ የበለጠ ዋጋ የሚሰጠው ማሳወቂያ (ለተወሰኑ አገልግሎቶች፣ የግላዊነት መምሪያ ለውጦች ኢሜይል ማሳወቂያን ጨምሮ) እንልካለን። ለግምገማ እንዲረዳዎ የዚህን የግላዊነት መምሪያ የቀድሞ እትሞች በቤተ-ማህደር እናስቀምጣቸዋለን።

የተወሰኑ ምርት ልማዶች

የሚከተሉት ማሳወቂያዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ከተወሰኑ የGoogle ምርቶች እና አገልግሎቶች ጋር ያሉ ልዩ የተወሰኑ የግላዊነት ልማዶችን ያብራራሉ፦

ስለእኛ በጣም ተወዳጅ የሆኑ አንዳንድ አገልግሎቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የGoogle ምርት የግላዊነት መመሪያን መጎብኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ ጠቃሚ ከግላዊነት እና ከደህንነት ጋር የሚዛመዱ ይዘቶች በGoogle መመሪያዎች እና የመርህ ገጾች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፣ በሚከተሉትም ውስጥም ጨምሮ፦

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ